ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አፈር ስሆን፤ ፌስ ቡክዎ ላይ አድ ያድርጉኝ!

አቤ ቶኪቻው

ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር… ብዬ ልጀምር ነበር “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!” ሲሉኝ ታየኝና ተውኩት።

ቆይ እስቲ ወዳጄ መጀመሪያ ከእርስዎ ጋር ሰላምታ እንለዋወጥ። እርስዎ ኖት ቀሪ ሃብቴ…! እንዴት አሉልኝ…? ጤናዎ አማን ነው? ግራ ቀኙ ሁሉ ሰላም ውሎ አድሯል? ጎሽ እንዲህ ነው እንጂ የጨዋ መልስ! እርሱ ጠባቂው ለወደፊቱም እቅፍ ድግፍ አድርጎ ይጠብቅልኝ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርኮኛ - ቅኝት መስፍን ማሞ ተሰማ (ሊያነቡት የሚገባ)

የመጸሐፉ ደራሲ ቆንጅት ብርሃን

መንደርደሪያ

ደምና ዕንባ ተቀላቅሎ በብዕር ሲቀሰም ምንን ይወልዳል? ምርኮኛ! ምርኮኛ የደም መፅሀፍ ነው።  የዕንባ መፅሀፍ። የአንድ ትውልድ ደም፤ የአንድ ትውልድ ዕንባ የተተረከበት የደም ዕንባ ታሪክ። ምርኮኛ አንባቢን ምርኮኛው አድርጎ በትርክቱ ባህር እየደፈቀ፤ ትንፋሽ እስኪያጥር ነፍስ እስክትቃትት አካልና መንፈስን ረግጦ የሚገዛ፤ ሃያል የደም ዕንባ ታሪክ ነው - ያልታደለው ትውልድ ታሪክ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖለቲካን መጋፈጥ እንጂ ማምለጥ አያዋጣም

ሉሉ ከበደ

የዘጠኝ ዓመት ልጅ ነው። አንድ ቀን አባቱን ጠየቀው፤ ” አባባ ፖለቲካ ምንድነው?” “ ጥሩ ጥያቄ ነው ልጄ! ቁጭ በል በምሳሌ አስረዳሀለሁ። “ ይልና አባት ልጁን ካስቀመጠ በሗላ ‘’ፖለቲካ ማለት እንግዲህ ይህን ቤታችንን እንደ ሀገር ቁጠረው። ቤታችን ሀገር ማለት ነው። በቤታችን ውስጥ ስራ እየሰራሁ ገንዘብ የማመጣ እኔ ነኝ።  እኔን እንደ ካፒታሊዝም ቁጠረኝ። እኔ ካፒታሊዝም እባላለሁ። እናትህ ደግሞ እኔ በማመጣው ገንዘብ ለቤታችን የሚያስፈልገንን ሁሉ ምግብም ልብስም ሌላውንም እየገዛች ታስተዳድረናለች ማለት ነው። እናትህን ደግሞ እንደመንግስት ቁጠራት። እናትህ መንግስት ነች። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ ቦላሌ!

ግርማ ደገፋ ገዳ

የመለስ ቦላሌ “ቦላሌ” ከመሆኑ በፊት ቁምጣ ነበር። አዲስ አበባ ለትምህርት ሲመጣ ቦላሌ ሆነ። ማገብት ጠርቶት ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ሲመለስ እንደገና ወደ ቁምጣ ተለወጠ። ዳግም ወደ ቁምጣ ሲቀየር፣ ሃሳቡ ኃይለኛ ቁምጣ ሆኖ ለመቅረት ነበር። ይሁንና አንዴ ቦላሌ አንዴ ቁምጣ እየሆነ፤ ራሱን እየቀያየረ በረሃ ከረመ። የሓርነት ድርጅቱ ተለዋጭ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ደረጃም ደረሰ። ድርጅቱ በገንዘብ ጠብሽ በተቃጠለበት በአንድ ወቅት፣ የአድዋን ባንክ መዝረፍ አማረው። አምሮትም ዝም አላለም፤ ድርጅቱን ሚሊዮን በሚሊዮን የሚያደርጉ ዘራፊዎችን መረጠ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ተመስገን!!..ቫት በልተን ቫት ጠጥተን እንኖራለን” (በግሩም ተ/ሀይማኖት)

መቼም ሀገር ደርሶ የመጣን ስደተኛ በጥያቄ ማጠደፉ ያለ ነው። አሀ! ቀዬ መንደሩ አገር ሰፈሩ ሰላም ነው ወይ ማለት ነውር አይደለም እኮ!..እኔማ ጥሎብኝ ሀገር ላይ የተነፈሱትን ትንፋሽ ይተነፍሱልኝ ይመስል፣የኢትዮጵያን ጠረን ይዘውልኝ የመጡ ይመስል.. እስራቸው ገብቼ በወሬ መተግተግ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሁለት አምባዎች ወግ... ወግ አንድ - ናፍቆቴን መልስልኝ

ያሬድ ጥበቡ (የቀድሞ ኢህዴን / ብአዴን ሊቀመንበር ነበሩ)

የዘንድሮ የልደት በአል ከወትሮው ለየት ያለ ነበር። ገፀ በረከትም ነበረው፣ ያውም ሁለት። በረከት ስምኦንና ሌተና ኮሎኔል መንግስቱ ያቀረቡልን ሰጦታ። ስጦታዎቹንም ከከፈትሁ በሁዋላ እኔም ስለሁለቱ አምባዎች ወግ ላወጋችሁ አሰብኩ። አንዱ አምባ የኢህአዴግ መሆኑ ነው ሌላው ደግሞ የደርግ። አምባ ላይ የሚሸልል ደግሞ አምባገነን ነው። እናንተዬ ይህን ቃል የፈጠረ መንዜ የኖቤል ሽልማት እንደሚገባው አትስማሙም? የመጀመሪያውን ወግ ‹‹ናፍቆቴን መልስልኝ›› አሰኝቸዋለሁ። ያለምክንያት አይደለም። ከአንድ ሁለት አመት በፊት “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ላቀረበልኝ ቃለምልልስ ‹‹የአዲሱና በረከት ሳቃቸው ይናፍቀኛል›› ብዬ ናፍቆቴን በአደባባይ ገልጬ እንደነበር የጋዜጣዋ ታዳሚዎች ያስታውሱ ይመስለኛል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሳዛኝ ዜና

በተስፋዬ ገብረአብ

ይህን አሳዛኝ ዜና የሰማሁት፣ ጥር 17፣ 2012 ተስያት ላይ ነበር። አንድ ጓደኛዬ በስልክ እንዲህ ሲል ጠየቀኝ፣ “ኢህአፓ የፈፀመውን ሰማህ?” “አልሰማሁም። ምን ፈፀመ?” ባጭሩ ነገረኝ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“እኔ ከታሰርኩ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይታሰራሉ!?”

አቤ ቶክቻው

“እያሱ በርሄን ያላየ ኦሞት… ይሄዳል ወደ ሞት!”  (አድማጭ ተመልካቹ)

ቆይማ አንዴ…ነገሩን ላልሰማችሁት ወዳጆቼ ከስረ መሰረቱ ለማስጨበጥ ሙከራ ላድርግ! ምን ሆነ መሰልዎ…? በጋምቤላ ክልል አንድ ሹም አሉ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ናቸው። አቶ ኦሞት ኦቦንግ ይባላሉ። ሹምየው በ1996 ዓ.ም ያኔ የፖሊስ ኮሚሽነር እያሉ የክልሉ ፖሊስ ሆዬ ከፌደራሉ ፖሊስ ጋር በመተባበር፤ በአኝዋክ ወንድሞቻችን ላይ “ዘግናኝ” የተባለ ጭፍጨፋ አካሂዶ ነበር። እንደውም፤ ምነው እንኳ የሆነ ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ሱዳኑ ጋሽ አልበሽር “በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለዛውም በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከሰሱ ነው” ተብሎ በሀገር ምድሩ ሲወራ፣ እኛም ስናንሾካሹከው አልነበር? ታድያኮ አንዱም ክስ ይሄ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ