የጥቃት ኢላማ የሆነው የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ፌደሬሽን (ከሳሙኤል ሽፈራው)
ይህ ፌደሬሽን በሂውስተንና በዳላስ ሁለት ቡድኖች ተመሰረተ። በቀጣዩ አመት ዳላስ ጨዋታው ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሜዳ በመሄድ የታደምሁ ነኝ። ይህ ፌደሬሽን ሲመሰረት ሁሉም እንደሚያስታውሰው ከቀይሽብር አምልጠውና ተርፈው የመጡ ስደተኞችና ትቂት በዚሁ በዳላስና ሄውስተን አካባቢ ለትምህርት መጠው የቀሩ ወገኖች የጀመሩት ነበር። በቀጣይ አመታት ከተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞች የተመሰረቱ ቲሞች ወደፌደሬሽኑ በመቀላቀል እድገት እንዲያገኝ አርገውታል። በየአመቱ በአሜሪካ የነጻነት ቀን ሰንበት የሚካሄደው የፌደሬሽኑ የእስፖርት በአል ላለፉት 28 አመታት ለኢትዮጵያውያን ልዩ የሆነ የአመት በአል በመሆኑ፤ ሳምንቱን ብዙ ወገኖች በጉጉት ይጠብቁታል። በ1980 ወቹ አመታት አገራችን በደርግ ስርአት ስር ስለነበረች፤ በጊዜው የነበረው አንባገነን ይህን ፌደሬሽን በክፉ ይመለከተው እንደነበርም የሚዘከር ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...



