ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

Eng. Hailu Shawel and Prof. Asrat Woldeyes

ዛሬ ጥቅምት አንድ ቀን 2009 ዓ.ም. ቀትር ላይ በሞት የተለዩንን ኢ/ር ኃይሉ ሻውልን ወደ ዘለዓለማዊው ቤት ለመሸኘት አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተገኝተናል። እዛው የተገናኘን ሰዎች ዝናቡ መቆሚያ ቢያሳጥንም አንድ ጥግ ይዘን አስክሬናቸው እስኪደርስ ወግ ይዘናል። ኢ/ር ኃይሉን ለመጀመሪያ ግዜ ያወቅናቸው በመአህድ ከዚያም በመኢአድ ቀጥሎም በቅንጅት፤ እንደገና ተመልሶ በመኢአድ በመሆኑ ከዚህ እውቀታችን በመነሳት ከፊት ወደ ኋላ እያስታወስን ስናነሳ ስንጥል የመአህድ መስራችና ፕሬዝዳንት የነበሩትንና በእስር ተሰቃይተው በግፍ የሞቱትን ፕ/ር አስራት ወልደየስን አስታወስን። የገደሉንንም የሞቱልንንም እኩል የምንረሳ ምን ጉዶችን በማለትም ራሳችንን ወቀስን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዮፍታሔ

Getachew Ambaye. ጌታቸው አምባዬ

- ችግሩ የተፈጠረው በኦሮሚያ እና ምናልባትም በአማራ ሆኖ እያለ በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ለምን አስፈለገ?

- ኦሮሚያና አማራ ከዚህ ተመሳሳይ በሆነ ወታደራዊ ዕዝ (Martial law) ቆይተዋል። ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ግን አላቆመውም። ይህ ከሆነ ይህን አዋጅ ማወጅ ለምን አስፈለገ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ"!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አብርሃ ደስታ

"ህዝቡ አሁን በአዋጁ ምክንያት የሚያጣው ዴሞክራሲያዊ መብት የለም። ምክንያቱም ከአዋጁ በፊትም ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተነፍጎ ነበረ። የአመጹ መንስኤም የዴሞክራሲ እጦት ነውና"

Abraha Desta

የኢህአዴግ መንግሥት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጇል። በሕገመንግሥቱ መሰረት አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወጣል፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል። በሁለቱም ምክር ቤቶች ልዩነት ስለሌለ መፅደቁ አይቀርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ11ኛው ሰዓት አዋጅ እና ህዝብ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ክንፉ አሰፋ

PM Hailemariam Desalegn

ስለአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የጠየቅኩት አንድ የአዲስ አበባ ወጣት ምላሽ አስገረመኝ። “የምን አዋጅ?” ነበር ያለው።

"ትላንት የታወጀው።"

"አቦ መስሚያችን ጥጥ ነው። ... ሚሰማ የለም" አለኝ።

ኃይለማርያም ደሳለኝ ዝም ብለው ኖሯል የደከሙት!

"ለመኖር ብቸኛው አማራጭ ሌላው እንዲኖር መፍቀድ ነው።" ብለው ነበር የሕንዷ ማህተመ ጋንዲ። እነሱ እየኖሩ ሌላው እንዳይኖር ለሚሹ ራስ ወዳዶች ትልቅ መልዕክት ነበረው። ማስተዋል የተሳናቸው ግን "እኛ ብቻ እንኑር" ይህንን የማይቀበል በሙሉ ይጥፋ የሚለውን ጭፍን አመለካከት እንደ ብቸኛ ምርጫ ይዘውታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አልተገናኝቶም፣ ህዝብ ለነጻነት፤ ፖለቲከኞች ለቤተ መንግሥት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

አልተገናኝቶም

የፖለቲካ ትግል የሥልጣን ትግል መሆኑ እሙን ቢሆንም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን በመታገል በህዝብ ድምጽ ተመርጦ ሥልጣን መያዝን ዓላማ ካላደረጉ የቤተ መንግሥቱ ወንበር የሚሆነው ለአንድ ሰው ብቻ በመሆኑ ትግሉ የመጠላለፍ ጨዋታው የጥሎ ማለፍ ይሆንና ሥልጣን ላይ ያለውን ኃይል ዕድሜ በማራዘም ሁሉም የሚመኙትን ወንበር ሳያገኙ ዘመናት ይቆጠራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሥህተቶችን ሳንደግም የተሻለች ኢትዮጵያን ወደ መገንባት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ገለታው ዘለቀ

በሚመጣው ህዳር ወር ላይ የኢትዮጵያ ልጆች የኦሮሞ ብሔር ልሂቃን ተሰብስበው በከፍተኛ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ሲባል ምክክሩን ወድጄው በስብሰባው ላይ ቢነሳ ጥሩ ነበር ብየ ባሰብኩት ላይ ለመወያየት ነው አነሳሴ። የውይይቱ አሳብ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው በርግጥ። እነዚህ የኦሮሞ ወገኖቼ ከዚህ ስብሰባ በሁዋላ የሚያወጡት የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያን ማኅበረ ፖለቲካ ለመለወጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የትብብር፣ የአንድነት አሳብ እንደሚሆን አምናለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ