"ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም" ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
"ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም" ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (ሙሉውን ቃለምልልስ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)
"ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም" ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (ሙሉውን ቃለምልልስ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)
ከጸጋዬ ገ.መድኅን አርአያ
በአጤ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት (በ1960 አካባቢ) ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ የዕለታዊው ኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ አማካሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። እኛም እንጠረጥረው እንደነበረ ሁሉ የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሠራተኛ (ኮንታክት ማን) ነው። (እግዜሩ ይይላቸውና ለካ በእኛም መሐል ሰዋቸውን ይተክሉ ነበር) ኤድ መሪ የሥነ ጽሑፍ ሰው ስለሆነ በማስታወቂያ ሚኒስቴር “ተረፈ ዜና” የምንለውን - የማይታተመውንና የማይታወጀውን (በራዲዮና በቴሌቪዥን) በንጥረ ነገሩ መውሰጃ ሥፍራ የተነፈስነውን ሁሉ ሰብስቦ ካገጣጠመው በኋላ ወደ አሜሪካ ሲመለስ Kulubi የሚል መጽሐፍ አወጣ። እንግዲህ ተረፈ ዜና የገባችሁ ይመስልኛል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም) ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ ደርሷል። ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል። በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ እንዳላልኩ ልብ ይሏል። ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣ በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው።
በፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም፦ በነጻነትለሀገሬ
ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
… በማስመሰል ታጥሮ መሆን በጠፋበት
ምን አገባኝ የሚል በተከማቸበት
የባይተዋር መንፈስ ከሞላ ባገሩ
ዘመኑን ማወቂያ ይሄ ነው ሚስጥሩ
ይሄን ጊዜ ጠርጥር እንደጠፋ ዘሩ።
(ገጣሚ ደምሰው መርሻ/ያልታተመ)
አዎን፣ ገጣሚ ደምሰው እንዳለው እኔም በዚህ ዘመን “ዘሩ እንደጠፋ” አሊያም ሊጠፋ እንደተቃረበ እጠረጥራለሁ፡፡ ስለምን? ቢሉ …በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና።
ከጸጋዬ ገ.መ. አርአያ
“ነፃነቴን ካልሰጣችሁኝ ሞትን እመርጣለሁ”
Give me Liberty or Give me Death – Patrick Henry
ፍሬደሪክ ዳግላስ (1818- 1895) ከባርያ እናትና ከነጭ አባት የተወለደና ራሱም ቢሆን በቦልቲሞር (ሜሪላንድ) የቤት አሽከር ሆኖ የቆየ ሰው ነበር። አንድ ማለዳ ጁላይ 4 ቀን 1852 ን ተንተርሶ (አንተርሶ) በሮቼስተር ከተማ (ኒውዮርክ) ንግግር እንዲያደርግ ጥሪ ይደርሰዋል። ደብዳቤው ሲደርሰው እንደ እብድ ከራሱ ጋር መነጋገር ያዘ። መቸም አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ለማመን የሚከብድ አጋጣሚ ሲመጣብህ ናላህ ይበጠበጣል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም
ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡንአወርድብላየብብቷንጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)
ነገሩ የሆነው አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከአዋሳ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)
አባ መላ ማን ነው?
በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...(ተመስገን ደሳለኝ)
በ2004 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን በታተመችው ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ፣ ‹‹የፈራ ይመለስ!›› በሚል ተመሳሳይ ርዕስ፣ ከሰላማዊ አብዮት ውጪ አማራጭ ካለመኖሩም ባለፈ፣ ኢህአዴግ ቢያንስ ሕገ-መንግስታዊ ጥበቃ ላላቸው ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት አቅምም ፍላጎትም እንደሌለው ለመሞገት ሞክሬ ነበር፡፡ ግና፣ አገዛዙ ለእንዲህ ያሉ ግዴታዎች የተዘጋጀ ባለመሆኑ ከማድመጥ-መዳ--መጥን፤ ከመመከር-መከራን፤ ከማሰብ-ቃሊቲ መሰብሰብን፤ ከመሻሻል-ከሀገር ማሸሽን፤ ከማመን-መርገጥን… በመምረጡ፤ ዛሬም ድረስ ነፃነት ናፋቂው ዘመነኛ ትውልድ፣ በፀጥታ አርምሞ ወደተዋጡት አደባባዮች ከማማተር ያለፈ አማራጭ እንዳያገኝ ገፊ-ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል፡፡