የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

TPLFተሻለ መንግሥቱ

በብሂለ ግዕዝ “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” ይባላል። አንዳንድ ነገሮችን በአፍ ወለምታም ይሁን በቴሌፓቲክ የነገሮች አፈጻጸም ሂደት ቀድመው ይጠቀሳሉ። መለስ ዜናዊ ስለአክሱም ሐውልት የይገባኛል ጥያቄና የባለቤትነት ይዞታ ሲናገር መረንን በማያውቀው ስድ አንደበቱ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ከፋፋይ ሃሳብ በገሃድ ተናግሯል። ለነገሩ መለስ ያልተናገረው ጠያፍ ነገር የለም። የአንዲት ሀገር መሪ ሆኖ ራሱን ሾሞ ሲያበቃ ሌሎችን እንደጨርቅ እርሱ የወጣትበን ጎሣ ግን እንደወርቅ መመሰሉን በአደባባይ ገልጾ እርሱና እርሱን መሰሎች ሀፍረትን ባያውቁም እኛ ስለነሱ አፍረናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዩንቨርስቲዎቻችን እባካችሁን አታሳፍሩን!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ታረቀኝ ሙጬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

“ልፋ ያለው በልሙ ዳውላ ሲሸከም ያድራል” እንዲሉ ሆኖብን ሰሚና አድማጭ ያለ እየመሰለን የምንጮህ ብዙዎች ነን። ግን ያው እነመምሩ “ነባይ ነባይነ ከምዘይባይነ ኮነ” (ጮህን፣ ጮህን ግና እንዳልጮህን ተቆጠርን (ሰሚ አጣን)” እንዳሉት ዘመናችን የጥንቶቹ ባቢሎናውያን ዓይነት የመደነቋቆሪያ ጊዜ ሆነና እንዲሁ በከንቱ እንደቁራ እንጮሃለን። ቢሆንም ካለመጮኽ መጮኽ ይሻላል - ዝምታም አንዳንዴ ከሞት አንድ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከአብርሃም ደስታ እስከ ሀብታሙ አያሌው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Habtamu Ayalewነቢዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ ... የሀገሬ ዲሞክራሲያዊ የበቀል ፖለቲካ

የሰሜኑ ኮከብ አብርሃ ደስታ እንኳንም ተፈታህ!

የሰሜኑ ኮከብ ወንድም አብርሃም ደስታ ከእስር እንደሚፈታ ቢገመትም ዘንድሮ ሲሆን እንጅ ሲባል ለማመን ተቸግሬያለሁና ዛሬን መቆየት ነበረብኝ ። እናማ የሰሜኑ ኮከብ ደፋሩና ለእውነት ግንባሩን የማያጥፈው የመቀሌው አብርሃም ደስታ "እውነት ተፈታ" ሲባል ሰማሁ፣ ደስ አለኝ! አብርሽ፤ እንኳንም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ አዝማድና ወዳጅ አፍቃሪ ወገንህ ጋር ተቀላቀልክ እልሃለሁ፣ አብርሽ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ባበደች ሀገር ውስጥ መኖር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ምሕረቱ ዘገዬ

ወዳጅን ቢከፋውም ጠላት ግን ደስ ይበለው - ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ለይቶላት ጨርቋን ጥላ ዐብዳለች። ዕብደት እንዴት ይገለጻል? የሀገርና የሕዝብ ዕብደት እንደኔ አስተሳሰብ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊገለጽ ቢችል የሚያስማማ ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከዐውሬ ጋር ትግል

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ነፃነት ዘለቀ

ትግል ከሰው ጋር እንጂ ከዐውሬ ጋር ከሆነ አደገኛ ነው። ህወሓት ከጥንስሱ ጀምሮ መቼም ቢሆን በሰዎች ተመርቶ አያውቅም። ይህ ድርጅት ከመነሻው በሰው መሰል አራዊት እንደሚመራ የታወቀ ሆኖ ሳለ ከእባብ ዕንቁላል ዕርግብ ይፈለፈል ይመስል ከዚህ ቡድን መልካም ነገርን የሚጠብቁ ሞኛ ሞኝ ፍጡራን ሲስተዋሉ የሚገርም ነው። እነዚህ የህወሓት ሰዎች የራሳቸው ጠባብ የአስተሳሰብ አድማስ ከፈጠረላቸው የትግሬ ዘር ውጪ ሌላውን ሰው በሰውነት ሊቀበሉ አይፈልጉም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከእንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣት የምንማረው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አንዱዓለም ተፈራ

Brexit የእንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣት

የዓለም የንዋይ ስምሪት አውታር ክንፎች አጥናፋቸውን ሲያሰፉ፣ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ቁልልፍ እየተወሳሰበ ሲሄድ፤ ግለሰቦች ከራሳቸው ከባቢ ውጪ ያለውን ክንውን፤ በንቃት መከታተል ግድ ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም በዚህ በተወጠረ የዓለም ትስስር ሕልውና፣ አንዱ አካባቢ የሚነጥረው ጠጠር ሌላውን አካባቢ ያረግባልና! ለዚህ ነው ከኢትዮጵያ በስደት አሜሪካ ተቀምጬ፤ አውሮፓ የሚካሄደውን የእንግሊዝ ከአውሮፓ ኀብረት መውጣት በንቃት የተከታተልኩት። እናም እነሆ ግንዛቤዬ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ