የዶርዜ ማርያም

 አስፋ ጫቦ

1. ዶርዜ ዴሬ (አገር) የዶርዜ ማርያም የለችም። ያሉ ሁለቱ አድባራት የጥንቱ፣ የጥዋቱ የዶርዜ ጊዮርጊስና የዶርዜ ሚካኤል ናቸው። ሚካኤል ከጨንቻ በልጅ እግር ከ30-45 ደቂቃ ቢወስድ ነው። በምን ሊከድ ኖሯል!? ልጅ ሆኜ አንድ ሁለቴ ሚካኤልን ለማንገስ መሔዴ ትዝ ይለኞል። ማንገሱ ሳይሆን የዶርዜ ዘፈኑ መስለኝ የሚጠራኝ። ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንትና ቲያትር አደራሽ እንደመግባት ይሰማኛል። አዳራሹ ሜዳው መሆኑ ነው። ዶርዜ ማርያም ብትኖርም እንኳ ዶርዜ ማራሞ ነው የምንለው። ታሪካዊዋንን የዜናሁ ለጋለ፤ የአባ ባሕርይ መጽሐፍ መፍለቂያ የብርብር ማርያም ደብረ ነች። ያችን እኛ ቢርቢራ ማራሞ እንላለን። ዚኒ ከማሁ፤ ኤሌ ጋብሬሌ፤ ዶርዜ ሚካሌ ነው የምንለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መዓት አውርድ!

ኣስራት ኣብርሃ

በዘመነ አፄ ልብነድንግል ጦርነት በመጥፋቱ ንጉሱ ጦርነት አውርድ ተብሎ በየቤተክርስቲያኑ ፀሎት እንዲደረግ ትዕዛዝ አውርዶ ነበር እየተባለ በአፈ ታሪከ ይነገርለታል፤ 24 ዓመት የሞላው የህወሀት/ኢህአዴግ ስርዓትም ጦርነት አውርድ፣ መዓት አውርድ እያለ እንደሚገኝ ከደርጊቶቹ ሁሉ መረዳት የሚቻል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

«የወያኔ ምስጢራዊ መረጃ፤ ጆሮ ያለው ይስማ»

ተክለሚካኤል አበበ

በርእሱ እንዳትሸወዱ

1-      ይሄ የኔ ርእስ አይደለም፡፡ የዛሬ 15 ቀን ተክለጊዮርጊስ በተባሉ (የብእር ይሁን የምር ስም አይታወቅም) ሰው የተጻፈን ስም አጥፊ ጽሁፍ የለጠፈው ኢትዮፍሪደም ድረገጽ ወይም የጽሁፉ ደራሲ፤ የአንባቢን ትኩረት ለመሳብ ይመስላል፤ የተጠቀሙበት የመግቢያ ሀይለቃል እንጂ፡፡ ጸሀፊው ለድረገጾች ያላቸውን ቅርበት በመጠቀም፤ እንዲሁም ወያኔ የተባለው ቃል ከተጠራ አንባቢ አያጣራም፤ ወይም ግለሰቡ ላይ ዘሎ ይረባረብበታል በሚልና፤ የስም ማጥፋቱ ሰለባ የሆኑት ሰው፤ ጨዋና እንዲህ ያለው እንከሰላንቲያ ውስጥ ገብተው አይመልሱም በሚል እሳቤ ይመስላል፤ ይሄንን ርእስ ተጠቅመዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት እና መኢአድ ነገር ቀላል አስቆዘመኝ እንዴ... ቁጭት እንደወረደ!

 ኣቤ ቶክቻው

በተለይ አንደነት ፓርቲ በበኩሌ ቀልቤን የሳበው ሲመሰረት ጀምሮ ነበር። ”የቅንጅት ህጋዊ እና ሞራላዊ ወራሾች ነን!” የምትለው ንግግር ዋዛ አልነበረችም። በብዙነታችን ውስጥ አንድነት የሚለው ሃሳብ ለሀገሬ መልካሙ መንገድ ነው ብዬ ስለማስብ ይሁን፣ የብርቱካን ሚዴቅሳ እና ፕሮፌሰር መስፍን ፖለቲካዊ ስብዕና ደስ ስለሚለኝ ይሁን፣ እነ አርአያን የመሳሰሉ ወዳጆቼ በዙሪያው ስለነበሩ ይሁን ብቻ በቅጡ ባለየሁት ሁኔታ በልቤ አንድነት ፓርቲ ክፉ ባይነካው ብዬ ስጸልይለት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መታረም የሚገባዉ ማነዉ?

ጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት ዓለሙ- (ከቃሊቲ እስር ቤት)

በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ። የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ። በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣ የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ባለቤት የሌለው መሬት – ቤጌምድር!

ዳዊት ከበደ ወየሳ

የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?)

በሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ “ገ’ጨው” በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል፡፡ ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱ አሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል፡፡ የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት – አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው – በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል-አቀባይ ኢሳት ወይስ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት? [ኤሊያስ ገብሩ-ጋዜጠኛ]

ኤሊያስ ገብሩ-ጋዜጠኛ

ወሳኝ ሀገራዊ መረጃዎችን ከመንግሥት መጠበቅ የለብንም ይሆን?

በእያንዳንዱ ሀገር ያለ ገዥ መንግሥት የየራሱ መረጃ ለህዝቡና ለዓለም-ዓቀፍ ማኅበረሰብ የመስጠት ባህሪ፣ ልምድና ባህል አለው። ወሳኝ የሆኑ ሀገራዊ፣ መንግሥታዊና ኅብረተሰባዊ መረጃዎች በሚመለከታቸው የመንግሥታት የመረጃ ሰጪ አካላት በኩል መረጃው ለሚያስፈልገው ሁሉ መድረስ እንደሚያሻ እሙን ነው – በተለይ በዘመነ ግሎባላይዜሽን እና በ21ኛው ክ/ዘመን! ኢትዮጵያን በተለያዩ ጊዜያት ያስተዳደሩ መንግሥታት ‹‹እየመራነው ነው፤ እያስተዳደርነው እንገኛለን›› ለሚሉት ሕዝብ መረጃን የሚሰጡበት የየራሳቸው አካሄድ ነበራቸው። በአሁን ወቅት ሀገራችንን እያስተዳደረ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ነውና በእሱ ላይ ማተኮር ተገቢ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምክር እስከመቃብር – ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ (በእውቀቱ ሥዩም)

በእውቀቱ ሥዩም

የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው። ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው።እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ። ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ። የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ። ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ። በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ። ባሩድ ኣገነፋለሁ። የታንክ ጎማ እነፋለሁ። በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ“ምርጫ” ወግ እና የውይይት ማስታወቂያ

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ - ካናዳ)

1-      የዚህ ጽሁፍ ዓላማ፤ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች፤ አሁድ ድሴምበር 28 ቀን ከሰአት በኋላ 2pm ላይ፤ በውጭ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ያዘጋጁትን የስልክ ውይይት ማስተዋወቅ ነው። ይሁን እንጂ ማስታወቂያውን እርቃኑን ባሰፍረው፤ አይማርክም በሚል፤ አንዳንድ ተያያዥ ነገሮችን ላለብሰው ፈቀድኩ። መለመላውን ከሚቀርብ የስልክ ጉባኤ ማስታወቂያ ይልቅ፤ ትንሽ ውዝግብ የለበሰ ማስታወቂያ ቀልብ ይስባል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ

በላይ ማናዬ

∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል

∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው

ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ