ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ

መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር)

ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያን ከቅርጫ ለማትረፍ

ኢትዮጵያን ከቅርጫ ለማትረፍ ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፤ ነጻነት ለሀገሬ)

የአሁኑ አስገራሚ ጊዜ ሸክስፒር፣ ጁሊየስ ቄሳር በሚለው ፅሁፉ ላይ ለተናገረው አነጋገር ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል፣ "ሰዎች የሰሩት ተንኮል ከመቃበራቸው በላይ ሀያው ሆኖ ይኖራል" ብሎ ነበር ሸክስፒር። በአሁኑ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ከሰሩት ተንኮሎችና ጭራቃዊነት የሞላው አስቀያሚ ተግባር ውርስ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠን እንገኛለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ = የነፃው ፕሬስ ፀር

ቅዱስ ዩሃንስ

ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጦሰኛው የዐይን ኩልና መሬት ቅርምት በኢትዮጵያ

ይሄይስ አእምሮ

እንደመነሻ - በዚህች ቅጽበት በኢቲቪ እየተላለፈ የሚገኘውን አንድ የእንግሊዝኛ ፕሮግራም ብትመለከቱ አዲስ አበባን የምታውቋት በጣም ልትገረሙ ትችላላችሁ። ወጣቷ ሴት ጋዜጠኛ ለፈረንጆችና አዲስ አበባን ከእግር እስከራሷ ለማያውቋት ቄንጠኛ የኢትዮጵያ ወይም የሌላው ዓለም ዜጎች ስለዚህችው ገሃነም ከተማ ቆንጆ ምስል ለመፍጠር እየቃተተች ስሰማት ሚስቴ እስክትታዘበኝ ድረስ ከንፈሬን ጠመም በማድረግ አሽሟጠጥኳት፤ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ባህር ዳር፣ አድዋ እና አዲስ አበባ

በባህር ዳር ሰልፍ በአድዋና አዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል ዝግጅቶች ይኖራሉ
አማኑኤል ዘሰላም

የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጉራማይሌ ፖለቲካ!

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሌንጮ ለታ - ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ...?

ክንፉ አሰፋ

ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። "ወጣ ብለው ይግፉ።" ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። "ይግዙ" ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል። የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ "እኔን ነው?" የሚለው ወዶ ይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማንነት

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ጽሑፌ ውስጥ ‹‹ማንነት ምንድን ነው፤ በሚል ንዑስ ርእስ ስር ከገጽ 98 ጀምሮ በተቻለኝ መጠን አፍታትቻለሁ፤ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ይህንን ለማንበብ ጊዜ አላገኘም፤ ወይም የተገለጠለት ዱሽ ቅንጫቢ በቅቶት ይሆናል፤ የምጠቅሰውም ለሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሁንስ በዛ!

አንዱዓለም ተፈራ
በተደጋጋሚ ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማችሁ፤ አሁንስ በዛ! ማለታችሁ አይቀርም። እኔም ይኼው ዕጣ አጋጠመኝ። ታዲያ ዝም ማለቱ ወንጀል ሆነብኝና ይኼን ጻፍኩ። እንዲህ ነው የሆነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፤ ላለንብት የፖለቲካ ምስቅልቅል፤ መፍትሔ ፈላጊዎች የሩጫ ፊታቸውን ወደ ታሪክ አዙረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ