አዳማ ከኦሮሚያ የመውጣት መብቷ ሊከበር ይገባል

ይመር አብዶ

St. Gebriel Church Nazreth Adama.
ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን፣ አዳማ (ናዝሬት) | Photo: Fikir A. (2017 Jan. 22)

የአዳማ ልጅ ነኝ። እዚያው ተወልጄ ያደኩ። አባቴ ኦሮሞ ሲሆን እናቴ ጉራጌ ናት። አባቴ ኦሮምኛ ይናገራል። ግን ቤታችን የሚነገረው አማርኛ ነው። በአብዛኛው የናዝሬት ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው። በከተማዋ በየመንገዱ በብዛት የሚነገረው አማርኛ ነው። አዳማ ናዝሬት እንደ አዲስ አበባ ናት ማለት ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባን ያቀፈ ሸዋ የሚባል ክልል ቢኖር ጥሩ ነው

ግርማ ካሳ

New Shewa zone.
"ኦሮሚያ ስትኖር ኢትዮጵያ ልትኖር ትችላለች። ኦሮሚያ ስትፈርስ ግን ኢትዮጵያ የምትባል አገር ቅዠት ትሆናለች" መርጋ ኢብሳ

መርጋ ኢብሳ የተባሉ ጦማሪ የአዲስ አበባና አካባቢዋን ሕዝብ በተመለከተ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተው አነበብኩኝ። ትንሽ አሳቁኝም አናደዱኝም።

"ኦሮሚያ/ሸዋ ውስጥ ያሉ በትምክተኝነት ምክንያት ኦሮምኛ ያልቻሉ ጥቂት ማኅበረሰቦች ካሉ ሁለት እድል አላቸው። አንደኛ ኦሮምኛን ለምደው ተስማምተው የክልሉን ሕግ አክብረው መኖር። ሁለተኛ ትምክተኝነት የሚወጥራቸው ከሆነ ደግሞ ወደመጡበት በፍላጎት ሄደው በክልላቸው እንደፈለጋቸው መሆን ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ኦሮሞን በጎጥ ለመከፋፈል የምትጥሩትን የሚሰማቹ የለም። ኦሮሞ አንድ ነው። ሁሉም የቦረኔ ባረንቱ ልጅ ነው። ሸዋ ሲነካ ወለጋ ተነካ፤ ሐረር ሲነካ ጅማ አርሲ፣ ባሌ፣ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ ኢሉ፣ ወሎ(ኦሮሞ)ን ያገባዋል። ኦሮሚያ ስትኖር ኢትዮጵያ ልትኖር ትችላለች። ኦሮሚያ ስትፈርስ ግን ኢትዮጵያ የምትባል አገር ቅዠት ትሆናለች“ ነው ያሉት እኝህ ጦማሪ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኛ ወደ ትግሉ ካልሄድን ችግሩ ወደኛ መምጣቱ አይቀሬ ነው

Christian and muslimባህር ከማል

እራስን ከጥቃት በመከላከል ሰላማዊ ህይወት ለመምራት ከሌሎች ሰዎች ጋር ተቻችሎና ተስማምቶ አብሮ የመሆን ባህርይ የሰው ልጅ በተፈጥሮ የሚያገኘውና በህወት ልምድም የሚያዳብር ችሎታ ነው ማለት ይቻላል። ይህ አብሮ የመሆን ልምድ ከቤተሰብ ጀምሮ በጉርብትና፤ በጎሳና ሀይማኖት መመሳሰል እያደገ አገርን እስከ መመሥረት ይደርሳል። በሂደትም አንድነት ኃይል መሆኑንም ያረጋግጣል። እነዚህ በየደረጃው ያሉት ስብስቦች በውስጣቸው ልዩነት መኖሩ አይካድም። ልዩነት በሀገር ደረጃ በተሰባሰቡ ሰዎች መሀከል ብቻ ሳይሆን በመንትዮች መሃከልም ይታያል። ሕዝቦች ልዩነታቸው አንደተጠበቀ ሆኖ በጋራ በሚያስተሳስራቸው፤ በሚያቀራርባቸውና ባሳለፏቸው ታሪካዊ አብሮነት ተመስርተው አንድነትን ፈጥረው በድንበር የተከለሉ አገራትን መስረተው አብረው ይኖራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲያልቅ አያምር

ተሻለ መንግሥቱ

Empress Taytu Betul and Emperor Menelek II of Ethiopia.
እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና አጤ ምኒልክ

እንዳጀማመራቸው አምሮባቸው የሚያልቁ ነገሮች ቢኖሩ በጣም ጥቂት መሆን አለባቸው ብዬ አምናለሁ። እንጂ ድል ባለ ድግስ የተዳሩ ጥንዶች በፍቺ ወይ በሞት እንደሚለያዩ፣ ብን ባለ ፍቅርና ወዳጅነት ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች አንዳች ነገር በመሃላቸው ገብቶ እንደሚመነቃቀሩና “ዐይንህ/ሽ ላፈር” እንደሚባባሉ … ፀሐይ የሞቀው ማኅበረሰብዓዊ እውነታ ነው። እናም እውነትም እንዳማረ አይገድልም - ማለቂያም ሁሉ እንደጅማሮ አያምርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድ ሚሊዮን ስንት ነው?

ነፃነት ዘለቀ

አንድ ሚሊዮን
አንድ ሚሊዮን ስንት ነው?

ይሄ የቁጥር ነገር አልገባኝ እያለ መቸገሬን የምገልጥላችሁ አገሬ ውስጥ በምታዘበው የሙስና ግዝፈት እያፈርኩና እያረርኩም ነው። ትንሹም ትልቁም ከመሬት እየተነሣ “አንድ መቶ ሚሊዮን ከባንክ ተበድሬ ...፣ አምስት መቶ ሚሊዮን ብር ከባንክ ተበድረን ስናበቃ ...፣ ለእገሊት 30 ሚሊዮን አበድሬያት ...” እያለ ሲያወራ አንደበቱን ያዝ እንኳን አያደርገውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድርድሩ

ይገረም አለሙ

ወያኔ ለምን ይደራደራል?
ወያኔ ለምን ይደራደራል? “ተቀዋሚዎች” ለምን ይደራደራሉ?

መንደርደሪያ፤ ብዙ ግዜ አዲስ ያልሆኑ ግን እኛ አዲስ የተፈጠሩ ያህል የምንጮህባቸው ነገሮች ሲከሰቱ ብዙዎች የሚያሳዩት ነገር “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” ይሉ አይነት ነው። ወያኔ ሥልጣኔን ያሰነብትልኛል ብሎ እስካመነ የማይቆፍረው ጉድጓድ እንደሌለ እየታወቀ ድርድር ጠራ ተብሎ፤ ተቀዋሚ ተብየዎችም ጥሪውን ተቀብሉ ተብሎ፤ አዲስ ተአምር የተፈጠረ ይመስል ድጋፍና ተቃውሞ በተለመደው መንገድ እየተሰማ ነው። ነገር ግን ከተለመደውና መረጃም ማስረጃም ፍለጋ ከማያደክመው የፍረጃና ውንጀላ ጉዞ ወጣ ብሎ ድርድር ለምን፣ ድርድር በእነማን መካከል፣ ድርድር እንዴትና በምን ሁኔታ? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ የሚችል አስተያየት መጻፉ፣ ልምድ ማካፈሉ ነበር የሚበጀው። እኔ ይህን ለማድረግ የሚበቃ እውቀትም ልምድም የለኝም። ፍረጃና ውንጀላ ላይ በመሮጥም ሆነ ጭፍን ድጋፍ በመስጠት ደግሞ አላምንም፣ በዚህ መካከል ሆኜ ስለ ድርድሩ የተሰማኝን ልበል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሳምንቴ ትዝብትና ትንግርት!

አስፋ ጫቦ (Corpus Chirsti, Texas, USA)

Donald Trump.
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ “አርብ ማታ ስዊድን የደረሰው አደጋ!” አለ። ስዊድኖቹ “እንዴት እኛ ሳናይ፣ ሳንስማ ትርምፕ ሰማ!” አሉና አሽሟጠጡት። ይህንን ዜና ያገኘው ከFox ነበር።

አሜሪካ ዛሬም በሁለንተናው ግምባር ቀደም ነኝ ስለምትል (“ያማ ያለፈ ወሬ ነው!) የሚሉ ሞልተዋል) በፕሬዚዳንቱ፤ በዶናልድ ትራምፕ፤ ልጀመር። ”የኔ ጠላት የአሜሪካን ሕዝብ ጠላት ነው”፣ “They are not my enmeies but the enemy of the American people) ብሎ አረፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፓርቲዎች የሚፈርሱት - በራሳቸው አባላት

ይገረም አለሙ

Ethiopian political parties
ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ እና አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ (ዲዛይን @ ኢዛ)

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ ከተቀዋሚው ጎራ የማይጠፋውና ሰሞኑን ከሰማያዊ ፓርቲ ሰፈር እየተሰማ ያለው መወነጃጀልና መፈራረጅ ብሎም ሰማያዊ ፓርቲን ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ ሊያፈርሱት ነው የሚለው ጩኸት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምዝበራ በየፈርጁ

ተሻለ መንግሥቱ

ሜቴክ
በከፍተኛ ደረጃ ምዝበራ ከሚካሄድባቸው ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ሜቴክ

ይህ የፍዳና የሰቆቃ ዘመን እስኪያልፍና የማይቀረው ወርቃማ የነፃነት ዘመን እስኪመጣ በሰመመን የምቆይበትን ብልኃት ባገኝ ወደድኩ። እንዲያ ዓይነት ጥበብ ተገኝቶ እንደእሥራኤሉ ፕሬዝደንት (ኤርየል ሻሮል) በሞትና በሕይወት መካከል አሸልቦ ሳይሰሙ ሳይለሙ ብዙ ጊዜ መቆየት ለእንደኔ ያለው ሰው ተፈልጎ አይገኝም። ኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር ጥቂት የማንባል ዜጎች አብዛኛው የምንሰማውና የምናየው ነገር ግራ እያጋባን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከመኖር ይልቅ አለመኖርን እንመርጣለን። አስደንጋጭ ወቅታዊ ሁኔታ ውስጥ ተዘፍቀናል። ራሳችንን እየታመምን የምንኖር አለን - በበኩሌ በጣም እያመመኝ እንደምኖር ብደብቅ ዋሸሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሕዝብ ለመታመን፣ የተግባር ሰው መሆን

ይገረም አለሙ

ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ በሚለው የብዕር ስሙ የምናውቀው አቶ ሙሉጌታ ሉሌ (ነብሱን ይማረውና) በጦቢያ መጽሔት የሀምሌ 1998 እትም ላይ ባስነበበን ጽሁፍ “ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ጭንቅላት የሀያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን መግቢያ ችግሮቻችንን ለመፍታት የምንደፋደፍበትም ሁኔታ አለ ለማለት እደፈርለሁ። በዚህ የተነሳም ነው በዘመናችን የሀሳብ ትግልና የሰከነ ውይይት ብሔራዊ ርዕይ ሊሰርጽ ያልቻለው፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ጭንቅላት ማሰብ በዚህ የተነሳ በዚህ ሀገር በራሳችንም በመንግሥታችንም መተማመን እንደጠፋ እንኖራለን። የምናምንበትና ህሊናችንን የሚኮረኩር አንዳች ኃይል በማጣትም የመንፈስ ሽባነት ያደረብን ይመስላል። ” ብሎ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ