ቅምሻ ጨዋታ “ሞተዋል እንዳልል ቀብርዎን አላየሁ፤ አሉም እንዳልልዎ ድምፅዎን አልሰማሁ …”

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  PM Meles Zenawiአቤ ቶኪቻው

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምን ውስጥ እንደገቡ እስከ አሁንም የጠራ ወሬ አልሰማንም። በምትኩ የተምታታ ዜና እያዳመጥን ነው። ቅዳሜ እለት ለህትመት የበቃው እንግሊዘኛው “ፎርቹን” ጋዜጣ መለስ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አስመልክቶ ፊት ለፊት ገፁ ላይ አስነብበቦን ነበር። ዛሬ ደግሞ ሪፖርተር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጪ ሃገር በእረፍት ላይ ናቸው ብሎ ዘግቦልናል። ነገሩን ልብ ብለን ስናየው ዘጋቢዎቻችንም እየዘገቡልን ሳይሆን እያወዛገቡን ነው የሚመስለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ አልጋ ወራሾች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Meles Zenawi መለስ ዜናዊ ተስፋዬ ገብረአብ

“መለስ ታመመ” የሚለውን ወሬ ተከትሎ፣ ኮማ ውስጥ መግባቱና መሞቱ እየተነገረ ሰንብቶአል። የወያኔ መንግስት ግን ወሬውን አፍኖ ለመቆየት ተጨናነቀ። መለስ ጀርመን ሃገር ላይ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉ በአንድ ወገን ሲገለፅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤልጅየም 10 ቀናት አልጋ ይዞ መሰንበቱ ተሰምቶአል። “አዲሳባ ገባ” የሚለው ተሰምቶ ሳያበቃ፣ “ብራስልስ ላይ መሆኑ ተረጋገጠ” ተባለ። ወሬዎቹ መልከ ብዙና ውል አልባ ነበሩ። ዞረም ቀረ መለስ ታሞአል። ከመለስ መታመም ጋር በተያያዘ እንዲሞትም ሆነ እንዲፈወስ የሚፀልዩ ተደምጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያለ ጨረታ! ለነ ሌንጮ ለታ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

እንግዳ - ከኦስሎ

መቸም! ተስፋዬ ገብረአብ በጥሩ ብዕሩ እያዋዛ በሚለቃቸው መጣጥፎቹ ውስጥ በየመስመሮቹ መሃል ወሸቅ የሚያደርጋቸው አፋጀሽኝ ቃላቶቹ አሁንም አልለቀቁትም። ”ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” ሆነና አድባር ስትከፍትለ’ት በሚለቃቸው መጣጥፎቹ መስመሮች ውስጥ - በአብዛኛው በአማራና - ኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ንትርክ እንዲቀጥል ሲፈልግ፣ ዛሬ ደግሞ ሴሜቲኮችና ኩሺትኮች በሚላቸው ኢትዮጵያውያን መሃል ሽኩቻው እንዳያባራ - የአበሻን - ተንኮል አሳምረው ሌንጮና ዲማ ያውቁታል በሚል ጥርጣሬው እንዲጠጥር በር ይከፍታል። ይህች አንጓ አስታራቂ ናት ወይስ ቀጣይ ጥርጣሬን ጫሪ? ደራሲ ተስፋዬ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሥራት አንለይ ትዝታዬና መጽሐፉ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አሥራት አንለይወለላዬ (ከስዊድን) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

... እራሱን የሚገል እራሱን የሚያድን

እራሱን የሚያስጠላ፤ እራሱን የሚሆን።

እኮ በሉ ጎበዝ! ይኸን ሰው እወቁት፤

ሲፈልግ የሚኖር፤ ሲፈልግ የሚሞት፤ ...

አሥራት ለአሥራት

ትምህርት ቤት ለሁለት ወራት ሲዘጋ ለደብተር መግዣ የሚሆነኝ ገንዘብ የማገኝበት ስራ የሚያስቀጥሩኝ ዘመዶች ነበሩኝ። ሁለት ወይም ሦስት ክረምቶች ሰርቻለሁ። በኋላ እንደተረዳሁት ስራው በክረምቱ ወራት እንዳልወሰልት መቆጣጠሪያ ጭምር እንደነበር ልረዳ ችያለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊቷን የገደሉ ሶስት የመናዊያን ፍ/ቤት በነፃ ለቀቃቸው … አል-ወሳይቂያ ጋዜጣ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሀበሻ በየመን

ሀረድ ካምፕ ውስጥ ያሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተላላፊ በሽታ ተጠቅተዋል … የመን ታይምስ ጋዜጣ

ልጄን ማዳን እፈልጋለሁ እርዱኝ … ልጇ የታመመባት እናት

በየመን 14,000 ኢትዮጵያዊያን ችግር ውስጥ ገብተዋል … የየመን ሬድዮ

ግሩም ተ/ኃይማኖት

ሰሞኑን የታተመ አንድ ”አል-ወሳይቂያ” የተባለ ጋዜጣ በአንዲት ኢትዮጵያዊት ላይ የተደረገ ግድያን ምስጢር አጋልጧል። ”እስከሞት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን በሰነዓ” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ምንጩ የየመን ሁማን ራይት ሚኒስቴር እንደሆነ ጠቅሶ ዘገባውን ለንባብ ያበቃውን ጋዜጣ ትርጉም እነሆ፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሙሉጌታ ኃይሉ - የጠለቀው ጀንበር

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ደረጀ ከበደ እና ኃይለገብርኤል አያሌው

እንደ አለመታደል ሆኖ አካዳሚክ እውቀት፣ የዘመናዊነት ተጽዕኖ፣ የምዕራባውያኑ በጎ ባህል ሁሉ የቅርባችን ሆኖ እያለ ልንላቀቀውና ልንተወው ካልቻልንው አሮጌ ባህላችን ውስጥ አንዱ የሆነው ሰዎች በህይወት ዘመናቸው ለሚያደርጉት በጎ አስተዋጽዖ፤ በሕይወት እያሉ የማመስገንና ለተተኪው ትውልድ ያላቸውን አርኣያነት በማንሳት ማክበርና የድካማቸውን ፍሬ ሌሎች እንዲማሩበት ማድረግ ተስኖናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ