መራራው መረራ
አንተነህ መርዕድ

መረራ ትናንትም ዛሬም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ተግቶ የታገለና አሁንም የሚታገል የአገር ጀግና ነው። ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል መረራ ጉዲናንና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ዝም የሚያሰኝ፤ አምባገነናዊ አገዛዝንም ባለበት የሚያፀና ቢሆን ኖሮ ደርግ ባልወደቀም ነበር። መረራም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ትግላቸውን አላቆሙም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አንተነህ መርዕድ

መረራ ትናንትም ዛሬም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ተግቶ የታገለና አሁንም የሚታገል የአገር ጀግና ነው። ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል መረራ ጉዲናንና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ዝም የሚያሰኝ፤ አምባገነናዊ አገዛዝንም ባለበት የሚያፀና ቢሆን ኖሮ ደርግ ባልወደቀም ነበር። መረራም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ትግላቸውን አላቆሙም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ይገረም አለሙ
ፍም አስፈላጊም አላስፈላጊም የሚሆንበት ወቅትና ምክንያት ይኖራል፣ ይህን ለይቶና ተገንዝቦ እፍንም ትፍንም እንደአግባቡ መጠቀም ውጤታማ ያደርጋል። ይህን ለማድረግ የሚቻለው እንቅስቃሴው ግላዊም ይሁን ድርጅታዊ መነሻውን ያወቀ፣ መሄጃ መንገዱን የለየ፣ መድረሻ ግቡን በግልጽ ያስቀመጠና ለግል ሥልጣንና ጥቅም በማሰብ ሳይሆን አገርንና ህዝብን በማስቀደም ላይ የተመሰረተና በስሜት ሳይሆን በእውነት በግብታዊነት ሳይሆን በእቅድና በስልት የሚከናወን ሲሆን ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ይገረም አለሙ
አቶ አሰፋ ጫቦ ከጦቢያ መጽሔት ከህትመት ውጪ መሆን ጋር አብሮ የራቀን ብዕራቸው አልፎ አልፎ በድረ ገጾች ብቅ እያለ እንደናፍቆታችን ባንረካም ከማጣት ይሻል ሆኖን ሰነባብቷል። ሰሞኑን ደግሞ አዘውትረው መከሰት ጀምረዋል እና እሰየው ብለናል። ግና በአብዛኛው የእገሌ ጽሁፍ/ነገር ኮርኩሮኝ እያሉ ብቅ የሚሉ በመሆኑ በቅርቡ ደግሞ ይህን ልጻፍ ብየ አስቤ ሳይሆን ብልጭ ሲልብኝ ወይንም ሲልልኝ ነው የምጽፈው ብለው እቅጩን ስለነገሩን ኮርኳሪ ነገር ከጠፋ ሊጠፉ ነው ብዬ ሰጋሁ። ለነገሩ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለተለከፈ ሰው የሚኮረኩረው አይደለም የሚያስቆጣ የሚያስቆጨው ነገር መች ይጠፋና ነው እንደዚህ ማሰቤ ብዬ ራሴን ብታዘበውም ብልጭ ሲል የሚጻፍና ታስቦ የሚጻፍ ልዩነት ስላለው ይህችን መልእክቴን ለመጻፍ ተነሳሳሁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





በሰፊ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ያልተደገፈ የፖለቲካ ትግል የሥልጣኔ እንቅፋት ነው!
ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
መግቢያ
በአብዛኛዎቹ የሦስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮችና፣ በጠቅላላው የካፒታሊስት አገሮች ተብለው በሚታወቁትና የሳይንስና የቴክኖሎጂ የበላይነትን በተጎናጸፉት አገሮች ያለውን ልዩነት ስንመለከት ልዩነቱ እጅግ ከመስፋቱ የተነሳ እንደዚህ ዐይነቱን የተወሳሰበ ሕብረተሰብ ለመገንባት የብዙ መቶ ዓመታት ሥራ እንደሚያስፈልገን ይታየኛል። በአጠቃላይ ሲታይ የካፒታሊስት አገሮች ይህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ዓለምን መቆጣጠር ሲችሉ እኛን ምን ነካን ብለን የምንጠይቅ ብዙ ላንሆን እንችላለን።
ሙሉውን አስነብበኝ ...




ግርማ ካሳ
ኅዳር 29 ቀን 2009 የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሚል በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በዓል ተዘጋጅቶ ነበር። በዝግጅቱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር አድርገዋል። ይህ ዝግጅት ለአሥራ አንደኛ ጊዜ ሲሆን በሐረር የተከበረው፣ በአሉን የሕዝቦች እኩልነት፣ አብሮ የመኖር የመቻቻል እሴቶችን ለማጎልበት የታሰበ እንደሆነ የገለጹት፣ ጠ/ሚኒስትሩ አሁን ያለውን ሕገ መንግሥት የሕዝቦች የቃል ኪዳን ሰነድ ሲሉም አሞግሰውታል። ቢሆን ደስ ባለን ነበር፤ ግን ሜዳ ላይ ያለው ሁኔታ ካሉት በጣም የተለየ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ተሻለ መንግሥቱ
የአየር ጠባይ:- የሰሞኑ ንፋስ ከባድ ነበር። በተለይ ኅዳር 25 እና 26 ሁለቱን ቀናት አዲስ አበባ ብቻ ሣትሆን ብዙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በኃይለኛ የንፋስ ወጀብ ሲናጡ እንደነበር ከአንዳንድ አካባቢ በተገኙ የሥልክ ልውውጥ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። ብዙ ደካማ ቤቶች የቆርቆሮ ክዳናቸውን ተነጥቀዋል፤ የወያኔዎች ዜጎችን ከመረጃ ውጪ የማድረግ ዕኩይ ባሕርይ ካስከተለው የዲሾች መነቃቀል ባልተናነሰ ብዙ ዲሾች ተነቃቅለውና አቅጣጫቸውን ስተው ጥቂት የማይባሉ ምሥኪን ዜጎችን ላልታሰበ ወጭ ተዳርገዋል፤ የመብራትና የሥልክ ምሰሦዎች ወድቀው ከኃይል መቋረጥ በተጨማሪ ቀላል የማይባል ጉዳት አድርሰዋል፤ ዛፎች ከሥራቸው ተነቃቅለዋል። ... ንፋሱ በዚህ ብዙም ባልተለመደና ባልተጠበቀም የማፍረስ ተግባሩ ሣይወሰን በተጓዳኝ ባስከተለው የጧትና የማታ ቅዝቃዜው በተለይ ባለጠጋዎችን ብዙ ጆንያ ከሰል እንዲጨርሱ አድርጓቸዋል። ... ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ብለን ዝም አልን - ለነገሩ ሌላ ምርጫም አልነበረንም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...