ለፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን እልፈት ማስታወሻ

Donald N. Levine. ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን፡ የልሂቃን ሁሉ ልሂቅ

ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን በዚህ ባሳለፍው ጥር ወር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የነበራቸው የረዥም ጊዜ ዕቅድ በህመማቸው ምክንያት የተጨናገፈ መሆኑን በኢሜይል መልዕክት ልከውልኝ ነበር። በዚያ አስበውት በነበረው ጉብኝት የሚከተሉትን ሶስት ዓላማዎች የማሳካት ዕቅድ ነበራቸው። እነርሱም፣

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምሥራች! የአንድ ዶሮ ዋጋ የዐርባ አምስት በሬ ዋጋ ሆነ!

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)

Doro. የአንድ ዶሮ ዋጋ የዐርባ አምስት በሬ ዋጋ ሆነ
ክርስቲያን አንባቢዎቼ እንኳን ለ2007 ዓ.ም. የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ። ሙስሊሞችና ሌሎችም እንኳን ለኛ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ለእናንተም በዓል(ላት) በሰላም እንዲያደርሰን የጋራ የሆነውን ፈጣሪን በጋራ እንለምነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ

Alemayehu Sentayehu (Zeleke Pola). አለማየሁ ስንታየሁ (ዘለቀ ፖላ)ክንፉ አሰፋ

እለተ እሁድ ከቀትር በሁዋላ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ቁጥሩ +251 945226530 ነበር። ስልኩን አነሳሁት።

"ሃሎ"

"አቤት"

"አለማየሁ ነኝ። መን አባክ ነው የምትጽፈው። እኔ አላማዬ ነው። አንተን ግን አንገትህን ቆርጬ ነው የማሳይህ። ለማየት ያብቃህ። ያን የምትጽፈውን ጽሁፍ... እኔ ምንም ልሁን ምን እንደዚህ አይደለሁም። እሺ። እናትክን ልብ... (ይህንን ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። ... ደግሞ ኢህአዴግ ዘርህን ይበ... (ይህንንም ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታሪክ ይፋረደናል!

አንዱዓለም ተፈራ
Atse Tewodros. አፄ ቴዎድሮስ

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ አገራችንን ሲጫወትባት፤ "እኛ የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!"፣ "እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!"፣ "እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!" እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን ተወጥሮ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በገንዘብ ዕጦት ምክንያት የተገደበ ግደብ?

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)
Sudanese President Omar al-Bashir, center, Egyptian President Abdel-Fattah el-Sissi, left, and Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, right, shake hands after signing an agreement on sharing water from the Nile River, in Khartoum, Sudan, Monday, March 23, 2015. Egypt, Ethiopia and Sudan on Monday signed an initial agreement on sharing water from the Nile River that runs through the three countries, as Ethiopia constructs a massive new dam it hopes will help alleviate its electricity shortages. El-Sissi, al-Bashir and Desalegn welcomed the agreement in speeches in Khartoum’s Republican Palace on Monday. (AP Photo/Abd Raouf) (The Associated Press)

ከላይ ለዚህ ትችት የተሰጠው ርዕስ እንደሚያመለክተው በአንድ በኩል በገንዘብ እጦት ችግር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት የተገደበ ወይም ደግሞ እንደ ጅብራ ተገትሮ የቀረ ግድብ የሚል ትርጉምን የሚይዝ ሲሆን፤ ሌላው ትርጉሙ ደግሞ ከፍተኛ በሆነ የገንዘብ እጦት ችግር ምክንያት የተመደበለትን ገንዘብ በማብቃቃት ለመስራት በማሰብ ደረጃቸውን ባልጠበቁ ግብዓቶች በመጠቀም ለርካሽ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል እንደምንም ተውገርግሮ የተሰራ ግድብ ብዙም ዘለቄታ ሳይኖረው በአንድ ወቅት አውዳሚ በሆነ መልኩ ተንዶና ተደርምሶ የህዝብ ሀብት እና ጉልበት መና ሆኖ ይቀራል የሚል ፍሬ ሀሳብን የያዘ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኤርትራ ነገር የኛ ጉዳይ፣ ትችትን በቅኝት

ሄኖክ የሺጥላ

ወዳጄ ልጅ ተክሌ የጻፈውን "የኤርትራ ነገር፣ የኛ ችግር፣ መርህ አልባ ፍቅር" የምትለዋን አየሁ። መስመር በመስመር ደግሜ ደጋግሜ አነበብኩ። ከዚያ ተመለሼ ወዳጄ መሳይ መኮንን በዳላስ ስለ ኤርትራ ቆይታው ያደረገውን ውይይት ተመለከትኩ፣ እኔ በነበርኩበት በሲያትል ላይ ስላደረገው ውይይትም ለማስታወስ ሞከርኩ፣ ከዚያ የፕሮፌሰር መስፍን ወለደማርያምን ጽሑፍ በድጋሚ አነበብኩ፣ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወቅታዊ መርህ ሊሆን የሚገባው ‹‹ያገባኛል›› ባይነት!

ኤልያስ ገብሩ

ኢ-ሰብዓዊነትን መቃወም በራስ ሲደርስ ብቻ አይደለም

ባለፈው ዓመት ‹‹ስለ ሀገር ያገባኛል›› የሚል አዲስ መንገድ በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ተጀምሮ ነበር፡፡ ይህ፣ በምንወዳት ሀገራችን ወቅቱ የሚጠይቀው ቃል ሲሆን ብዙዎች እውነተኛ መርህ አድርገው በተግባር ሊኖሩበት ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የት ሂዱ ነው?

Prof. Mesfin Woldemariamፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም (አዲስ አበባ)

ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላለን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞት ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዓሊ ቢራ የጥበብ ሥራዎች የኦሮሞ ሕዝብ ሀብት ብቻ ናቸው እንዴ?!

Ali Birra. ዓሊ ቢራ

ቋንቋዎቻችን የልዩነት፣ የጥላቻና የዘረኝነት ጽኑ ግምብ ሲሆኑብን!

ኒቆዲሞስ

የኃይማኖት ሊቃውንት በጥንት ዘመን ፍጥረት ሁሉ በአንድ ቋንቋ ይነጋገር እንደነበርና ቆይቶ ግን ይህ በአንድ ቋንቋ የመግባባት ጉዳይ ብዙም ሳይዘልቅ እንደተቋረጠ ያትታሉ። ምክንያቱን ሲያብራሩም ጥንታውያኑ ባቢሎናውያን ገናና ሥልጣኔያቸው ጫፍ በነካ ማግሥት ሰማይን የሚታከክና የፈጣሪን መኖሪያ፣ ክብሩንና ልዕልናውን የሚዳፈር ረጅምና ግዙፍ የሆነ ታላቅ ግምብ ለመገንባት ተነሱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ