ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡

ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”

በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት?

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቶሮንቶና የነቀምት ግንባር፤

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ)

የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤

1-       “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች ከቀበናው የአንድነት ጽ/ቤት ይነሳሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለፍትሕ ሲባል፤ ሥርዓቱ ይፍረስ! (ሊያነቡት የሚገባ!)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው?

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ… በጨለመው የሳውዲ ወህኒም ይነጋል…

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ

ግፍ ከበዛበት ወህኒ የአክብሮት ስላምታየ ይድረሳችሁ!

እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍታ ያህል እድሉን አግኝቸ ወህኒ የመውረዴን እውነታ ላስረዳችሁ ግድ አለኝ ። ዛሬ አስረግጨ የምነግራችሁ ወህኒ የመውረዴ ምክንያት ሚስጥር ግምሽ እድሜየን ህግና ስርአቷን አክበሬ የኖርኩባትን የሳውዲት አረቢያን ህግ ተላልፊ አይደለም ! የስደተኛው ጉዳይ ያገባኛል በሚል የማቀርበው መረጃ ቅበላየ የማይመቻቸው ፣ ያመማቸው ከተሴረውና እየተሴረ ካለው እገታ ጀርባ ስለመኖራቸው አልጠራጠርም ። … ዛሬ በዚህ ዙሪያ ብዙ አልልም!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት” በሁለት ሺህ አስራ አራቷ ኢትዮጵያ እይታ ሲገመገም

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም;- በነጻነት ለሀገሬ

ታላቅወንድም በአንክሮ እየተመለከቷችሁ ነው! በሚስጥር፡ የሚንሾካሾከው ወሮበላ መንግስት 2014ኢትዮጵያ 

በኢትዮጵያ ያለው ሚስጥር አነፍናፊው ገዥ አካል በጉአዳ ውስጥ የተደበቁ የኢትዮጵያውያንን/ትን ሚስጥሮች መርምሮ ለማውጣት በጣም ውድ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠቀም የስለላ ፕሮግራሞችን በመተግበር በታላቅ ፍርሀት ውስጥ ተዘፍቆ በመንፈራገጥ ላይ ይገኛል፡፡ ከፍርሀታቸው የተነሳ ህዝቡ በእነርሱ ላይ ምን ለማድረግ እንደሚችል ስጋት ውስጥ በመውደቅ እራሳቸውን በማስጨነቅ እንቅልፍ አጥተው ሲባንኑ ያድራሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሱዳን ያሉ ስደተኞች በምጥ ቀጠና ውስጥ… (በግሩም ተ/ሀይማኖት)

   ሰሞኑን ሱዳንም እንደ ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊያኖችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ደፋ ቀና እያለች ነው የሚል ወሬ ተናፍሶ ብዙዎች ምጥ በቁናን አስበው እህህህህን እያቀነቀኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ተስማምቷል፡፡ (ደህና ነገር አዘጋጅቶ ረግጠው የወጡ ይመስል ለማስመለሱ ፍጥነቱ ይገርማል፡፡ ከሰዑዲ ተመላሾች ምን ተደረገላቸው?) ታዲያ ሲስማማ የዜጎቹን መብት ለማስጠበቅ ቅንጣት ያህል እንደማይደራደር የብዙዎች ፍርሃት ነው፡፡ አሁን የስደተኛው ፍርሃቱ እውን ሆኗል፡፡ ይፋም ተደርጓል፡፡ ኢህአዴግ ዳግም ሊሳሳት የማይገባው በሳዑዲ አረቢያ እንደተደረገው ዜጎቻችንን በአደባባይ መጨፍጨፍ እና ማሰቃየት እንዳይከሰት ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ ቢሆንም ተቃዋሚ የሚባሉ በችግር ከሀገር የወጡ ስደተኞችና ኢህዴግን የማይደግፉ ግን እንኳን ወደ ሀገር መመለሱ እየተደረገ አይደለም አሁንም ጉሸማና እስር እንዳልቀረላቸው ይነገራል፡፡
 
 
    በዚህ ዙሪያ ሱዳን ያሉ ወዳጆቼን ለማናገር ሞክሬ ነበር፡፡ ሁሉም ፍርሃት የሸበባው በመሆኑ ችግሩን ገልጸው ለመናገር ያልደፈሩ መሆናቸው ያመሳስላቸዋል፡፡ ፍርሃታቸውን ሳይ ገዢው ፓርቲ በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ብገነዘብም ስደት ተወጥቶም መፈራቱ አሳዝኖኛል፡፡ በሀገር አላኖር፣ በሰው ሀገርም አላኖር ማለቱም ይገርማል፡፡ መግረም ብቻም አይደለም ይሄ ትውልድ የለበሰውን የፍርሃት ሸማ የሚያወልቀው መቼ ነው ያሰኛል፡፡ በሌላ በኩል ያናገርኳቸው ሁሉ የሚስማሙበት አንድ ነገር አለ፡፡ ወደ ሀገር መመለሱ ብቻ ሳይሆን አሁንም ኢትዮጵያዊያን ላይ እየተደረገ ያለው ግፍ ማነው ሀይ የሚለው? ዋነኛ ጥያቄያቸው ሲሆን መታሰር እና መደብደብ፣ እንግልት እንዲቆም እና በሰላማዊ መንገድ ወደ ሀገር መመለሱ እንዲከናወን ይመኛሉ፡፡ ወደ ሀገር መመለሱ ሳይታሰብ ጀምሮ ኢትዮጵያዊያን የሚሰቃዩበት ሁኔታ እንዳለ ነው አሁንም የሚናገሩት፡፡ የፍርሃታቸው ምንጭም ይሄው እስር እና እንግልት ይመስለኛል፡፡
 
 
   በፊትም ቢሆን ሱዳን ውስጥ የኢህአዴግ ካድሬዎች የፈለጋቸውን ማድረግ እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች ከሀገር ውጭ እንደልብ ከሚንቀሳቀሱባቸው ሀገሮች ዋነኛዋ ሱዳን ናት፡፡ አሁን ደግሞ እንኳን ዘንቦብሽ እንዲሁም…እንዲሉ ተቃዋሚ ሀይሎች እንቅስቃሴ ከጀመሩ ጀምሮ ሱዳን ከለላ፣ መሸጋገሪያ እንዳትሰጥ ያልተደረገ አይነት ጥረት የለም፡፡ እንዲያውም ድንበር አካባቢ ያለው መሬት ተቆርጦ የተሰጠበው በአባይ ግድብ ድጋፍ ለማግኘትና ለተቃዋሚዎች መንቀሳቀሻ መሬት እንዳትፈቅድ እጅ መንሻም ለማድረግ ነው የሚሉ ፍንጮች አሉ፡፡ የሆነው ሆኖ ሲዳን ውስጥ በየቦታው የወያኔ ጭፍራዎች፣ ካድሬዎች ስደተኛውን አላኖር ብለዋል፡፡ ስደተኛውን የመከታተላቸው ሂደት UNHCR ቢሮ ድረስ ዘልቆ የገባ በመሆኑ ከቢሮው የሚሰጠውን የስደተኛነት ማረጋገጫ /Mandate/ በአመት መታደሱ ቀርቶ በየስድስት ወሩ እንዲታደስ በማድረግ ስደተኛውን ለመቆጣጠር እንዲያመቻቸው  አድርገዋል ብለው ቅሬታ የሚያቀርቡ ልጆች አጋጥመውኛል፡፡
    
 
  በርካታ ኢትዮጵያኖች በየቀኑ እየታሰሩ እንደሆነም የገለጹልኝ ልጆች አሉ፡፡ እስር ቤት ለገቡት የሚያያቸው ወይም የሚከራከርላቸው የለም፡፡ እምዱርማ የሚባል እሰር ቤት አለ፡፡ እዚህ እስር ቤት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያኖች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ የምግብ ችግር አለ፣  እንኳን መብታቸውን መጠየቅ ይቅርና ሄደህ ለማናገር አትችልም፡፡ ወደዛ መሄድ ራሱ አስፈሪ ስለሆነ ማንም ደፍሮ ሄዶ ሊያይ አይቻልም…ብቻ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንኳን አስቸጋሪ ነው ብለውኛል፡፡ እግዚአብሄር ስደተኛ ወገኖቻችን ከሚደርሰው…ከፈሩት ስቃይ አንተ ጠብቅልን፡፡
 
 
     በኤምባሲውም ምንም ተስፋ እንደሌላቸው ሲገልጹልኝ…‹‹ኤምባሲው ስራው ለዜጎች የሚጠቅም ሆኖ አይተነብ አናውቅም፡፡ ከትግራይ ክልል የሚመጡ ራሳቸውን ትግራይ ባንድ ብለው የሰየሙ አርቲስቶች አሉ፡፡ ሙዚቃ ዝግጅት ያደርጋሉ ማታ ማታ ማስጨፈር ነው፡፡ የኢህአዴግ አባል ካልሆንክ ምንም ችግር ቢደርስብህ የሚደርስልህ የለም፡፡ አባል ለመሆን ብር ክፈል ትባላለህ፡፡ መታወቂያ ትይዛለህ፣ የአማራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የደቡብ…ልማት ማህበር አባል ለመሆን ነው ይሄ ሁሉ….ምዝገባ ክፍያ…መንግስት  ነኝ ብለው ስልጣን ላይ የተፈናጠጡት ሰዎች መቼ ይሆን ከዜጋቸው መብት ይልቅ ገንዘብ ማስቀደም የሚተዉት? መቼ ይሆን እንብላው እንብላው…ገንዘብ አምጡ አምጡን የሚተዉት? አሁንማ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደድሮው ፌደራል ፖሊስ መጣ ሲባል ሳይሆን የሚፈራው ለዚህ ነገር መዋጮ ሆኗል ፍርሃቱ…
 
                    ቸር ያሰማን እሰኪ…   
 

የማሕበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት (ሊያነቡት የሚገባ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ማሕበረ-ወያኔ

በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ቢደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል። የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እውነተኛው አ.ኢ.ግ.ተ. (EITI) ወይስ የማዳም ክላሬ የሙስና ማጋበሻ ቡድን?

ከፕሮፌሰር አለማየሁገ ብረማርያም

ትርጉም - በነጻነት ለሀገሬ

ማዳም ክላሬ አሸንፈዋል! እንኳን ደስ ያለዎት፣ ማዳም ክላሬ!

ባለፈው ሳምንት የ አምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀ መንበር የሆኑት ማዳም ክላሬ ሾርት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና በማስፈራራት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሙስና ማጋበሻ ቡድናቸው አባል እንዲሆን ለማስቻል የEITI የቦርድ አባላት ድምጻቸውን እንዲሰጡ በማድረጉ ጥረት ሲያካሂዱት የቆዩት ዥዋዥዌ ጨዋታ ተሳክቶላቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ