“ኩኩሉ …” ማለት ይቻላል አይደል? (በፍቃዱ ሞረዳ)

Jawar Mohammed

“ለሁሉም በሚበጅ ጉዳይ ላይ ተቀራርቦ ያለመታከት መነጋገር ያስፈልጋል፤ በግራ እጅ እየካቡ በቀኝ መናድ ኪሳራ ነው - በፍቃዱ ሞረዳ (ጋዜጠኛ)

የውጭ አገር ዜግነት ባላቸው ሰዎች የሚተዳደሩ ሚዲያዎችን አስመልክቶ ዐቢይ አሕመድ ለኢሕአዴግ ፓርላማ ያሰሙትን ንግግር/ዛቻ፣ አንዳንድ ቅን ልቦች "ጃዋርን የሚመለከት አይደለም" እያሉ ሊያረጋጉ እየሞከሩ ነው። "እንደአፋችሁ ያድርግልን" እንላለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመደመር መጽሐፍ ምረቃ - የዘገምተኞችና አድር ባዮች ጭብጨባ በሚሌኒየም

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመደመር መጽሐፍ ምርቃት ላይ ፊርማ ሲያኖሩ

“በርግጥ ሰውዬውም ጭብጨባ ይወዳል”

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. - የዶ/ር ዐቢይ መጽሐፍ ተመርቋል። እኔም ከዚያ በተያያዘ ራሴን ታምሜ ዋልኩ - አሁን ድረስ። የነበረኝ የEmotional Quotient አንጻራዊ የተሻለ ደረጃ ወርዶብኝ ራሴው ስቸገርና ሰዎችንም ሳስቸግር አመሸሁ። የሚገነዘብህ ሰው ሲጠፋ ራስህን ያምሃል፤ ሲያምህ ሁሉም ነገር ያስጠላሃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኦርቶዶክስንና አማራን አከርካሪ የመምታት የመጨረሻው ምዕራፍ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ፓትርያርኮች

“ኦርቶዶክስም አሁን ለምትገኝበት የነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ አሳሳቢ ደረጃ የደረሰችው የራሷን የመታነቂያ ገመድ ራሷው ፈትላ ነው”

ምሕረት ዘገዬ

1. የጠ/ሚንስትሩ የመደመር ልቦለድ መጽሐፍ እየተመረቀ ባለበት በአሁኑ ቅጽበት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ምን እየተደረገ ነው?

  • መዝገብ የያዙና በሥውር የፖሊስ ኃይል ጥበቃ የሚደረግላቸው የወለጋና አርሲ ቄሮዎች በጀሞና በሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ይዞታዎች ሥር የሚገኙ መሬቶችን እየተከፋፈሉ ነው። ካለበቂ ጥበቃ የሚገኙ ኮንዶሚኒየሞችን በር በመስበርም እየተሻሙ ነው። እነሱን ሃይ የሚል ግሕግ የለም። …
  • የሌሎች ዜጎች በተለይም የአማሮች ቀደምት ይዞታዎች በሻማና በኩራዝ እየታሰሱ እንዲፈርሱና ሰዎቹ ወደው ባልተፈጠሩበት ነገዳቸው ምክንያት ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ከቦታቸውና ከአገራቸው እንዲፈናቀሉ እንዲሰደዱም እየተደረገ ነው - በአዲስ አበባ ዙሪያ ሁሉ። …
  • አማሮች ከያዟቸው የፌዴራልና የክልል ሥልጣንና ኃላፊነቶች እየተነሱ የገዢው ኃይል ታማኝ የሆኑ ሆዳሞችና ምሥጢረኞች እንዲሁም የአማራን መጠሪያ ስሞችና የአማራነትን ዘውጋዊ የውሸት ማንነት በዳግም ጥምቀት ያገኙ አሰለጦች እየተተኩ ነው። አማራ በቋንቋውም ሆነ በባህሉ ለማንምና ለሁሉም እኩል ክፍት በመሆኑ ይህ ሁኔታው ክፉኛ እያስጠቃው ይገኛል። በተቅጠፈጠፈ አፉና በአስመሳይ ኢትዮጵያዊ የሥነ ልቦና ቀመሩ ሠርጎ የሚገባ ዘረኛ ሁላ፤ አማራን በቀላሉ ለጥቃት ይዳርገዋልና ለዚህ ዐይነቱ ችግር አፋጣኝ መፍትሔ ካልተገኘ ችግራችን እንደጠነነ መቀጠሉ ነው። ለዚህም አንዱ ምሣሌ ከአማራ ሕዝብና አዴፓ አባላት ጋር ውኃና ዘይት የሆነው የጠሚው ልዑክ - ስሙም ጠፋኝ - የአማራው ክልል አዲስ ፕሬዝዳንት ነው። ይህ ሰው መንፈስ ቢጤ ሳይሆን አይቀርም። የት ነው ያለው ግን? ምን እየሠራስ ነው? ዋና ተልእኮው ለጠሚው ነው ወይንስ ለአማራ? የዘር ሐረጉ የሆነውን ይሁን ግዴለም - ግን ለክልሉ ምን እየፈየደ ነው? በፍንጭ ሰጭ ቃላት ጉግል አድርጌ ስሙን አሁን አገኘሁት - እውነቴን ነው - ተመስገን ጥሩነህ። ወይ መሪና ተመሪ! ተለያየን።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

እውነትም ስምን መላክ ያወጣዋል - ደጀን ከተማና አካባቢዋ ያሳዩት ኢትዮጵያዊነት!

ከዓርብ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከረፋድ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ጎሐጽዮን አካባቢ ቄሮዎችና የኦሮምያ ፖሊስ መንገድ ዘጉ

ግርማ በላይ

የአንዳንድ ስያሜዎች እውናዊ ልጨኛነት የሚገርም ነው - የአንዳንዶች ደግሞ ከማስገረምም አልፎ በለበጣ የሚያስፈግግ ነው። “ዐመለ ወርቅ” ተብላ ነጭናጫ፣ “ሽመክት” ተብሎ ባንድ ጥፊ የሚዘረር፣ “ደም መላሽ” ተብሎ ከእናትና አባቱ ገዳይ ጋር በጎን ተመሳጥሮ ባንድ መሸታ ቤት አሥረሽ ምቺው የሚል ወስላታ፣ … የመኖሩን ያህል፤ እንደስማቸው “አለልኝ”ና “ድጋፌ” ሆነው ለተመካባቸው ሰው ደጀንና ከለላ የሚሆኑ ድንቅ ዜጎች አሉ። እርግጥ ነው ስም አይገዛምና በስም ዙሪያ ብዙ ተቃራኒ ነገሮች መኖራቸው እውነት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ዛሬ በአዲስ ዓመት

Ethiopia Zare

የአዲስ ዓመት ቃል - ከኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ

መልካም አዲስ ዓመት!

ድረ ገጻችን ኢትዮጵያ ዛሬ ሚዛናዊ መረጃዎችን በማቅረብ የተለያዩ አመለካከቶች እንዲንፀባረቁና የሐሳብ ነፃነት እንዲጎለብት ባለን አቅም ባለፉት አሥራ አንድ ዓመታት ስንንቀሳቀስ ቆይተናል። ይህ የመረጃ ምንጭ (ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ) በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሚዛናዊ የሆኑ መረጃዎችን ለማቅረብ እንዲችል የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጅቱን አጠናቋል። ቀደም ብሎ ዕለታዊም ሆነ ተከታታይ መረጃዎችን ለመሥጠት የነበሩብንን ውስንነቶች በማስተካከል የተሻለ ለማገልገል ተነስተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለልጀ ደባልቄ ቢተው (ክፍል ኹለት)

ይድረስ ለልጀ ደባልቄ ቢተው

ዘጌርሳም

ይድረስ ለምንወድህና ለምትናፍቀን ልጃችን ደባልቄ ቢተው፤

እንዴት ከረምክ ልጀ? እኛማ ባለፈው ስናወጋ እመጣለሁ ባልከን መሠረት መምጣትኽን እየተጠባበቅን እንዳለን፤ ለአንተ ምኑን እነግርሃለሁ፤ በአሁኑ ወቅት ወሬውን ከእኛ ቀድማችሁ ስለምትሰሙት አገሩ ሁሉ ታምሶ የመንግሥት አልጋም ተናውጦ በመክረሙ ያገርህ ገበሬ በነቂስ ሞፈርና ቀንበሩን ሰቅሎ፤ ቤት ያፈራውን መሣሪያ እየወለወለ ዱር ገብቷል። እኛ ግን አቅምና ጉልበታችን ቤት ስለዋለ ትመጣ ይሆናል በማለት በር በሩን እያየን በናፍቆትህ እንደተሰቃየን አለን፤ የሊቦው ጊዮርጊስ የተመሰገነ ይኹንና እስካሁን የደረሰብን አንዳችም ክፉ ነገር የለም። እናትህ ግን ክስት ጥቁር እንዳለች በየደብሩ እየዞረች ያልተሳለችበት ታቦትና ያልቋጠረችለት የስለት ገንዘብ አይገኝም። ሌትና ቀን ዓይንህን እንዲያሳያት ያን የምታውቀውን የሊቦ ጊዮርጊስን አቀበትና ቁልቁለት ደከመኝ ሳትል ስትወጣ ስትወርድ ከረመች፤ ምን እሱ በቅቷት! ጣራ ገዳምና ዘንግ ሚካኤል ድረስ ሳይቀር ትመላለሳለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አፍሪካዊነትን የሚያስጠሉ ሦስት ወቅታዊ ክስተቶች

Yoweri Kaguta Museveni  (Ugandas president) & Omar Hassan Ahmad al-Bashir (former Sudanese president)

ነፃነት ዘለቀ

በዜና ስከታተላቸው ለጊዜው “ብው” ያልኩባቸውን መጥቀሴ እንጂ፤ አፍሪካዊ መሆን በተለይ ከቅርብ ዘመናት ወዲህ የሚያኮራ ወይም የሚመኙት ሆኖ አይደለም - ርዕሴን እንደዚያ የሰየምኩት። አፍሪካ በሚገርም ሁኔታ ዓለምን እያሳቀችና ጥቂት የማይባሉ ዜጎቿን እያሳቀቀች ትገኛለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ከዶ/ር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር

PM Abiy Ahmed and activist and journalist Eskinder Nega

ዲበኩሉ ቤተማርያም

ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ሌት ተቀን እየተንገበገብኩ አቅሜ በፈቀደልኝ መጠን በጋራ ከማደርገው ትግል በተጨማሪ በግሌም እየታገልኩ ባለኹበት የመከራ ወቅት፣ እርስዎ ድንገት ብቅ ብለው የነፃነት ብርሃን እያበሩ ሲመጡ፤ እልል ብለው ከተቀበልዎት መኻል አንዱ ኾንኩ። ሙሉ ድጋፌንና ክፍት ልቤንም ልሰጥዎ ተገደድኩ። ፈጣሪንም አመሰገንኩ፤ ዕድሜና ጤና እንዲሰጥዎትም ለመንኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለወንድሜ አባዊርቱ

PM Abiy Ahmed

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

አባዊርቱ ሰላምታየ ይድረስህ። አንተ ብል አትቀየምም ብዬ አስባለሁ። ጽሑፍህን ሁልጊዜ እከታተላለሁ። አንድ የሥርዓተ ነጥብ አጠቃቀምህን ላስታውስህ እልና እዘነጋዋለሁ። አሁን ግን ሳልረሳ እዚች ላይ ላስታውስህ ወደድኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለልጀ ደባልቄ ቢተው

Ploughing with cattle in southwestern Ethiopia.

ዘጌርሳም

የሰማዩን ርቀት፣ የምድሩን ስፋት፣ የባሕሩን ጥልቀት ያሕል ለጤናህ እንደ ምን ባጀህ? የሊቦው ጊዮርጊስ የተመሰገነ ይኹንና እኔም ሆንኹ እናትህ አለሙሽ ማንያዘዋል፣ ወንድሞችህ አንሙትና ይርጋ፤ እኅቶችህ ፍትፍቴና ዘርትሁን እንዲሁም እጎቶችህ ደብተራ ዋሴና መምህር መዝሙር፤ ሌላውም ዘመድ አዝማዱ በሙሉ ደኅና ነን። የአንተ ናፍቆት ግን እኔን ጤና ነስቶ እናትህንም ክስት ጥቁር አድርጓታል። ወንድሞችህም ትዳር መሥርተው ጨቅሎች አፍርተዋል፤ እኅትህ ፍትፍቴ ግን የብላታ ባይለየኝን ልጅ፣ ዳምጤን ልናጋባት ፍጥምጥም ተደርጎ፤ ማጫውም ተወስኖ፤ ቀን ተቆርጦ ድግሱ በመደገስ ላይ እንዳለ በውድቅት ሌሊት መንና ገዳም ገባችብን። እኛም የአባት እደሩን ካሣ ከፍለን ታረቅን። ዘርትሁን ግን ማለፊያ በለሴ የባለጠጋ ልጅ አግብታ ውባውብ ጉብሎች እድርሳልች፤ ለእኔና ለእናትህም የዓይን ማረፊያ ሆነውናል። ምኞትና ጠሎታችንም ይኽ ነበር። አንተም የአደባባይ ሰው ሆነኽ ለምድረ ሊቦ ዋስ ጠበቃ ትሆናለህ ብለን ስንመኝኽ፤ የጧት ግንባርህ ኾነና ዳር አገር ጥለኸን ጠፋኽ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ