የጤፍ ምርትን ለውጭ ገበያ ይቁም ሊባል የሚገባ

አሰግድ ኣረጋ (ኮለምበስ - ኦሃዮ)
ጤፍ Teff. Photo by Peter Bregg

ሰሞኑን ስለጤፍ ምርታችን የባዕዳኑ ብዙኀን መገናኛ አጀብ እያሉን ነው፤ ለዘመናት የተደበቀው የዘሩ ገመና መጋለጡን እየነገሩን ነው፤ ስለያዘው ንጥረ ነገር፣ ስለጤናማነቱ፣ በምዕራቡ ገበያ ስለመፈለጉ፣ ከሁለም በላይ ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭነቱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እየተንፏቀቀ የመጣው ረሃብ በኢትዮጵያ

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al-Mariamፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም - ነጻነት ለሀገሬ)

ፈረሰኛው ረሃብ ኢትዮጵያ ላይ አያነጣጠረ ነው!
ባለፈው ሳምንት ኤንቢሲ/NBC የተባለው የዜና ወኪል በኢትዮጵያ እየተንፏቀቀ በመጣው ረኃብ ላይ ያደረገውን ጥናታዊ ዘገባ ዋቢ በማድረግ በማርቲን ጌይስለር አማካይነት ከዚህ በታች የተመለከተውን ሀተታ ለአየር አብቅቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አለምነው መኮንን - ኃላፊነት የጎደለው ኃላፊ

ነጋ ዓለማየሁ

ሰሞኑን የአማራ ክልል ባለሥልጣን ናቸው የተባሉ ሰው በአማራው ሕዝብ ላይ የጅምላ ስድብ ሲሳደቡ ተደምጠዋል። ሰውየውን ስሙንም ሰምቼው አላውቅም። እንዲህ አይነቱን ሰው አንቱ ማለትም የሚገባ አልመሰለኝም። ሀገሪቱን የሚመራው መንግሥት ከየት አምጥቶ እንዳስቀመጠው እራሱ ነው የሚያውቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራች በሳውዲው ስደት

አስገራሚው የሳውዲው "ኮራጅ " አባት ምክር

ነቢዩ ሲራክ
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ከ20 ዓመት በፊት ሳውዲው ወጣት ራሱን ለሁለተኛ ደረጃ ፈተና ከማዘጋጀት ይልቅ በረቀቀ መንገድ ለፈተናው መልስ የሚሆነውን ማጭበርበሪያ የመልስ ወረቀት አዘጋጅቶ ለፈተና ይቀርባል። ፈተናውን በረቀቀ መንገድ አጭበረብሮ ሰርቶታልና ፈተናውን በተገቢ ውጤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለማለፍ በቃ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳት ገለልተኛ ይሆን ዘንድ እንደገና ይዋቀር

አማኑኤል ዘሰላም

"ስልክ ጠላፊው ሰላይ 'ጋዜጠኛ'" የሚል አንድ ጽሁፍ አነበብኩ። ሲያትል የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ናቸው የጻፉት። የአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን አጠንክረው ይተቻሉ። በቅርቡ በድረ ገጾችና ፌስቡክ የተለቀቀው፣ አቶ አበበ ገላው የተናገሩትን አንዳንድ አባባሎችን የያዘ ኦዲዮ ነው። ይህ ኦዲዮ አቶ አበበ፣ ሳያውቁት የተቀዳ ነው። ይህ አይነቱም ንግግርን በሚስጠር የመቅዳት የፓፓራዚ ተግባር በጣም አሳዛኝ ከመሆኑም በተጨማሪ ነውርም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት መሪዎች መታሰርን አይፈሩም

ግርማ ካሳ

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ለገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የሰላምና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። "ኢሕአዴግ እኛን እንደ ጠላት እና ሽብርተኛ ማየቱን ማቆም አለበት። እኛም ደግሞ ኢሕአዴግን እንደ አውሬ ማየት ማቆም አለብን። ከጥላቻ ፖለቲካ በመውጣት ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት መማር አለብን" ሲሉ ነበር፣ ለአገር በሚጠቅሙ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጋር ለመስራት፣ ያሉትን ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት አንድነት ፍላጎት እንዳለው የገለጹት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለግንቦት 7ም ሆነ ለሌሎች ተቃዋሚዎች ያለመተቸትን ከለላ ማን ሰጠ?

የእነ "... ወይም ሞት" ፖለቲካ

ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ
ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው የ".... ወይም ሞት" አስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ

የወያኔ ሳያንስ የነፃ አውጪዎቻችን (የግንቦት 7) የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙኀን ዝምታ
ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ

ከተወሰኑ ወራቶች በፊት "ወያኔ የሚፈጽማቸውን ስህተቶችና ወንጀሎች ሌሎች ሲፈጽሙት ትክክል ወይም ሕጋዊ ሊሆን አይችልም" በሚል ርዕስ አጠር ያለ ጽሑፍ ለአንባቢያን አቅርቤ ነበር። መልዕክቱም የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ዕድሜ እናሳጥራለን፣ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ

(ሊያነቡት የሚገባ ሰፊ ትንታኔ)

 በኃይሌ ላሬቦ

የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእኛ ታሪክና የፖለቲካ ውጥንቅጥ

ጥቂት አሳቦች በሞገደኛው ተክሌ ወሥርጉተ ሥላሴ ጽሑፎች ላይ (ክፍል-፩)

ዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን

ሥርጉተ ሥላሴ የተባሉ ጸሐፊ በተለያዩ ጊዜያት የሚጽፏቸውን በአብዛኛው ታሪካዊ የሆኑ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርስ አዘል፣ በኃይለኛው አገራዊ/ኢትዮጵያዊ ዘዬ፣ ትውፊትና ባህል የተጫነው የሚመስለውንና፤ እንዲሁም ምክርና ትችት ዘመም የኾኑ፣ እንዲያም ሲል “የኢትዮጵያዊነት ወኔና ስሜት” በእጅጉ ጎልቶ የወጣበትንና ያየለበትን መጣጥፎቻቸውን ለማንበብ ዕድሉ ገጥሞኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ