የዶ/ር ምህረት ደበበ “የተቆለፈበት ቁልፍ”
ብርሃኑ ሰሙ
ከሁለት ወር በፊት መጋቢት ላይ ነበር “የተቆለፈበት ቁልፍ” የተሰኘው የዶ/ር ምህረት ደበበ ገ/ጻዲቅ ረዥም ልቦለድ መጽሐፍ አንባቢያን እጅ የገባው። መቼቱን በአገር ውስጥና በባህር ማዶ ያደረገው ልቦለድ፤ በ439 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ደራሲው የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስትነት ደረጃ የደረሱት ትምህርታቸውን በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ በመከታተል ነው። በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካንና በኢትዮጵያ እየተመላለሱ በሙያቸዉ እያገለገሉ እንደሆነ በመጽሐፋቸው ላይ ተጠቁሟል። ዶ/ር ምህረት፤ ከሐኪምነታቸዉ በተጨማሪ በአስተሳሰብና በአእምሮ ለውጥ ዙሪያ እያስተማሩና ጥናት እየሰሩ እንደሆነ የሚጠቅሰው መረጃው፤ ህብረተሰባዊ ለውጥ ከግለሰቦች የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚጀምር የሚያምኑ መሆናቸውን ይገልፃል። ልቦለድ መጽሐፋቸውም ይሄንኑ የሚያንፀባርቅ ነው። ልቦለዱ በፍቅርና ጥላቻ፣ በደግነትና ክፋት፣ በግልጽነትና መሰሪነት፣ በሀብትና ድህነት፣ በትጋትና ስንፍና፣ በእውቀትና መሃይምነት ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን በጠንካራ የልብ ሰቀላ የአንባቢውን ስሜት ይዞ ከመነሻ እስከ መድረሻ ይዘልቃል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዓለማየሁ ታዬ
“ነፍስ ካለ፣ መፍጨርጨር አይቀርም!”
ደራሲ፡ ግርማ ደገፋ ገዳ
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
ተስፋዬ ገብረአብ 


