በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመውን የሻርፕቪሌን ዕልቂት ማስታወሻ

Sharpeville Massacreፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

ደቡብ አፍሪካ እ.ኤ.አ. በ1960፣

እ.ኤ.አ መጋቢት 21/1960 ልክ ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት ወደ 5 ሺ የሚገመቱ ሰልፈኞች (እንደ አፓርታይድ ፖሊስ የተጋነነ መረጃ ከሆነ ደግሞ 20 ሺ ሰዎች) በደቡብ አፍሪካ በሻርፕቪሌ ከተማ በትራንስቫል ግዛት (በአሁኑ ጊዜ ከደቡብ አፍሪካ 9 ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው እና ጋውቴንግ እየተባለች በምትጠራው ግዛት) ፖሊስ ጣብያ ፊት ለፊት ተሰባሰቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኤርትራ ነገር፤ የኛ ችግር፤ መርህ አልባ ፍቅር

ተክለሚካኤል አበበ ሳሕለማርያም (ቶሮንቶ)

1- የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደዋሽንግተን ዲሲ መጥቶ ከኢሳት ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ተከትሎ፤ በመስከረም 2013 በጻፍኩት ጽሁፍ፡ በቃለምልልሱ ላይ አቶ ይሳያስ አፈወርቂን መስቀልና ማጋነን እንዳልነበረበት ተችቼ የሚከተለውን ጽፌ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኑሮ በአዲስ አበባ

Live in Addis. ኑሮ በአዲስ አበባ

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ - እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ሳውዲ የቀረው ገበሬ እንግልት

Raya Jemal. ራያ ጀማልየማለዳ ወግ

ነቢዩ ሲራክ

ወንድም ራያ ጀማል የ5 ወንድ እና የ3 ሴት ልጆች ጎልማሳ አባት ነው። ወደ ሳውዲ የመጣው ድህነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የፖለቲካው ሙቀት አልያም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ገፍቶት አይደለም። ሳውዲ የመጣው፣ የእስልምና እምነቱ በሚያዘው መሰረት በህይወት ዘመኑ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ከብቶቹን ሽጦ የሃጅ ጸሎት ለማድረግ ነበር ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ የ“ዲፕሎማቶች ቁንጮ” መሳለቅያ ቅጥፈት

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

የወባ ትንኝ ተመራማሪ የሆነ ሰው ስለዲፕሎማሲ ጥበብ እና ሳይንስ ምንድን ሊያውቅ ይችላል? ወይም ደግሞ እውነትን በመናገር እና ውሸትን በመናገር መካከል ያለው ልዩነት ምን ያውቃል? ወይም ደግሞ የለየለት ቅጥፈትን አምኖ በመቀበል እና ቅጥፈትን በማውገዝ መካከል ያለውን ልዩነት ምን ያውቃል? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ያለምክንያት አላነሰዋቸሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታሪክ መዛባቱ አያከራክረንም! ለመሆኑ ማን ነው ያዛባው?

Isaias Afewerki, ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ)

በቅርቡ ኤርትርያን የጎበኙት የኢሳት ጋዜጠኞች ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ብዞዎቻችንን እያነጋገረ ነው። እንደገና የሁለቱ አገራትና ሕዝቦች ዝምድናና የወደፊቱ እጣ ተጣማሪነት በተለያዩ ሚዲያዎች መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መጥቷል። ልክ እንደ በፊቱ እያወዛገበ ነው ማለቱ ሳይሻል አይቀረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምን አስተሳሰብ ይሆን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር?

TPLF, ወያኔ/የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ዶ/ር አበባ ፈቃደ

ጥንታዊት ቅድስት ኢትዮጵያ አገራችንን ከገጠማት ብሄራዊ ቀውስና ካንዣበበባት ሕልውናዋን ፈታኝ አደጋ ለመታደግ ምን መደረግ አለበት የሚለው ጥያቄ መመለስ ከመቸውም ግዜ በበለጠ የወቅቱ ዋናና አጣዳፊ ጉዳይ መሆኑ ለሚመለከተንና ለምንቆረቆር ሁሉ አጠያያቂ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከእስክንድር ናፍቆት እስከ አንድነት ዘመነ

አይዞህ ወንድም አለም ...

ነብዩ ሲራክ

... ምስላቸውን ተመልክቸ፣ ታሪካቸውን ሰምቸ ስሜቴን ካናወጡት ጥቂት ምስሎች መካከል ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቅምጥል ከታዳጊ ናፍቆት በቅርቡ አባቱን ከታሳሪዎች መካከል ሲያፈላልግ የተነሳው የፖለቲከኛው ዘመነ ምህረት ልጅ አንድነት ዘመነ ተናጋሪ ምስልን ከአገር ውስጥ ካየኋቸው ስሜት ኮርኳሪ ተናጋሪ ምስሎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርቲስቶቹ የህወሐት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ?

ኤልያስ (አዲስ አድማስ)

ሁሌም ምርጫ ሲደርስ ብቅ ብቅ የሚሉ (በኢቢሲ ማለቴ ነው!) ፊታቸው “የቁጣ አስተማሪ” የሚመስል አንዳንድ ግለሰቦች አላጋጠማችሁም? ፖለቲከኞች ወይም ባለሥልጣናት እንዳይመስሏችሁ። (እነሱ አይቆጡም አልወጣኝም!) እነዚህኞቹን “የምርጫ ዬኔታ” ይሏቸዋል፡፡ ይሄ ስያሜ ለምን እንደተሰጣቸው አላውቅም፡፡ ምናልባት ቁጣ ቁጣ ስለሚላቸው ይሆን? የሚገርመው ደግሞ እየተቆጡ የሚያስተምሩን እንዴት ምርጫውን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ---እንደምናደርገው ነው፡፡ (ሰላማዊ ምርጫ --- በቁጣ?!)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ