የነጻነት ቀን እስትንፋስ
የትነበርክ ታደለ

"ነጻነትን እንደ ዛሬ አይቻት አላውቅም!" አንድ ጋምቢያዊ የተናገረው ነው። 22 ዓመት ሙሉ በውስጡ የተሸከመው መርግ ልክ ረዥም ርቀት በጀርባው ኩንታል ተሸክሞ ማውረጃው ሲደርስ ሸክሙን 'ድብ' አድርጎ ወርውሮ እፎይ እንዲል አዲስ የነጻነት ትንፋሽ እየተነፈሰ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የትነበርክ ታደለ

"ነጻነትን እንደ ዛሬ አይቻት አላውቅም!" አንድ ጋምቢያዊ የተናገረው ነው። 22 ዓመት ሙሉ በውስጡ የተሸከመው መርግ ልክ ረዥም ርቀት በጀርባው ኩንታል ተሸክሞ ማውረጃው ሲደርስ ሸክሙን 'ድብ' አድርጎ ወርውሮ እፎይ እንዲል አዲስ የነጻነት ትንፋሽ እየተነፈሰ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አብርሃም ቀጄላ (ከዋሽንግተን ዲሲ)

በርካታ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶች አሁንም ዛሬ በግዕዝ ፊደል መጠቀም ቀላልና ለሕዝብ ሳይኮሎጂካል፣ ማኅበራዊና ብሔራዊ ማግባባት እንደዚሁም ለመጭው ትውልድ አብሮነት ተወዳዳሪና መተኪያ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑንና፤ ይኼው እንዲፈጸም በበርካታ መረጃዎች እያስደገፉ በማስረዳት ላይ ይገኛሉ። አሁን ላይ ሆነን በዛሬ መስተዋት ያንን የጨለማ ጊዜ ስናየው እንዴት የሚያሳፍር ሁኔታ ውስጥ ማለፋችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5





ተሻለ መንግሥቱ
ከኢትዮሚዲያ ድረገጽ ያገኘሁትን አንድ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ መጣጥፍ ይዤ ሳነብ የንባብ ፍላቴን ማረከውና ዘለቅሁት። በዚያም አልበቃኝም። እዚያው መጣጥፍ ውስጥ በተጠቆመ ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ወደ ኢካድፎረም ድረገጽ አመራሁና በዶክተር ተድላ ወ/ዮሐንስ የተጠቀሰውን የፀጋየ አራ አርሳ ፌስቡካዊ ንግግር የተተቸበትን የራሱን የተድላን ትንሽ ቆየት ያለ የሚመስል ጽሑፍ አነበብኩ ... አነበብኩ እንኳን ሳይሆን በንዴት ተቃጠልኩ ነው ማለት ያለብኝ - ለነገሩ እንዲህ ዓይነት የታሪክና የትውልድ ጭንጋፎች በአነስተኛው የሚፈልጉት እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን በንዴት መንጨርጨር ነው። ወፍ ዘራሾች አዕምሯዊ ሥሪታቸው ወይም የአስተሳሰብ ቀመራቸውና ነገረ ሥራቸው ሁሉ ግራ በመሆኑ የሚያስደስታቸው የሚያሳዝን ነገር ነው። ያን ጽሑፍ ስጨርስ ነው እንግዲህ በመግቢያየ ባስቀመጥኩት ርዕስ የተሰማኝን እንደወረደ ለማስቀመጥ ብዕር ያሳሁት። ይህን ግን ያዙልኝ፡- እንደኢትዮጵያ የተረገመ አገር የለም!!!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ይገረም አለሙ

ለማናቸውም ዓላማ ሰዎች ተሰባስበው ድርጅት የመፍጠር መብት አላቸው፤ በአንጻሩ ለድርጅታቸው የሚሰጡት መጠሪያ እናራምደዋለን የሚሉት ዓላማ እና እንደርስበታለን የሚሉት ግብ በተናጠል ግለሰብንም ሆነ በወል ማኅበረሰብንና አገርን ሊነካ ስለሚችል ከዚህ አንጻር ሊፈጽሙት የሚገባ ግዴት አለባቸው። በመሆኑም በሕገ መንግሥትም ሆነ በፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጆች ውስጥ እነዚህ ከመደራጀት አንጻር ተግባራዊ የሚሆኑ መብቶችና ግዴታዎች ሰፍረው ይገኛሉ። ነገር ግን በፌስ ቡክ ድርጅት ሲመሰረት የመስራቾቹ ቅን ፍላጎትና ራስን ለሕግ የማስገዛት ሰውነት ከሌለ በስተቀር ለሕግም ለሞራልም ግዴታዎች እንዲገዙ የሚገደዱበት ሁኔታ አይኖርም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5





ሸንቁጥ አየለ

፩ኛ- ወያኔዎች ለ25 ዓመታት በየሚዲያው፣ በየመጠጥ ቤቱ፣ በየጓዳቸው እና በየስርቻው የሚለፈልፉት አንድ የምቀኝነት ንግግር አለ። "እኛ ታግለን፣ እኛ ሞተን፤ ለማን ብለን ነው ሥልጣኑን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለተቃዋሚ የምናስረክበው?" የሚል ነው። ይሄም ሲፈታ ምን ማለት ነው? በኛ ደም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ከምትገነባ፤ ኢትዮጵያ በመከራ ለዘመናት እየተሰቃየች ትኑር ማለት ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ገለታው ዘለቀ
በቅርቡ ፋና ብሮድካስት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ “ኢሕአዴግን” የወከሉት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ምክትል ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ጥቂት ለመወያየት ነው የዛሬው አሳቤ። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ እኚህ ሰው የተናገሩት ብዙው ነገር ከተለመደው የተለየ ባይሆንም በተለይ የኢትዮጵያን ፍላጎት በተመለከተ የፓርቲያቸው አመለካከትና ጥናትና ምርምር ምን መሰረታዊ ችግር እንዳለበት መመርመር የዚህን መንግሥት መሰረታዊ ችግሮች እንደገና ለማሳየት ይጠቅማል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...