አማርኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ዮፍታሔ

Amharic Language
አማርኛ ቋንቋና ፊደል

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ገና ምኑም አልተነካም። አብዛኛው ተቃጥሏል፣ ወድሟል። ከዚህ የተረፈው ተዘርፏል።

በውጭ ሰዎች የተዘረፈው በየቦታው አለ። ነገር ግን ተተርጉሞና ለምርምር አመቺ በሆነ መንገድ ጸሐፍትና ተመራማሪዎች እንዲደርሱበት ሆኖ ለአገልግሎት አልቀረበም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሽሽት እና የአባዱላ ገመዳ ነገር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክንፉ አሰፋ

Abadula Gemeda
አባዱላ ገመዳ

ከሰሜን እና ከበስተ-ምስራቅ አቅጣጫ እየነፈሰ ያለው አውሎንፋስ መርከብዋን እያናጋት ይገኛል። ጫፍ ላይ ጉብ ያሉትን አስተናጋጆች እያንጠባጠበ የሚገፋው ኀይል እየበረታ መጥቶ፣ አሁን ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ይህ ሁላችንንም የሚያስማማን መራራ ሐቅ ነው። ችግሩ እዚህ ላይ አይደለም። ግን ... እየሰመጠ ካለው ከዚህ መርከብ ለማምለጥ የተገኘችውን ቀዳዳ እየተጠቀሙ የሚሾልኩትን ሁሉ "ጀግና" ብለን ለመጥራት እንደምን ይዳዳን?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“አይትቅትሎ አይትህድኖ” - መምርሂ ሻዕቢያ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ በላይ

Ethiopia and Eritrea
ኤርትዮጵያ

ግዕዝ/ትግርኛ ለማይረዱ አንባቢዎች ርዕሴን ግልጽ ላድርግ። ርዕሴ በቁሙ ወደ አማርኛ ሲተረጎም፤ “‹አትግደለው አታድነው› - የሻዕቢያ መመሪያ” የሚል ፍቺ ይሰጣል።

ሰሞኑን ከአንድ ትግራዋይና ከአንድ በቀድሞ አጠራር የኤርትራ ክፍለ አገር ተወላጅ ጋር የሞቀ ጭውውት ይዘን ነበር። የልብ ጓደኝነት ያህል በጣም ስለምንግባባ የሆድ የሆዳችንን ነበር የምንጫወተው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ሶሺዮ ፖለቲካ ጉዞ፣ ተግዳሮቶቹና የመፍትሄ ሃሳብ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ገለታው ዘለቀ

የኢትዮጵያ ሶሺዮ ፖለቲካ ጉዞ
የኢትዮጵያ ሶሺዮ ፖለቲካ ጉዞ፤ ወዴት እንሂድ!?

ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባት ምቹ የሆነ የሶሺዩ ፖለቲካ ሥርዓት ወደ መፍጠር

(ለአራተኛው የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንፈረንስ የቀረበ ጽሁፍ)

የሰው ልጅ ማኅበራዊና ግላዊ ተፈጥሮ ስላለው ለማኅበራዊ ኑሮውና ለግላዊ ኑሮው የተለያዩ ጠገጎችን እያበጀ ይኖራል። እነዚህ የሚሰራቸው ጠገጎች ለግል ሕይወቱም ሆነ ለማኅበራዊ ሕይወቱ ወሳኝ ናቸው። ሰው የዚህን ዓለም ኑሮውን ለመግፋት ከሚያስችሉት መሳሪያዎች አንዱ እነዚህ ጠገጎቹ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

H.Res 128 በአሜሪካ እንደራሴ ከጸደቀ በሽብር ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር አልተባበርም ማለት ምን አንድምታ አለው?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ገለታው ዘለቀ

Dream of ISIS
የአይሲስ (IS) ሕልም

የተከበሩና የዘወትር የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገር የሚቆጫቸው እንደራሴ ስሚዝ ክሪስ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ትግል ለመደገፍ ሲሉ H.Res 128 ሕግን አርቅቀዋል። ይህ ሕግ በውጭ ጉዳይ በንዑስ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ ጸድቆ ወደ ዋናው ምክር ቤት ለድምጽ ውሳኔ በመሄድ ላይ ነው። ባለፈው ኦክቶበር ሁለት ለሕዝብ ተወካዮች ለድምጽ ይቀርባል ተብሎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይሁን እንጂ እንደተራዘመ ተገልጻል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክህደትና ድጋፍ መንሳት - የፖለቲከኞች መሰሪ ስልት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

ተዋከበና

ወዲህ ዘወር ቢል ሰው የለምና

ገብርዬ ሲሞት ቀኙ ዛለና

አረሩን ስቦ ጠጣው ያ ጀግና

ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን አያሌ ዓመታትን ወደ ኋላ በምናብ ተጉዞ ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ የዘፈነው ዘፈን መቅደላ በዓይነ ህሊናችን እንድናይ የማድረግ አቅም አለው። በምስል የምናውቀው ሽጉጥ የጎረሰው ቴዎድሮስ ፈጥኖ ከህሊና ድቅን ይላል። እንዲህ በትውስታ የቴዎድሮስን ምስል እያየሁ በስሜት አንድነት አጥተን በወያኔ በባርነት የመገዛታችን ቁጭት እያንገበገበኝ ከግጥሞቹ መካከል ወዲህ ዘወር ሲል ሰው የለምና የምትለዋ ደግሞ ከመቅጽበት 16 ዓመታት ወደ ኋላ አንደርድራ 2001 ዓ.ም. ላይ ትወስደኝና ሌላ ትውስታ፣ ሌላ ቁጭት፣ ሌላ ወይ ነዶ ውስጥ እያስገባችኝ ተቸግሬአለሁ። ዝግባ የሚያሳቅፍን አንድ ፍቅር አጥተን ሲልማ፣ ምን ብዬ ልግለጸው። ዘፈኑን ማዳማጥ ማቆም ሳይኖርብኝ አይቀርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ