“ሸቦ ግቢ እንገናኝ” ሊቀር ነው (ግርማ ደገፋ ገዳ)

ሆላንዶች አበባ ይወዳሉ። ወንጂ ውስጥ ያላመጡት አበባ የለም። በተለይ ሽቦ ግቢ ውስጥ ከሆላንድ የመጡ አበቦችና ዛፎች በብዛት ይታያሉ። ቤታቸውና ቢሯቸው ዓይን በሚማርኩ ልዩ ልዩ አበቦች የተከበበ ነው። ሽቦ ግቢ ያደጉ ያካባቢያችን ልጆች፣ ማለዳ ከእንቅልፋቸው ተነስተውና መስኮታቸውን ከፈት አድርገው፣ እነዚያን ውብ አበባዎች እየተመለክቱ፤ “Today is a beautiful day” ይላሉ ብለን እናስባለን። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

ጭንቀት የወለደው የጦርነት ነጋሪት (በላይ ለገሰ)

መቋጫ የሌለው የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ አ ንዳ በአፍሪቃ አህጉር ተወዳዳሪ የሌለው የተራዘመና የተወሳሰበ አውዳሚ ጦርነት ቁጥር ስፍር የሌለው የኢትዮጵያውያን ህይወት በልቷል፣ ብዙ ንብረትና  ብት አውድሟል፣ ባጠቃላይ በኤርትራ ከርሰ ምድር የኢትዮጵያውያን አፅም ያልተቀበረበት መሬት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለምንበብ ይህንን ይጫኑ)

የጎጠኝነት አጥሩ እየተሰበረ … የተስፋ ጎህ እየቀደደ ነው (በዳኛቸው ቢያድግልኝ)

አማርኛና ኦሮምኛ ህብር ፈጥረው የአየር ሞገድ እየሰነጠቁ በጆሮአችን እየተንቆረቆሩ ነው። ፓልቶክ በሚሉት ዘመን አመጣሽ መገናኛ። …አብሮነታችን ያስከብረናል ነጻነት ለሁሉም ሲሆን ያኮራል፣ አብረን ስንሆን ያምርብናል የሚሉ አረፍተነገሮች ከየአቅጣጫው ይሰማሉ። ኢትዮጵያ በኦሮሞ ልጆችም የደም ክፍያ አገር ሆና የቆመች የነጻነት ተምሳሌት እንጂ ኦሮሞ እንደ ህዝብ የማንም ባርያ አልነበረም። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለምንበብ ይህንን ይጫኑ)

የተስፋው ቃል፣ የአህአዴግ ቃል

ተመስገን ደሳለኝ

ተስፋ ቆርጬ አላውቅም። ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ሳያጋጥመኝ ቀርቶ አይደለም። ብዙ ጊዜ ገጥሞኝ ያውቃል። ነገር ግን የብዙ ሀገራት ተሞክሮን ካየክ ተስፋ እንድትቆርጥ አይገፋፋህም። ለምን? ካልከኝ ብዙዎች ‹‹ሞቱ፣ ተቀበሩ›› ሲባሉ እንደ ገና መግነዛቸውን በጥሰው ሲያቸንፉ ታያለህና። በሀገራችንም ቢሆን ‹‹አለቁ፣ ደቀቁ›› የተባለላቸው ሟርቱን አቸንፈው አይተሀል። ‹‹እፍኝ የማይሞሉ…›› ሲባል የነበረበትንም ዘመን መቼም ትረሳዋለህ ብዬ አላስብም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ስድብ አምራቾች!

አቤ ቶኪቻው

በመጀመሪያም

ይህ ፅሁፍ ባለፈው አርብ ለወጣችው ለምናፍቃት ፍትህ ጋዜጣ ልኬው ታትሞም የነበረ ነው። ታድያ ለፍትህ ስፅፈው በተቻለኝ አቅም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ያሉት ፈላጭ ቆራጮቻችን ደም ብዛታቸው ከፍ እንዳይል በመጨነቅ አንዳንድ ሃሳቦች ላይ ቁጥብ ስድር ለማለት ሙከራ አድርጊያለሁ። ምክንያቱም ሰዎቹ ደማቸው ሲፈላ የሚያደርጉትን አያውቁትምና፤ የአዲሳባ ወዳጆቼ እንዲሁ ያለባቸው ጦስ ሳያንሳቸው እኔ ደግሞ ተጨማሪ አልሆንባቸውም ብዬ ነው። እናም ይህ ፅሑፍ ዛሬ ለዌብ ሳይቶች ስልከው ትንሽ ከለስ ከለስ አድርጌዋለሁ…

እስቲ አንብቡልኝ…! ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኸረ የፍትህ ያለህ! (ከንጉሤ ጋማ)

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፤ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርኣት ዉስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብኣዊ መብታቸዉ ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፡ የሚናገሩ፤ የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላዉ ለነዚህ ፅንሰ ሃሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርኣቱ ጠላቶች ተደርገዉ በመቆጠር ላይ ናቸዉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሳዛኙ ዜና ኀዘን

ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

መቼም ተስፋዬ ገብረአብ ከጻፈ አንድ ትዝታ የሚጭር ወይም ስሜት የሚነካ ነገር አያጣም። ባለፈው ሣምንት ”አሳዛኝ ዜና” በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሁፉ ደግሞ ስሜቴን መንካት ሳይሆን በክፉ የኀዘን ትዝታ ውስጥ ዘፍቆኝ ሰነበትኩ። እንዴት ሆኖ ማለትዎ አይቀርም፤ እነሆ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮ/ል መንግስቱ “ትግላችን” እና የአእምሯዊ ንብረት መብት (ከታክሎ ተሾመ)

ኮሎኔል መንግስቱ ኃ.ማርያም ትግላችን የተሰኘ ባለ 505 ገጽ መጽሀፍ ጽፎ ሎስ አንጀለስ (አሜሪካ) ፀኃይ አሳታሚና አከፋፍይ ድርጅት ታትሞ ገበያ ላይ ከዋለ ሰነባብቷል። ኮሎኔል መንግስቱ ጨካኝ ብቻ ሳይሆን የራሱን ህዝብ በጥይት ፈጅቶ አገሪቱን ለተገንጣይ አጋልጧል። በአፍሪካ ተወዳዳሪ ሊገኝለት ያልቻለ አብዮታዊ ሰራዊት በትኖ ሀረሬ ውስጥ የግል ህይወቱን እየኖረ ነው። ከስደት ሁኖ “ታሪክ” መተረኩ መልካም ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አኬልዳማ-2 “አቅመ አዳም ላልደረሱ አህዮች የተከለከለ” (አዜብ ሃይሉ)

በጋምቤላ የፉኝዶ ወረዳ የአንድ አባ ወራ አህያ ወደ ጎረቤቱ ዘልቆ አንዲት የሌላ አባወራ ንብረት የሆነች ሴት አህያ ላይ ይንጠላጠልና የልቡን ያደርሳል። የሴቷ አህያ ባለቤትም አህያዬ “ተደፈረችብኝ” በሚል ክስ ይመሰርታሉ። የወንዱ አህያ /ደፋሪው መሆኑ ነው/ ባለቤት ፖሊስ ዘንድ ይወሰዳሉ ክስ ይመሰረትባቸውና ይቀጣሉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግቡን የሳተ ቀስት!

‘ኢሕአፓ’ - አዲሱ የነጻ ፕሬስ ጠላት!?

ከአትክልት እና ጓደኞቹ

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ላለፉት 20 ዓመታት በእሳት የተፈተኑ ቁርጠኞች ናቸው። እስርና እንግልቱን በተደጋጋሚ የወጡበት የወረዱበት ሸክም ነው።  በጠራራ ፀሀይ በወያኔ ጥይት የተገደሉትን መርሳት ይከብዳል። ህክምና ተነፍገው ዘብጥያ ውስጥ የሞቱትንም ማስታወስ እንዲሁ... ይሰቀጥጣል። ዛሬም ወፍራም ወፍራም ክስ ተለጥፎባቸው ቃሊቲ ውስጥ የሚጉላሉትንም ልብ ይሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ