ሆነና ነገሩ የተገላቢጦሽ፣ አህያ ወደ ቤት ውሻ ወደ ግጦሽ

ይገረም አለሙ

አበው መሆን ያለበት ቀርቶ የማይሆነው ሲሆን፣ ያለ አባቱ ያለወግ ሥርዓቱ የሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው የሚገልጹበት ይህ አባባል ተቀዋሚ ተብሎ ለተሰለፈው ግን ምን ለምን እንዴት? አንደሚወም ለማያውቀው ቢያወቅም በወሬ እንጂ በተግባ ለማይገኘው ወገን ድርጊት በጣሙን ገላጭ ይመስለኛል። ድርጊት እየጠቀሱና ማስረጃ እያጣቀሱ በዚህ አባባል የሚገለጹ በርካት ጉዳዮችን ማንሳት የሚቻል ቢሆንም ለዛሬ ግን አንዱን ብቻ በእጅጉ የተጠናወተንን የመርሳት በሽታ/ችግር ብቻ ላንሳ። ግን ከዛ በፊት ርእስ ያደረኩትን አባባል ባስታወሰኩ ቁጥር ፈጥኖ በአእምሮየ የሚመጣ አንድ ነገር አለ፣ ፕሮፌሰሩ ከአሜሪካ ወደ ትግል ሜዳ ኮረኔሉ ከትግል ሜዳ ወደ አውሮፓ ከአባባሉ ጋር የተዛመደ አይደለም ትላላችሁ። ኮረኔሉ ግዴለም መሄዱን ይሂድ እዛ ሆኖ ታጋይ ነኝ ማለቱ እንዲህም ብሎ አጃቢና ተከታይ ማግኘቱ ግን አዬ! እኛ ያሰኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከቆሻሻ ኑሮና ሞት ለመላቀቅ ቆሻሻውን ሥርዓት ማስወገድ

መሳፍንት ዘፈረንሳይ ለጋሲዮን

Koshe landslide, Addis Ababa, Ethiopia
በቅርቡ ከ115 ሰዎች በላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ያለቁበት የቆሻሻ ናዳ አደጋ የደረሰበት ቆሼ ሰፈር በከፊል
ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ በሆነባት አገራችን በየጊዜው የሚፈራረቁት ሰቆቃዎች ልብን በኀዘን ካራ ማድማታቸውን እንደቀጠሉ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከደረሱብን መዓቶች ጥቂቱን ብናነሳ፤ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ደጃፋቸው ላይ ድፍት ብለው የቀሩትን፣ መብታቸውን ለመጠየቅ ሲጮሁ የጥይት ራት የሆኑትን፣ የኢሬቻን በዓል ለማክበር አምረው ደምቀው እንደወጡ ገደል ሰብስቦ ያስቀራቸውን፣ እንዲሁም በቅርቡ በቆሻሻ ናዳ ታፍነው እስከወዲያኛው ያንቀላፉትን ወገኖቻችንን በቁጭትና በመሪር ኀዘን እናስባለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን?

አንዱዓለም ተፈራ

አሜሪካ ለሩስያ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ናት።
የአሜሪካ ርዕዩተ ዓለም ከሩስያ ርዕዩተ ዓለም የተለየ ነው።

በአሜሪካ፤ ከአገሪቱ የግለሰብ የሃሳብ የነፃነት የተነሳ፤ ከአገራቸው ይልቅ ራሳቸውን የሚያስቀድሙ ሰዎችም በመንግሥት መዋቅርም ይሁን በንድግ ተግባሩ ውስጥ በኃላፊነት የሚገኙ አሉ። ይህ የግል አመለካከታቸው፣ የራሳቸው ከመሆኑም በላይ፤ በማንም ግለሰብ፤ የበላይ አለቃቸውም ሆነ ለነሱ ተጠያቂ በሆኑ ግለሰቦች ዘንድ፤ አያስገምታቸውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመማረር - ማምረር

ይገረም አለሙ

ኃይለማሪያም በመለስ ጭንቅላት
መማረር ማውራት ከፍ ካልም ሰልፍ መውጣት ሲሆን፤ ማምረር ግን ድርጊት የሚጠይቅ መሆኑ ነው

ሰሞኑን የአቶ ሀብታሙ አያሌውን ቃለ ምልልስ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል አዳምጠን ብዙዎች አዝነናል፣ አልቅሰናል፣ ተናደናል፣ ወያኔን ተሳድበናል አውግዘናል ወዘተ። በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በደረሰው አልቂትም እንዲሁ። ይህን ሁሉ ግን በሰማን ቁጥር አዲስ ለሚሆንብን ለእኛ እንጂ አዲስ አይደለም። አቶ ሀብታሙ በሕይወት ተርፎ በነጻናት መናገር የሚቻልበት አገር ተሻግሮ ሊነግረን በመቻሉ እንጂ፤ ከዚህ የባሱ ብዙ አጅግ ብዙ ኢ-ሰብዓዊ የሆኑ ዘግናኝ ድርጊቶች በኢትጵያውያን ላይ ተፈጽመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአድዋ ድል "በዕድል”?

ከ"ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዕውቀት መለዋወጫ መረብ" የተሰጠ አስተያየት

አድዋ | Adwa.
የአድዋ ጀግኖቻችን

የትግሬ ነፍጠኛ፣ የሸዋ ፈረሰኛ፣ የጎጃም እግረኛ፣ የአማራ ስልተኛ ከቦ ይቀላው፣ ያናፋው፣ ያንደገድገው ጀመር። ከእንዝርት የቀለለ የጁየ፣ ከነብር የፈጠነ ቤጌምድር፣ ከቋንጣ የደረቀ ትግሬ፣ ከአሞራ የረበበ ሸዌ፣ ከንብ የባሰ ጎጃሜ እያባረረ በየጎዳናው ዘለሰው። አውሬ የነጨው ነጭ መንጋ እየመሰለ በየዱር ሆዱን ገልብጦ ወደቀና የአሞራ ቀለብ ሆነ።[1]
መጋቢት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፱ ዓ. ም.

በወለላዬና በዶክተር ተድላ ሃሳብ ላይ ተጨማሪ፣

በቅድሚያ ክብር በደምና በአጥንታቸው አንድነት አገር ላቆዩልን ለአድዋ ጀግኖች በሙሉ፣ ወለላዬ በስዊድን የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል መዘክርና በዝግጅቱ ላይ የነበሩትን ክስተቶች ስላሳወቁን ብቻ ሳይሆን ምላሽ በመስጠትዎና ለሚመለከተውም ጥሪ በማድረግዎ ምስጋናችን የላቀ ነው። በእኛም በኩል የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል በመጣጥፎች ለመዘከር ዝግጅት በምናደረግበት ጊዜ አንዳንዶቻችን የእቴጌ ጣይቱን ታላቅ አስተዋጽዖ ለብቻው ማዘጋጀት ጀምረን፣ ነጥለን የምናወጣው ታሪክ ጎደሎ ሆኖ ስላገኘነው አድዋን ከመላው ጀግኖቹ ጋር መተረኩ የተሟላ ሆኖ አግኝተነዋል። (የወለላዬን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!) | (የተድላ ደ. ተክሌን (ዶ/ር) ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለአድዋ፣ ስለምኒልክ በስዊድን

ተድላ ደ. ተክሌ (ዶ/ር)

ጣይቱ ብጡል እና ምኒልክ
እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና አጤ ምኒልክ

ይህ ጽሁፍ መሰረት ያደረገው “እምዬ ምኒልክ ወላዋይ ነበሩ ወይ?” በሚል ርዕስ ወለላዬ የተባሉት ጸሐፊ ከስዊድን አበክረው መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው (የወለላዬን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)። በጽሁፉ መሃልም ወለላዬ ጋዜጠኞችና ተመራማሪዎች የት ናችሁ፤ ዝም አትበሉ ሲሉ ይማፀናሉ። የጥሪያቸው ምክንያትም የስዊድን ሶሻል ዴሞክራት ተቀጥላ የሆነው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማኅበር የአድዋን ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ የመጨረሻው ተናጋሪ ያደረጉት ንግግር ነበር። እኝህ ሦስተኛ ተናጋሪ ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ ይባላሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አማራው ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል

ተሻለ መንግሥቱ

ከዐይን በላይ የሚታመን ባለመኖሩ “ማየት ማመን ነው” ይባላል። እኔም አየሁ፤ አመንኩም። እናም አልሁ - “ወያኔ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን በተለይም በአማሮች ላይ የሚፈጽመው ድንበርየለሽ ግፍና በደል በመጨረሻው የዞረ ድምር ምን ያመጣብን ይሆን?” አሳሳቢና አስጨናቂ ጥያቄ ነው። የዚህን የወያኔን ዘመን ፍጻሜ ለማየት ብዙዎቻችን የችግሩ ገፈት ቀማሾች ብንጓጓ እስካሁን ከምናውቀውና ከዚህ በታች ከምነግራችሁ አስደንጋጭ መረጃ አንጻር አይፈረድብንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኛ ስናደርገው ትክክል፤ ሌላው ሲያደርገው ወንጀል

ይገረም አለሙ

Girma Seifu
አቶ ግርማ ሰይፉ

የፖለቲካ ባህላችን ከጅምሩም ያላማረበት በሂደትም መሻሻል የማይታይበት ሆኖ ዛሬም በትናንቱ መንገድ ከመንጎድ መውጣት ባለመቻላችን ለገዢዎች እንደተመቸን አለን። ብልሹው የፖለቲካ ባህላችን ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ሌላው ሲናገረው ወይንም ሲሰራው ወንጀል ያልነውን አኛ ስንሰራ ስንናገረው እንደ መልካም ነገር ይታይልን መባሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ድፍረትና ንቀት

ይገረም አለሙ

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

22 ፓርቲዎች የፕሮፌሰሩን ፓርቲ ጨምሮ ከወያኔ ጋር በወያኔ ጋባዥነት ድርድር ጀምረዋል የሚለውን ዜና እየሰማን ባለንበት፤ መድረክ ከኢህአዴግ ጋር የብቻ ድርድር ይፈልጋል፣ ምክንያቱም ዋንኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ስለሆነ የሚል ነገር በፕ/ር በየነ አንደበት ሲነገር ሰማን። የፖለቲካ ፓርቲ እንመራለን የሚሉት ርስ በርስ ስለሚተዋወቁ እናንተ 22ትም ሆናችሁ 102 አትረቡም ጠንካራው እኔ የምመራው መድረክ ነው ማለታቸው ተቀባይነት ባይኖረውም አያስገርምም። ሕዝቡ መድረክን ርስተ ጉልት ስላደረጉት እርሳቸውም ሆነ ስለ መድረክ ምንም እንደማያውቅ ቆጥረው ይህን ማለታቸው ግን የድፍረታቸውን ልክ የንቀታቸውን መጠን ነው የሚያሳየው። በወያኔ መሪዎችም በተቀዋሚ ተብየዎችም አክብሮት የተነፈገው ሕዝብ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እምዬ ምኒልክ ወላዋይ ነበሩ ወይ?

የአድዋን በዓል አከብራለሁ ብዬ ሄጄ፤ አፄ ምኒልክ ሲሰደቡ ሰምቼ ተመለስኩ

ወለላዬ ከስዊድን

Prof. Tekeste Negash
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ | Prof. Tekeste Negash

ምሁር ባልባልም በቃ! አልጸጸትም፣
ፊደል ቢሸከሙት አያደርስም የትም።
አሮጌ ልብስ ነው አስቀያሚ ኮተት፣
ማስተዋል ካነሰው ቢከመርም ዕውቀት።
(የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ወለላዬ)

የስዊድን ሶሻል ዴሞክራት ተቀጥላ የሆነው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማኅበር የአድዋን ድል በዓል ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ ስቶክሆልም ዝግጅት አድርጎ ነበር፤ እሁድ ማርች 5 ቀን 2017። በዝግጅቱ ላይ እንድገኝ ጥሪ ደርሶኝ ከተካፈሉት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ነበርኩ። ዝግጅቱ በቪድዮ ክሊፕ እንድናዳምጣቸው የተመረጡልን ሰዎች ሲኖሩት፣ በአካል የተገኙ እንግዳም ነበሩ። ክሊፑን በስክሪን እያየን ካዳመጥናቸው አንዱ “The Battle of Adwa” የተባለውን መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር ዮናስ ሬይሞንድ ሲሆኑ፣ ስለ መጽሐፋቸው ከኢጣሊያ የታሪክ ተመራማሪ ከጆን ዌልሽ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ይገኝበታል። ሁለተኛው ደግሞ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሚስተር ታቦ ምቤኪ፣ በስድስተኛው የዓለም አቀፍ አፍሪካ ኮንግሬስ ላይ ስለ አድዋ ያሰሙት ንግግር ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ