አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር
ክንፉ አሰፋ
በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም። እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል። ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ።
ክንፉ አሰፋ
በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም። እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል። ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ።
በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አስመልክቶ "ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ" ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር አድሃኖም ገብረየሱስ የጻፉትን ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ልከውልናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ለልጅ ተክሌ የተሰጠ ምላሽ
ሥርጉተ ሥላሴ
አረሙ ወያኔ በየትኛውም መስፈርት ኢትዮጵያዊነትን የመቀማት ሞራሉም ሆነ አቅሙም የለውም - በጣም በእርግጠኝነት!
ጤና ይስጥልኝ ሞገደኛው ተክሌ እንደምን ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? የብዕር አጣጣልህ እንደ አቤ ቶኬቻው ውብ ስለሆነ ለረጅም ጊዜ እያደንኩ አነባለሁ። ጠረባህንም አክሎ። በጠረባህ ዙሪያ አንድ ቀን የምለው ይኖረኛል ... ዛሬ ግን ልታገሰው ስላልቻልኩት ማለት ፈለግኩ ... በሦስት ነገሮች ዙሪያ ... እንዲህም እላለሁ ... እኔው ...
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የማለዳ ወግ፦ የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታና እዚህ ያደረሰን መንገድ!
ነቢዩ ሲራክ
ፈታኙን ወቅት ለማለፍ ...
የሳውዲ የምህረት አዋጅ አልቆ በሪያድ መንፉሃ ላይ አለምን ያሳዘነ ሰቆቃ ተፈጸመ ... ስጋት ነግሶ፣ ኑሮ ከብዶን ጨንቆን ጠቦን ከርመናል! በዚህ ክፉ ቀን ወገን ወገኑን ለመርዳት ደፋ ቀና በማለቱ ረገድ የሃገሬ ልጅ ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጭት ስሜት ሲንቀሳቀስ የፖለቲካው ትኩሳት ወላፈን እያጓተተን አልሰነበትንም አይባልም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ቅዱስ ዮሃንስ
ትምህርት ዜጎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመቅረጽ ለራሳቸው፣ ለማህበረሰባቸውና ለሀገራቸው ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ የእውቀት ማሸጋገርያ ስልት ነው። ዛሬ በስልጣኔ የገሰገሱ የአለም ሀገራት የዕድገታቸው ዋነኛ መነሻ ትምህርት ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ይሄይስ አእምሮ
ከጥቂት ሣምንታት ወዲህ በተለይ የኢትዮጵያን የወያኔ መንግሥት በሚቃወሙ የሚዲያ ማዕከላት ዘንድ ዋና መነጋገሪያ ሆኖ የሚገኘው በሳዑዲ የኢትዮጵያውያን መንገላታትና መሰቃየት እንዲሁም ከኢሰብዓዊነትም በወረደ ሁኔታ በግፍ መጨፍጨፍ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ... ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ-ካናዳ)
የሳኡዲ ግፍና የኛ ሰልፍ፤
እንደመግቢያ፤ የፋና ነገር
1. ፋና፤ ኢትዮጵያዊ ካናዳዊት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፡፡ እሱዋ እንደምትለው ከሆነ ፖለቲካ አትወድም፡፡ በአባይ ቦንድ ሽያጭና በመሰል የመንግስት መርሀ ግብር ዝግጅቶች ላይ ግን ቀድማ የምትገኝ ጎበዝ ነች፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ ተቃዋሚዎች መፈክር ይዘው በኢህአዴግ ላይ ሲሰለፉ ስትመለከት ግን ደምዋ ይፈላል፡፡ ሰሞኑን በዚህ በሳኡዲአረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ ስላሳዘናት፤ ሳውዲዎችን ልክ ልካቸውን ልትነግራቸው ቆርጣ ተነስታለች፡፡ ስለዚህም በመጪው አርብ መሰል ጉዋደኞችዋን ይዛ ሰልፍ ልትወጣ ተፍ ተፍ ትላለች፡፡ በፋና እምነት በሳኡዲ በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ሰቆቃ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኤፍሬም ማዴቦ
የኢትዮጵያ ህዝብና እናስተዳድረዋለን የሚሉት አምባገነን ገዢዎቹ ተስማምተውና አንዱ ሌላውን አክብሮ የኖረበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ የለም። የእስከዛሬው ታሪካችን ምዕራፍ በጥቅሉ ሲታይ ታሪካችን የሚቋጨው ህዝብ ተረገጠ፤ ተጋዘ፤ ገዢዎች ደግሞ ረገጡ፤ ገዙ፤ አሰሩ፤ አጋዙ እየተባለ ነው።
አሸናፊ ንጋቱ
በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት የዛሬ 22 ዓመት አንግቦት የነበረውን የዲሞክራሲ መፈክር በማየት ዲሞክራሲ የጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ጮቤ በመርገጥ ነበር የተቀበለው። ነገር ግን ይህ መፈክር ድራማ መሆኑ እየዋል እያደረ ነበር እየተጋለጠ የመጣው።
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም፣ ትርጉም፦ ነጻነት ለሀገሬ
ባለፉት አስርት ዓመታት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በአገራቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር በተለየ መልኩ ተንሰራፍቶ እየተፈጸመ ካለው ጭካኔና ርህራሄ የጎደለው አምባገነናዊ ስርዓት ለማምለጥ ሲሉ እግራቸው ወዳመራቸው አገር በመሰደድ ላይ ይገኛሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...