የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማለት የሕወሓት የበላይነት ማለት ነው
ብርሃኑ ጉተማ ባልቻ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቋረጠ ትግልና በኢሕአዴግ ምክር ቤት ውስጥ የኦሕዴድንና የብአዴንን ሙሉ ድጋፍና ከደኢሕዴንም የተወሰነ ድጋፍ በማግኘት ጠ/ሚ ለመሆን ችለዋል። የሊቀመንበርነቱ ምርጫ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቢሆን ኖሮ ዐቢይ ጠ/ሚ ለመሆን አይችሉም ነበር። ምክንያቱም የሕወሓት የበላይነት በኢሕአዴግ ምክር ቤት ውስጥ እየተወገደ ቢሆንም፤ በተቃራኒው ግን የሕወሓት የበላይነት በኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ውስጥ እንደቀጠለ ነው። የሕወሓትን የፖለቲካ አቅም ለመገንዘብ እነዚህን የኢሕአዴግ ሁለት ቁልፍ የፖለቲካ መዋቅሮች ማለትም የኢሕአዴግ ምክር ቤትንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴን በሚገባ መረዳት ይገባል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...