የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ (ክፍል አንድ)

ያሬድ ኃይለማርያም ከቤልጅየም፤ ብራስልስ
ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫ ስለሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚኖረውን ገጽታ እና ትርጓሜ ማስቀመጥ ያስቸግራል። አንዱ ሰው የሚፈራውን ነገር ሌላው ላይፈራው ስለሚችል ፍርሃት እንደ የግለሰቡ ባህሪ እና ጥንካሬ ወይም ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ የተለያየ መልክ ይኖረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ - በብሔር ብሔረሰቦች መነገድ ይብቃህ!

ኢትዮጵያ የሁሉም እኩል ሀገር ትሆናለች
ደመቀ በሪሁን
በዓለም ላይ በየጊዜው በርካታ የታሪክ አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። አንዳንዶች የተፈጠረውን አጋጣሚ በሚገባ በመጠቀም ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ታላላቅ ሥራዎችን ይሠራሉ፤ ሌሎች በአንፃሩ የተፈጠረውን አጋጣሚ በማባከን ሀገርንና ህዝብን የሚጎዳ ታሪካዊ በደል ይፈጽማሉ። ወያኔ በኢትዮጵአ በተፈጠረው አጋጣሚ ለመንግሥት ሥልጣን በቅተሃል፣ የተፈጠረውን አጋጣሚ ለምንና እንዴት እየተጠቀምክበት እንደሆነ መመልከት ጠቃሚ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በማንዴላ ሞት መንግሥቱን ከግፍ ለማንፃት?

በልጅግ ዓሊ

የማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ተመልክቶ በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ ሁኔታ ስናይ ሰነበትን። ማንዴላ የሠራውን መስራት ሳይሆን እሱ የታሰረበትን ዓላማ በተጻራሪ የሚተገብሩ ሁሉ በቀብሩ ላይ ለመገኘት ከተደበቁበት ብቅ ብቅ ማለታቸው የሚስደምም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለባለሥልጣናት እንፀልያለን፤ ግፍን ግን አንታገስም!

PM Hailemariam Deslegne ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝግርማ ካሳ

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ብዙዎች እንደ "እግዚአብሔር ሰው" ይቆጥሯቸዋል። በየቀኑ ፀሎት እንደሚያደርጉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚያነቡም ይናገራሉ። እርግጥ ነው፣ ሰዎች ፀሎት ሲያደርጉና መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነቡ፣ መልካም ነው። ነገር ግን ፀሎት ማድረግና መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ፣ በራሱ የእግዚአብሔር ሰው ያሰኛል ብዬ አላስብም። ቄስ፣ ወንጌላዊ፣ ፓስታር፣ ጳጳስ ... መሆን የእግዚአብሔር ሰው አያሰኝም። መስቀል ይዞ መዞር፣ በያሬዳዊ ዜማ ቅኔ መዝረፍ፣ በልሳን መፀለይ ... የእግዚአብሔር ሰውነት መመዘኛ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-
ሐረር እንደ ማሳያ
(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለምን ህወሓት/ኢሕአዴግ ያሸንፋል?

አማኑኤል ዘሰላም

በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት የነበረውን ሁላችንም የምናስታወሰው ነው። ያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፁን ለቅንጅት ቢሰጥም፣ ህወሓት/ኢሕአዴግ የሕዝቡን ድምፅ ነጥቆ እስከአሁን ድረስ በኃይልና በጡንቻ እየገዛ ነው። በሥልጣን ላይ ለመቆየት በቀዳሚነት አገዛዙ የወሰዳቸው አምስት እርምጃዎች ነበሩ። እነርሱም ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ ግርማ ካሣ ቀልድ ጨምሯል!

ነፃነት ዘለቀ - ከአዲስ አበባ

የግርማ ካሣን ጽሑፎች አልፎ አልፎ አነባቸዋለሁ። ሀገር ወዳድ መሆኑን ይጠቁማሉ - ጽሑፎቹ። ታታሪ ሰው ይመስለኛል፤ በጥረቱና በሀገር ፍቅር ስሜቱ እወደዋለሁ። ሁልጊዜ ሳይታክት ይጽፋል። ሳይታክቱ የሚጽፉ ብፁዓንነት የሚበዛባቸው ቢሆን ዕድለኞች ግን ናቸው። ብዙዎቻችን እየደከመን መጻፍ ቀርቶ ማንበባችንንም እያቆምን በምንገኝበት ሰዓት አዘውትሮ መጻፍ መታደል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል

ዘለቀ ረዲ

የተከበራችሁ አንባቢያን በተለመደው ግንኙነተችን መሰረት ዛሬ ከእዲስ አበባ ተነስቼ ገላን፣ ዱከም፣ ደብረዘይት፣ ቢዮዲማ፣ ሞጆ፣ ሙዳ፣ ኤጀርሳ፣ ቆቃ፣ ዐለምጤና፣ መቂ ዝዋይ አድርጌ ጉዳየን ጨርሼ ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ያቀድኩ ቢሆንም በመንገዱ መጨናነቅ ሳቢያ በመጣሁበት መንገድ ተመልሼ አዲስ አበበ መግባት ከባድ እንደሆነ ስለገመትኩ በዚያ መመለስ ሰዓቴን እንደሚጨርስ ስለተረዳሁ በዝዋይ ቡታ ጅራ እዲስ አበባ መመለስን መረጥኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግልጽ ደብዳቤ ለግንቦት ሰባት መሪዎችና አባላት

ግንቦት ሰባት Ginbot-7ግርማ ካሳ

በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። ከአምስት ዓመታት በፊት ከአንዳንዶቻችሁ ጋር፣ በቅርበት፣ በቅንጅት ድጋፍ ማኅበራት ውስጥ አብረን ሰርተናል። አብረን ለሰላም ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት መስፈን፣ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት መከበር፣ ለሕሊና እስረኞች መፈታት ስንጮህ፣ ስንሰራ፣ ስንደክም፣ ስንመክር ነበር። መሃከል መንገድ ላይ የፖለቲካ ስትራቴጂ ልዩነቶች ተፈጠሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ