ከኤርትራ ጋር የመሥራት አስፈላጊነት (አባኪያና ጓደኞቹ)
በኤርትራ በቀር ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስድ መንገድ የለም
አባኪያና ጓደኞቹ ከካናዳ - ነኀሴ 2000 ዓ.ም.
ኤርትራን እንደ አገር፤ ሻዕቢያን እንደ አጋር
ብዙዎቻችሁ ይሄ ቀጥዬ የምጽፈው ነገር፤ ገና ከርዕሱ ወደላይ ሊላችሁ ይችላል። ለምደነዋል። ሃሳብን በነፃነት በመግለጽ መብት ብናምንም፣ ብዙ ራሳችንን እንደ ዲሞክራት የምንቆጥር ሰዎች በፖለቲካችን ውስጥ የሚሰነዘሩ አንዳንድ ሃሳቦች ሽቅብ ሽቅብ ሲሉን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተመልክቻለሁ። ሃሳብ እንደተመልካቹ ነው። አንዳንድ ሰዎች የኤርትራ ነገር እይይይይይይ … ሊያሰኛቸው ይችላል። አንድ ምልከታ ነውና አልቃወምም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...



በቅርቡ አሜሪካዊው ፕሮፌሠር ዶናልድ ሌቪን ”ኦባማ እና ኢትዮጵያ - ከተስፋ ማጣት ወደ መሪነት” በሚል በእንግሊዝኛ ያቀረቡትን ጽሑፍ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ”እንቢልታ” የተሰኘው ጋዜጣ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ለንባብ አብቅቶታል። ይህንኑ ትርጉም የኢትዮጵያ ዛሬ ታዳሚዎች በሀገራቸው ቋንቋ ቢያነቡት ለግንዛቤ ይረዳቸዋል በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል። 


