የአድዋ ድልና የአሉላ አባ ነጋ ጠላቶች

ከአንተነህ መርዕድ

እነሆ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ኩራት የሆነውን የአድዋን ድል 118ኛ ዓመት ልናከብር ተዘጋጅተናል። ይህንን ታላቅ ቀን ባንድ ትንሽ ማስታወሻ ብዙ ማለት ባይቻልም ለድሉ አስተዋጾ ካደረጉት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አሉላል ላነሳ ፈለግሁ። አሉላ አባ ነጋ ትግራይ ውስጥ በተንቤን አውራጃ መናዌ በምትባል መንደር እንግዳ ቁቤ ከተባሉ ገበሬ ነው የተወለዱት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አያስቅም! አጭር ወግ

ክንፉ አሰፋ

በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ  የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን ምግብ ቤት ያጨናንቋት ነበር። ቁምራን የማታውቁ ካላችሁ፤ ለጽድቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ጾም እንዳይመስላችሁ። እድገ ትና ትራንስፎርሜሽኑ ያመጣው አዲስ ክስተት ነው - ቁርስ ምሳና ራት በአንድ ጊዜ የመመገብ ዘዴ። «ኑሮ በዘዴ ፣ ጾም በኩዳዴ» ይባል ነበር። ይህ አባባል አሁን መኖ በዘዴ በሚል ተቀይሯል። መቼም ሁሉም ነገር በነበር እየቀረ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብልሁ ፓይለት!

ከግርማ አንድሪያስ (ኔዘርላንድ -ኣምስተርዳም)

''...ልብ በሉ ልጆች የምነግራችሁን ኣድምጡ። ችሎታችሁ ምንም ጥርጥር የለውም። መሮጥ ከጀመራችሁ - ካልጨረሳችሁ አንደማታቆሙ ኣውቃለሁ። የምትሮጡት አንደባለፈው ጃፓን -ቶኪዮ ላይ ኣይደለም። ኣይደለም።  የኣሁኑውድድራችሁ ጣሊያን ጣሊያን ጣሊያን ጣሊያን ሮም ነው። ነው። ነው። ጣሊያኖች ችሎታችሁን ስለማይችሉት ሊተኖኮሎኣችሁ ይችላሉ።  በውድድር ላይ ሆናችሁ ቢመቱዋችሁ አንኩዋን መልስ ኣትስጡ። ለማዘናጋት ለማሰናከልና ስህተት አንድትሰሩ ስለሚፈልጉ  የሚጠቀሙበት ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ነውና ነውና ነውና ኣደራ ኣደራ ኣደራ !... ይድነቃቸው ተሰማ ነበሩ። ነበሩ። አነ ኣበበ ቢቂላን ወደ ሮም ለሩጫ ከመውሰዳቸው በፊት  በዝግጅት ላይ የተናገሩት።  (ድሮ መጽሔት ላይ ቃል በቃል ባይሆንም በግርድፉያስታወስኩትን ያሰፈርኩት ነው።)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኛና “እነርሱ”!

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡ በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡ በፍጥነት ገብተን ቦታችንን ያዝን፡፡ ሊቀ-መናብርቱም ቦታቸውን ያዙ፡፡ ‹ዛሬ ስለወሰድነው እርምጃ ለጦር አዛዦች ማሳወቁ ይበጃል በማለት ጠርተናቸው እዚሁ ይገኛሉ› ብለው ወደ አጃቢዎቻቸው ፊታቸውን ዘወር አድርገው ‹አስገቧቸው!› የሚል ትዕዛዝ ሻለቃ መንግስቱ ሰጡ፡፡ ጄነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ጄነራል ግዛው በላይነህ፣ ጄነራል ታደሰ ገብሬ፣ ጄነራል ወርቁ መኮንን ተከታትለው ገቡ…››

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቦይንግ 767 - እገታ እና እንድምታው

ክንፉ አሰፋ
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፈረደበትስ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ግንቦት 7 እና የኤርትራ መንግስት አይደሉም!

ለአቶ ተክለሚካኤል አበበ፤ ጥያቄዎች ምላሽ ቢሆን

ያሬድ ኃይለማርያም
በመጀመሪያ በአቅርቡ በተከታታይ ለአንባቢያን ያቀረብኩዋቸውን ሁለት ጽሁፎች አንብበህና ጊዜህንም ወስደህ በዝርዝር ላቀረብከው የሙግት ሃሳብ ምስጋናዮ የላቀ ነው። ለነገሩ የጽሑፌም ዋና አላማ ጉዳዩን ሕዝብ እንዲያውቀው ብቻ ሳይሆን በተነሱት ነጥቦችም ዙሪያ በአንባቢዎች ዘንድ የውይይት ሃሳብንም በማጫር ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝም ጭምር ስለሆነ ያንተ ምላሽ እኔንም በዚሁ ጉዳይ ላይ በድጋሚ እንድመለስበት አድርጎኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአባይ ግድብና የአገዛዙ ተቃርኖዎች (ቴዎድሮስ ጌታቸው)

ቴዎድሮስ ጌታቸው Tewodros Getachewቴዎድሮስ ጌታቸው (ከኦስሎ - ኖርዌይ)
በዓለም የወንዞች ታሪክ እንደ አባይ የተዘፈነለት፤ የተዘመረለት ወንዝ ያለ መቸም አይመስለኝም በዓለም በረዥምነቱ የሚስተካከለው የሌለው አባይ በትውልድ ሃገሩ ከዘፈን ግጥምና ከእንጉርጉሮ አድማቂነት ያለፈ ጥቅም ሳይሰጥ ለዘመናት ያለማቋረጥ መፍሰሱ እርግጥ ነው። ከወቀሳ እስከ ሙገሳ ከቁጭት እስከ ብስጭት ብዙ ብዙ ተብሎለታል ለአባይ ያልዘፈነ ዘፋኝ፣ ያልገጠመ ገጣሚ፣ ያልተቀኘ ባለቅኔ ማግኝት ይከብዳል፤ እናም አባይ ለቁጥር የሚታክቱ የሥነጥበብ ጉዳዮችን አስተናግዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ለምን ይሸበራል? (ዳዊት መላኩ)

ዳዊት መላኩ (ከጀርመን)
አባቶች ሲተርቱ ''ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም'' ይላሉ። ዝላዬን ተከትሎ ምን እንደሚመጣ ስለሚያውቅ በዝላይ አይሳተፍም ዝላይም አይወድም። የወያኔ አንባገነን መንግሥት ለምን ይሸበራል? ብለን ስንጠይቅ መልሱ ቀላል ነው። ከባዱ እና አስካሁን ብዙ በሥልጣን እንዲቆይ ያስቻለው ግን በመፍትሄው ላይ በጋራ መሥራት አለመቻላችን ነው። ወያኔ የሚሸበረው የህዝብን ሀብት ስለሚዘርፍ፤ ህዝብን ስለሚገድል፤ ህዝብን የሚጎዳ ሥራ ስለሚሰራ፤ የገንዛ ሥራው ነው ጥላ እየተከተለ እንደሸበር የሚያደርገው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቁጥር ጨዋታ?!

ጽዮን ግርማ

ሕፃን እዮሲያስ የጓደኛዬ ልጅ ነው። በሰባት ዓመቱ ሁለተኛ ክፍል ገብቷል። ፈጣንና መጠየቅ የሚወድ ታዳጊ ነው። ባገኘኝ ቁጥር በጥያቄ ልቤን ጥፍት ያደርገዋል። አብዛኛው ጥያቄዎቹ ትምሕርት ቤት ከጓደኞቹ ጋራ ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚመነጩ ናቸው። ባለፈው ሰሞን እንዲህ ብሎ በእንቆቅልሽ መልክ ጠየቀኝ። ለእኔም አጠያየቁ ልጅነቴን ስላስታወሰኝ በትዝታ ፈገግታ ታጅቤ “ምናውቅልህ” አልኩት። ”እ … ቢሄዱ፣ ቢሄዱ የማይሰለቻቸው?” አለኝ። ጥያቄውን እኔ ከለመድኩት የልጅነት የእንቆቅልሽ መልስ ጋራ ለማዛመድ የዱር አልቀረኝ የቤት መንገድ አይሰለቻቸውም ስል ያሰብኳቸውን እንስሳት ማሰላሰል ቀጠልኩ። የመሰሉኝንም ስማቸውን ደረደርኩለት፤ አልተሳካልኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፈረደበት ግንቦት 7፤ የፈረደባት ኤርትራ

ለአቶ ያሬድ ኃ/ማርያም አንዳንድ መልሶች

ተከልሚካኤል አበበ - ቶሮንቶ
እንደመግቢያ፤ ያሬድና ጽሁፉ
1- አቶ ያሬድ ኃይለማርም (ያሬዶ) ለሰብአዊ መብት መሟገት አመል ሆኖበት (አመሉ፤ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ማለቴ ነው)፤ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ ጽሁፍ አውጥቶ ነበር። ያንን ጽሁፍ ተከትሎ አንዳንድ በብእር ስም ጀርባ የተደበቁ ተቺዎች አበሳጩት መሰለኝ ሌላ ተከታይ ሁለተኛ ጽሁፉም ጽፎዋል። የኔ አስተያየት በመጀመሪያው ጽሁፍ ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ