አገራዊ የጸሎትና ምህላ ጥሪ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
ጸሎት

ምሕረት ዘገዬ

የአገራችን ጉዳይ ከድጥ ወደ ማጥም አልፎ ልንገልጸው ቃል ያጣንለት የመቅሰፍቶች ሁሉ ትንግርታዊ ትዕይንት ሆኖኣል። አንዱ ቀን አልፎ ሌላው ሲተካ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት ሄዶ ዜጎች በቋሚነት ወላፈኑ በማይበርድ ምድጃ ላይ ተጥደው እንዲቃጠሉ ተፈርዶባቸዋል። በዚህም ምክንያት የምናደርገው ጠፍቶን ብዙዎቻችን በአገራችን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ላይ ክፉኛ ተጨንቀን ተጠበናል። የዚህች ታሪካዊ አገር መጥፋት የሚያስደስታቸው ካልሆነ በስተቀር ጤናማ ለሆነ የዓለም ዜጋ ለኛ ለኢትዮጵያውያን የተደገሰልን መከራ እጅግ ዘግናኝ ነው። በዚህን ወቅት አገር አማን ብሎ የሚተኛ፤ ከዚያም ባለፈ በእህል ውኃ ስካርና ጥጋብ ጮቤ የሚረግጥ ካለ ዓለም ብታልፍ የማያሳስበው ግዴለሽ እንጂ የሚያስብ አንጎል ባለቤት የሆነ ጤናማ ሰው አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጽንፈኛ ብሔርተኝነት መዘዝ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ይለምልም!

በቀለ ደገፋ (ከኦስሎ)

ከሁለት ዓመት በፊት በኢሕአዴግና በተቃዋሚ ቡድኖች መካከል ሲደረጉ የነበሩ ክርክሮች ከሞላ ጎደል በዴሞክራሲ፣ ፍትሕና ልማት ዙሪያ ያጠነጠኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን ፖለቲካችን መጀመሪያውም መጨረሻውም የማንነት ፖለቲካ ሆኗል። እንደዚህ ዐይነት የፖለቲካ አካሄድ ከ40 ዓመት በፊት ማርክሲዝምን እንደ ሃይማኖት በተቀበሉ ተማሪዎች የተጀመረና በገዥው ፓርቲም እንደ ብቸኛ ማደራጃና ማታገያ መንገድ የተያዘ ከመሆኑ አንጻር፤ አሁን ያለንበት ቀውስ ብዙዎችን አያስገርምም። ምናልባትም እንደ ትንቢት እያንዳንዱ ነገር ከታቀደለት ጊዜ ሁሉ ቀድሞ እየተደረገ ያለ ነው የሚመስለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ግዛቸው ሺፈራውና ሀብታሙ አያሌው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
አቶ ሀብታሙ አያሌውና ኢንጂንየር ግዛቸው ሺፈራውና (ፎቶ ቅንብር ኢዛ)

ይገረም አለሙ 

በቅድሚያ ኢንጂንየር ግዛቸው አለማለቴ፤ መጠሪያ አይደለም ከሚል እምነት የዘለለ ምክንያት እንደሌለው ይታወቅልኝ።

ለዚህ ጽሑፍ አብይ መነሻ ምክንያቱ “የሀብታሙ አያሌው ቅጥፈትና የባዶ ቅል መንኳኳት” የሚለው የአቶ ግዛቸው ጽሑፍ ነው። የሀብታሙ አያሌውን መጽሐፍ አላገኘሁትም። በአቶ ግዛቸው ጽሑፉ እንደተገለጸው የአቶ ሀብታሙ መጽሐፍ እንዲህ ከእውነት ይልቅ በስሜት ከማስረጃ ይልቅ በጥላቻ የተሞላ ከሆነ አለማግኘቴን እሰየው እላለሁ። ምክንያትም ምላሽ በመስጠት ያደክመኝ ነበርና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲያልቅ አያምር፤ “የሥርዓቱን አሟሟት ያሳምርልን!”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Ethiopian PM Hailemariam Desalegn

ያሬድ ኃይለማርያም (ከብራስልስ)

የዛሬ ሦስት ዓመት ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ›ም “ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ፤ የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ.ምሳሌ ም.22፣ ቁ.14)” በሚል አርዕስት ለንባብ ባበቃሁትና በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በገመገምኩበት ጽሁፍ ይህን ከትቤ ነበር፤ “አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ስር ሊቆይ ይችል። ይሁንና ዕድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም። ሥርዓቱም እንደ ድርጅት፣ ሹማምንቱም እንደ ሰው የጉብዝና ዕድሜያቸው የተወሰነ ነው። የአፈናን ስልት በመለዋወጥና ሸምቀቆውን በማጥበቅም ዕድሜን ማራዘም የሚቻል ቢመስልም በተቃራኒዉ ውድቀትንም ያፋጥናል። ግፉ እየበረታና የመብት ጥሰቱም መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር የሕዝብ ትእግስት ይሟጠጣል። ሕዝብ መቆጣት ከጀመረና ቁጣውም ወደ አደባባይ አመጽ በተቀየረ ጊዜ የግፍ አገዛዝ ወደ መቃብር፣ ግፈኞቹም ወደ ዘብጥያ እንደሚወርዱ እርቀን ሳንሄድ ባለፉት አምስትና አሥርት ዓመታት ውስጥ በአለም የታዩ ሕዝባዊ ነውጦችንና ያስከተሉትን መዘዝ ማጤን በቂ ነው።” የዚህ ጽሁፍ አላማም የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግ ቀን ይመጣል እያለ አምቆ የያዘው ብሶትና ክፌት ሊፈነዳ ጥቂት ስለቀረው ሥርዓቱ በጊዜ እራሱን ያርቅ፤ ካልሆነ ግን የማይቀረው አመጽ ይነሳል። የሥርዓቱም ፍጻሜ እንዳያምር ይሆናል። የሚል ማሳሰቢያ ጭምር ነበር። ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነገሮች እያፈጠጡ መጡ። ይህን ጽሁፍ ምሉውን ለማንበብ ከዚህ ገጽ ሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።[1]

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተቃዋሚ ጎራው ”የወያኔ መውደቂያ ደረሰ” የሚለው ወቅታዊ አጀንዳ መሰረቱ ምን ይሆን?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
The End of TPLF

ሸንቁጥ አየለ

”ይሄን ያህል ጄነራል፣ ይሄን ያህል ልብስ አልባሽ፣ ይሄን ያህል ሹም ከዳ፤ እናም ወያኔ ሊወድቅ ነው” እያለ ወቅታዊ አጀንዳውን ያራግበዋል። ጥያቄው ከማን ወገን ነው የከዳው። ሃያ ስድስት ዓመታት ሙሉ ከወያኔ/ሕወሓት ፓርቲ ወይም ጄነራሎች ውስጥ አንድም ኀይል ከድቶ አያውቅም። የወያኔ የሥልጣን ነብስ፣ ልብ፣ አዕምሮ እና ስሜቱ ደግሞ ሕወሓት እና ሕወሓት ብቻ ነው። ለበርካታ ዓመታት እንቶኔ ከዳ፣ እንቶኔ ለቀቀ ሲባል የሕወሓት ጄነራሎች ውስኪያቸውን እያንጫለጡ ይስቃሉ። የሕወሓት ፖለቲከኞችም የተቃዋሚው ሚድያ የሚያርገበግባቸው ሚስጥር የሚመስሉ ነገሮችን አውቀ ይለቃሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባዱላ ገመዳ የእኛ አጀንዳ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

Abadula Gemeda
አባዱላ ገመዳ

አምና በዚህን ሰዓት፣ ልክ አንደ ሰሞኑ ፓርላማው ሲከፈት ፕሬዝዳንት ሙላቱ አንብቡ ተብሎ የሚሰጣቸውን ይዘው፣ ከፓርላማ ተገኝተው የምርጫ ሕጉን እስከ መሻሻል ሄደን ከተቀዋሚዎች ጋር አብረን እንሰራለን አሉ። ተቃውሞአችው እንደ ዥዋዥዌ ጨዋታ የሆነው አንዳንዶች በዚህ ንግግር ተመስጠው እውነት አደርገውም ወስደው ወያኔ ከመቅጽበት የተፈጥሮ ባህሪውን ይለወጥ ይመሰል አምነውት ሊያሳምኑን ባይሳካላቸውም ትንሽ መንገድ ተንገዳገዱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ