ዶ.ር ፍስሃ እሸቱ፣ ሄኖክ የሺጥላ እና ሌሎች የፌስ ቡክ ታጋዩች!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ታፈሰ ወርቁ

አንዷ ያገሬ ሴት ደጋግማ ስታወራኝ ነው አንዱን የፌስ ቡክ ዝነኛ ታጋይ ያወቅሁት። እንዴት እስካሁን እንዳላየሁት ገርሞኝ በስሙ ፈልጌ ገባሁ። ጊዜየን አላጠፋሁም። ዘጋሁት። ካሁን ቀደም እንዴት የፌስ ቡክ ገጼ ላይ እንደመጣ ሳላውቀው ገጭ ብሎ ባገኘው ከፍቼ አይቸው፣ ሰምቼው... ወዲያው ነበር የዘጋሁት። ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳየው፣ ነብያችን ድንገት ተከስተውለት ኖሮ፣ አዲስ ሙስሊም (convert) ሆኖ ነው መሰለኝ፣ ጥቂት የማውቃቸው ሙስሊም የፌስ ቡክ ወዳጆቼ፣ ላይክ አድርገው “ኢንሻላህ! ሱብሃናሁ ወተዓላ ...”፣ “... እንኳን ወደ እውነተኛው እምነት መጣህ ወንድማችን ...” ... ወዘተ የሚሉ ጽሁፎች ገጹ ስር ተኮልኩለው አይቼ ሳምንት ሳይሞላኝ ነው ያቺው ያገሬ ሴት ስትነግረኝ እንደገና ፈልጌ የገባሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማነህ ባለሳምንት? የ“መሪ” ወርተራ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Assefa Chaboአስፋ ጫቦ

እንደመግቢያ

የኦርቶዶክሶች ማኅበር ቤት ወር ተረኛውን ለመመደብ ዳቦ ከተቆረሰና መውጫ ሲቃረብ ሙሴው ይነሳና፤

ማነህ ባለሳምንት?
ያስጠምድህ ባስራ ስምንት
እኔ ነኝ የምትል የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ ይላል።

ገብርኤሉ እንደማኅበራቸው ታቦት ሥም ይቅያየራል። ተራኛው ይቆምና የሚባለውን ብሎ ጽዋውን ይረከባል። ይህ እውደት በየወሩ ቋሚና ቀጣይ ነው። ከልጅነቴ ያስታወስኩት ነው። እዚህም፤

ማነህ ባለሳምንት?
እኔ ነኝ የምትል ሴራ ወዳጅ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ የአማራ ተጋድሎ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ዶ/ር ተክሉ አባተ

YeAmara tegadelo

ከጥቂት ወራት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረ ከሳቡ ወሳኝ ጉዳዮች ውስጥ የአማራ መደራጀት ዋናው ሳይሆን አልቀረም። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ ጽሑፎችና ንግግሮች ተደርገዋል። አማራው እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ መደራጀትና ራሱን ከተቀነባበረ ጥፋት ማዳን እንዳለበት የሚሞግቱ በርካቶች ናቸው። አሳማኝ የመከራከሪያ ነጥቦችንም አንስተዋል። በአንጻሩ ደግሞ አማራው በኢትዮጵያዊነት እንጅ በነገዱ መታገል መዘዙ ብዙ እንደሆነ ያስጠነቀቁ አሉ። ከሁለቱም ወገኖች አንዳንዶች ነጥቦቻቸውን በምክንያት ወይም በመረጃና በማስረጃ መደገፍ ሲሳናቸው አፍ አውጥተው ሌሎች ጸሐፍትን ሲሳደቡና ”ወያኔ ነህ”፣ ”ፀረ አማራ ነህ” እያሉ ሲያሸማቅቁ ታይተዋል። ከነዚህ ከተሳዳቢዎችና ከአሸማቃቂዎች በስተቀር ለሌሎች ጸሐፍት ከፍ ያለ አክብሮትና ምሥጋና አቀርባለሁ። መሠረት ያላቸው ውይይቶችና ክርክሮች ለሚደረገው ትግል ግልጽነትንና መናበብን ይፈጥራሉና!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእሳት እራት ራሷን ለመታደግ ቀለሟን ቀየረች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Mareshet Mesheshaማርእሸት መሸሻ

ታላቁ የዝግመተ ለውጥ (evolution) ሳይንቲስት ቻርለስ ዳርዊን የነፍሳት ሥነ ነገር (Origin of Species) በተባለው ምርምሩ ላይ የቀመረው ታሪክ አለ። ይህም አንዲት የትንሽ እሳት እራት ዘር (the peppered moth) በህልውናዋ ላይ የተደቀነባትን ድንገተኛ አደጋ እንዴት አድርጋ እንደተወጣችው የሚተርከው ነገር ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1880ዎቹ ዓመታት የተቀሰቀሰው የኢንዱስትሪ አብዮት (industrial revolution) ብዙም ሳይውል ሳያድር የታላቋን ብሪታንያ ገጠር በውበት አልብሶት የነበረውን፤ ቀለሙ ነጣ ያለ ቅጠል የሸፈነው ደንና ጫካ ከየፋብሪካው የተነነው ቆሻሻ ተመልሶ ወደ ህዋ መጥቆ፣ ወደ መሬት ዝናብ ሆኖ ተመልሶ ወርዶ፤ አገሪቱን በጥቅርሻ አለበሳት። ደንና ጫካው ቅጠሉ ነጣ ያለ በነበረበት ጊዜ የምርምሩ አርዕስት የሆነችው እሳት እራት የነበራት ቀለም ነጣ ያለ ነበረ። ከመኖሪያዋና ከአካባቢዋም የሷም ቀለም በመዋሃዱ ምክንያት ራሷን ከወፍ ዕራት ለመሆን አድኗት ነበር። ቅጠሎች በጥቅርሻ ሲሸፈኑ ግን በድንገት ተጋለጠች። ከአካባቢዋ ቀለም የእሳት ራቷ ቀለም ነጥቶ በመታየቷም አዳኝ ወፎች በቀላሉ ይለቅሟት ጀመር። ዘሯ በሙሉ ህልውናው ለአደጋ ተጋለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመሸበት ማደር!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አስፋ ጫቦ

Prof. Merera Gudina in jail

“እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር!” የሚል አባባል አለ። ወዳጄን ዶክተር መረራ ጉዲናን ሳስታውስ ያ አባባል ይመጣብኛል። ከዚያ የተሻለ ሊገልጸው የሚችል አባባል ሊኖር ይችላል። አልመጣልኝም! አሁን ታሰረ! በዚያ ምክንያት ነው ይህንን የምጽፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፍተን ብናየው? የሻዕቢያና የኦነግ መስተፋቅር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Assefa Chaboአስፋ ጫቦ (ዳላስ፣ ቴክሳስ)

እንደመግቢያ

ዛሬ ትንሽ መጻፍ የፈለኩት በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና በኢሳይያስ አፈወርቂ መካከል ያለውን የቆየ ጥብቅ ትስስር በመጠኑ ለመፈተሽ ነው። መነሻ የሆነኝ እንግሊዝ አገር ሎንዶንና አሜሪካ፤ አትላንታ፣ ጆርጂያ የኦሮሞ “ምሁራንና ብሔርተኞች” ያደርጉት ስብሰባና የሰጡት መግለጫ ነው። ያ ራሱን ችሎ መነገር ያለበት ስለሚመስለኝ እመለስበታለሁ። የዚህኛው ዓላማ እዚያ ሰበሰባ ላይ ተካፋይ ከነበሩት “ነፃ አውጭዎች” አንዱን ኦነግን በጨረፍታ ለመታዘብ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ