ለ’ፋታ’ ንፉግ የሆነው ፖለቲካችን

አብርሃም አየለ
የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5
አብርሃም አየለ
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
አምባቸው ደጀኔ
አገራችን በየቀኑ መነጋገሪያ አጀንዳ አታጣም - በተለይ በዚህ ዘመንና በጣም በተለይ ደግሞ ባለፉት 12 ወራት። በነዚህ ሁለት ቀናት ደግሞ “አትርሱኝ” እያለ ያለው በቀለ ገርባ ነው።
ላለመረሳትና በሕዝብ አንደበት ዘወትር ለመወሳት እኮ በግድ ክፉና ጠማማ መሆን አያስፈልግም። ሰዎች እንዴት ነው እያሰቡ ያሉት? እንዴትስ ነው ያድጋሉ ሲባሉ እያነሱና እየኮሰመኑ የሚሄዱት? ምን ቢነካቸው ነው? አንድ ሰው ዕውቀትንና ጥበብን መጨመር ቢያቅተው ያለውን ይዞ መጓዝ እንዴት ይሳነዋል?
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ግርማ በላይ
አጤ ምኒልክ ከልምድዎ፤
አንዳንድ እያለ ቀረልዎ፤
አምናስ አለማያ ነበሩ፤
ዘንድሮን ወዴት ዋሉ?
ግንቦት ሰባት ከልምድህ፤
አንዳንድ እያለ ቀረልህ፤
አምናስ አሥመራ ነበርክ፤
ዘንድሮን ወዴት ዋልክ?
የኢትዮጵያ ሾተላይ ግዳይ መጣሉን ቀጥሏል። ልጆቿን ለሆነ ዓላማ ያሰባስባል፤ ከዚያም ቁም ነገር ሊያከናውኑ ሲሉ አንዳች ነገር ብን ያደርግባቸውና እያባላ ይበትናቸዋል - ደብተራዎች “አንደርብ” እንደሚሉት ዐይነት ነገር። አገሪቱ የሰብስብ ሣይሆን የበትን አለባት። ኢትዮጵያ ከምትወልዳቸው ልጆቿ ሙሉ በሙሉ ሳታያቸው በባህሉ መሠረት የጥቂቶቻችንን ጆሮ ቀንጠብ አድርገው ሰጥተዋት ካልበላችና የልጇን ጆሮ መብላቷን ነግረው ካላስደነገጧት በስተቀር የሾተላይ ዛሯ እንደ አገር የመቀጠሏን እድል እያጫጫው ነው። አሁንማ ሁሉ ነገር ኳስ አበደች ሆኗል። መንግሥት የለ፤ ሕዝብ የለ። ኦና ብቻ! ኦና አገር። ንብ-አልባ ቀፎ ሆነናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ምሕረቱ ዘገዬ
ሁሉም ሰው በግልጽ የሚረዳው በሕክምናው ዓለም የሚተገበር አንድ አሠራር አለ። ይሄውም በአንድ ሕመም ውጫዊ የስቃይ ምልክቶችና ውጤታቸው ላይ ብቻ ከማተኮርና፤ የሕመም ስሜቶችን ብቻ እየተከታተሉ ስቃይን በማስታገሻ መድኃኒቶች ለተወሰነ ጊዜ ፋታ ከመስጠት በተጓዳኝ፤ የበሽታውን መንሥኤ ማጥናትና ሕመሙን ከሥር መሠረቱ አክሞ መፈወስ ተመራጭ የመሆኑ እውነታ ነው። ይህ አሠራር በጤናው ዘርፍ ብቻ የሚወሰን አይደለም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
ዘ-ጌርሳም
ገና ስምንት ወር ብቻ ነው - ሕፃናት ተወልደው ቁመው የማይሄዱበት ዕድሜ፤ ከድምፅ በቀር ቃላት እንኳን አያወጡም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ተጭኖት ከነበረው የመከራና የግፍ አገዛዝ ቀንበር ራሱን ነፃ ለማድረግ፤ መራራና ፈታኝ መስዋእትነት ከፍሎ ለውጡን ለሚመሩለት ኃይሎች አስረክቧል። ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት በየቀኑ የሚያሳያቸውንና የሚያስመዘግባቸውን ለውጦች በአንክሮ ለሚከታተል ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኝ ሆኖ ጥራቱና ፍጥነቱ ደግሞ የበለጠ ያስደምማል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...