የጎሳ ፌዴራሊዝም መርዝ በኢትዮጵያ

Ethnic Federalism Ethiopiaፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሀሰት እና የሸፍጥ የተውኔት መድረክ የተንጸባረቀበትን ህገመንግስት አርቅቆ እ.ኤ.አ ታህሳስ 8/1994 በማጽደቅ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጫነ። በህገ መንግስቱ ሰነድ የመጀመሪያ መግቢያ መንደርደሪያ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ሰፍሮ ይገኛል፣ "እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesusክንፉ አሰፋ

አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።

"ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ

ጴጥሮስ አሸናፊ

እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ

አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ እኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው? የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔን የእብሪት ወረራ እስከ መቼ እንሸከማለን?

ሊቁ እጅጉ

በዓለም ታሪክ ውስጥ አምባገነን ገዥዎች ለሥልጣናቸው የሚሰጡት ሕጋዊ ሽፋን ከሁሉም በላይ አዋቂዎች፣ ለሕዝብ ተቆርቋሪዎች፣ የድሆችን እንባ ጠባቂና … ወዘተ ስለሆነም እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ይሰይማሉ። አንዳንድ በአመጽ ሥልጣን ላይ የወጡ ቡድኖችና መሪዎች ብዙ ግዛቶችን በጭካኔ አጥቅተው ከያዙ በኋላ ሰው መሆናቸውን እስከመካድም ደርሰው ነበር። ሆኖም ግን መጨረሻቸው እነሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ውጤታቸው ታላቅ ውርደትና በሕዝብ ዘንድ መጠላትን፣ ውድቀትንና የሕዝብ እልቂትን ከማስከተልና የታሪክ አተላ ከመሆን አላመለጡም፣ አላለፉም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢትዮጵያ መብትን፣ ክብርን እና ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ሰነድ?

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

የእንግሊዝ ህዝብ መሰረታዊ ህገ መንግስት 800ኛ ዓመት በዓል በማክበር ላይ እገኛለሁ

እንዴት!?

አንዴ በጅ በሉኝ! ጥያቄአችሁን ተገንዝቤዋለሁ! በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ሀገር የሚኖር አንድ በአፍሪካ ያውም በኢትዮጵያ የተወለደ ሰው በመካከለኛው ዘመን ከ800 ዓመታት በፊት በእንግሊዝ ሀገር ያመፁ ባለጉልት ባላባቶችና በነጉሳቸው መካከል በተደረገው የስልጣንና የግል ጥቅም ትግልና ስምምነት ለምንድነው የሚያከብረው? ስለነሱ መብትና ነፃነት ምን ግድ አገባው?
ብላቸሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከጨርቁና ከቋንቋው በስተጀርባ

ይሄይስ አእምሮ (ከኢትዮጵያ)

ዛሬ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. የወያኔ 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል መዘምዘሚያ በወያኔው አባል በቱጃሩ አላሙዲን የሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ እየተከበረ ነው። ዘፈንና ደስታ አለቅጥ ሲበዛ የሚያስከትለውን ምልኪያዊ ሀዘን የተረዱ አይመስሉም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ

ክንፉ አሰፋ

"አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!" አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር -ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። "ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን" ሲሉ አሳቁን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአስራ አንደኛው ሰዓት - የህዝባዊነት ክትባት

አዜብ ጌታቸው

የአርቲስት ሜሮን ጌትነት “አትሂድ” የተሰኘው ግጥም ሌላውንም አርቲስት እያነቃቃ ነው። ግጥሙ መቼም የአመቱ ምርጥ ግጥም ነው ብል አካበድሽ! አልያም የጾታ አድልዎ ነው እንደማልባል ተስፋ አደርጋለሁ። ብባልም ግድ የለኝም። ለለውጥ ያህል “የሴት ትምክህተኝነት” ይጀመር መሰለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

‹‹በሀገራችን የነጻነት ጥያቄ ፊት ለፊት ፍጥጥ ብሎ መጥቷል›› ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

ኤሊያስ ገብሩ -ጋዜጠኛ

‹‹በዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋዜጠኝነትን ለመስራት ምን ያህል ተጠቀምንባቸው?!››ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
‹‹በሙያችን ለሀገራችን አበርክቶት መስጠት ይጠበቅብናል።›› ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
‹‹...ብዙዎቻችን የምንሻው ነጻነት የሚመጣው ጥቂቶች በሚከፍሉት ዋጋ ብቻ አይደለም››ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
ባሳለፍነው ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍቃዱ ማህተመወርቅ እና ሳሙኤል አበበ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር። ፍቃዱም ወደዞን አንድ፣ ሳሙኤል ወደዞን እኔ ደግሞ ወደዞን ሶስት ለጥየቃ ገባን። ከታሰሩ አንድ ዓመት ሊሞላቸው ያሉትን ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ እንዲሁም የዞን 9 ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀን አስጠራኋቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

አብርሃ ደስታን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል
‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፣ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡ እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ›› ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ