የፈጣሪና የህዝብ ዓይኖች በናንተ ላይ ናቸው!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ዮፍታሔ

GODs eye

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃችኋል።

በግልጽ አፋኝ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸምና ዝርዝር ደንብም አውጥታችኋል።

ከዚህ ቀደም ሁሉን አድራጊው ራሱ ያልሆነ ይመስል፤ "ኮማንድ ፖስቱ የሀገር መከላከያ ኃይል፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልል መንግሥታት ልዩ ኃይሎችን ያካተተ" መሆኑንም በመግለጽ አላግጣችኋል።

እንዲህም ሆኖ የራሳችሁን ሕገ-መንግሥት ታከብሩ ከሆነ ሌላ የሚቀራችሁ ነገር አለ። እንደማይጠቅም ብናውቅም በሰነድ ይይዘው ዘንድ ህዝቡ ይከታተላችኋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"አንድ ኢትዮጵያ! አንድ ሀገር! አንድ ህዝብ!" ምን ማለት ነው?

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ሸንቁጥ አየለ

Out of Many WE are ONE!

ኢትዮጵያ በምልዓት ድና እና ተፈውሳ ማዬት የምትፈልጉ ኃይላት "አንድ ኢትዮጵያ! አንድ ሀገር! አንድ ህዝብ!" የሚለውን የአስተሳሰብ አድማስ እንዳትለቁ። ለነገሩ ይሄ አስተሳሰብ ከተሸነፈ ቆዬ። የፀረ-ኢትዮጵያዊነት ኃይላት በመጀመሪያ ወደ ምድር ከስክሰው በእግራቸው የረገጡት እና ያስረገጡት ይሄን አስተሳሰብ ሐሰት ነው በማለት ነው። የአንድን ወገን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚነፋ ፕሮፖጋንዳ ነው በሚል ሐሰተኛ ቀመር ተነስተው ነው ውድቅ ያደረጉት። የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አንድነት የለውም ብለው ተነስተው ይሄው ዛሬ ሀገሪቱን የህልውናዋ ማክተሚያ ወደ ሆነ አፋፍ ላይ ገፍተዋት ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ጥለዋታል። ከዛሬው ትርምስ ይልቅ የነገው ትርምስምስ ይበልጥ አሳሳቢ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም! መወገድ ያለበት እንጂ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

“በገሃነም ውስጥ እጅግ የሚያቃጥለው ቦታ የተያዘላቸው፤ የሞራል ቀውስ በሚታይበት ወቅት ለህዝብ ወገናዊነትን ለማያሳዩ ሰዎች ነው።” Dante

Bereket Simon

መግቢያ

ሰሞኑን ወያኔ የሚያወናብደው ራሱን ለማደስ እንደተዘጋጀና ጊዜም እንደሚያስፈልገው ነው። በአገዛዙ ውስጥ የአስተዳደር ብልሹነት አለ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ባህል ተስፋፍቷል፣ ሙስና ለቢሮክራሲው ማነቆ በመሆን ሥራ አላሠራም በማለት የሀገርን ዕድገት እየጎተተ እንደሆነ እየመላለሰ ይነግረናል። እነዚህንና ሌሎች የአስተዳደር ብልሹዎችን በየስብሰባውና በቴሌቪዥን “የውይይት መድረከ” ላይ የሚያወሩልን የአገዛዙ የመሪ ቁንጮዎች በሽታዎቹ ከሰማይ እንደወረዱ እንጂ እነሱ ለአጋዛዛቸው እንዲያመቻቸው ሆን ብለው የፈጠሩትና ከተበላሸ ኢ-ሳይንሳዊና ሀገር አፍራሽ የአሠራር ዘዴ ጋር እንደተያያዘ አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የለውጥ ኃይሎች” ግልፅና ደፋር ውይይት ለመፍትሔና የጋራ ድል (ኤርሚያስ ለገሰ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Ermias Legesseለህዝብ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ (ቺካጎ/ኢሊኖይ)

ኤርሚያስ ለገሰ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ራዲዮ(ኢሳት)

ጥቅምት/2016

ማስታወሻ

*ይህ ጽሁፍ ከራሴ ውጭ የምሰራበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬዲዮ (ኢሳት)ን ጨምሮ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም።

**"የአዲስ አበባ ነዋሪ" ("አዲስ አበቤ") የሚለው ቃል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሆኖ በአዲስ አበባ የሚኖር አሊያም ለወደፊት የመኖሪያውን አዲስ አበባ ለማድረግ የፈለገን በሙሉ የሚያጠቃልል ነው።

መንደርደሪያ

የዛሬ ሦስት ወራት አካባቢ ከኦሮሞ አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ ጋር በኢሳት ስቱዲዮ ለአጭር ሰዓታት ኢ-መደበኛ ወግ ጠርቀን ነበር። ገረሱ በወጋችን መሀል “ለጋራ መፍትሔ ግልፅና ደፋር ውይይት የማድረጊያው ሰዓት አሁን ነው” በማለት ይናገር ነበር። መልሶ መላልሶም “የጋራ ችግር አለብን፤ ያልተነጋገርናቸው እና በይደር ያቆየናቸው ድፍረት የሚጠይቁ አጀንዳዎች ከፊታችን ተቆልለዋል። በግልፅና በሐቅ ተወያይተን መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል” እያለ የቀጣይ ስጋቱን ይዘረዝር ነበር። የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገንም ጭምር። የነገንም ብቻ ሳይሆን የተነገወዲያውም። ለልጅና ልጅ ልጆቻችን!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጃዋር ቻርተር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

Jawar Mohammed

መንደርደሪያ

ጃዋር የኦሮምያን ቻርተር እያዘጋጀን ነው በማለት የተናገረው ዋንኛ የመነጋገሪያ ብቻ ሳይሆን፤ የመነታረኪያም ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል። ከሚያግባባን ይልቅ በሚያለያየን ላይ ጎራ ለይቶ የመነታረካችን አንዱና ዋናው ጉዳይ ወይ ከዚህ ወይ ከዛ የሚለው መሃል ላይ ቦታ የሌለው ወይንም የማይሰጠው ፖለቲካችን ነው። ሁለተኛው ችግራችን ደግሞ ድጋፋችን ነፋስ አይንካህ የሚል ነቀፌታችን መልካም ጎኖችን የማይመለከት መሆኑ ነው። ይሄ በፍጹም አይበጅም የምንወደውንና የምናደንቀውን ልንተቸውም ሆነ ልንመክረው፤ የማንወደውንና የማንደግፈውን ደግሞ ብዙ ስንነቅፈው ለበጎ ሥራው በትንሹም ቢሆን ጎሽ ልንለው ይገባል። ነቀፌታም ሆነ ትችታችን ወደ መሃል የሚጎትት እንጂ ወደ ዳር የሚገፋ መሆን የለበትም፤ ከስህተት ለመማር ከጥፋትም ለመቆጠብ የሚያበረታታ እንጂ፤ ጥላቻን የሚያስፋፋና እልህ ውስጥ የሚያገባ መሆን አይኖርበትም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፌስቡክን እንደምክንያት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ኃብተወልድ ተሾመ

Facebook banned in Ethiopiaሀገሬ ይህን ጊዜ ባታይ እመርጥ ነበር፤ ከ54 የአፍሪካ ሀገራት በህዝብ ብዛት ናይጄሪያን ቀጥላ በሁለተኝነት የምትቀመጠው ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ባለፉት ሩብ ክፍለ ዘመን ዕይታ የማታውቀው አይነት ነው። በየቦታው በየአካባቢው ወጣቶች ይታሰራሉ፤ ወጣቶች ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ይፈጸምባቸዋል፤ ባስ ሲልም አንዲት ሕይወታቸውን የሚያጡበት ጠያቂ የበዛበት መልስ የሌለበት ዘመን ላይ ደርሰናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ