ኢህአዴግ ስለምን ይጮኻል?

ተመስገንደሳለኝ

በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም በተፈጥሮ ሞት ነውና፡፡ በ1983 ዓ.ም ወርሃ ግንቦት በጠብ-መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ-መራሹ መንግስትም ቢሆን፣ በቀድሞዎቹ ገዥዎች ‹የብረት ጫማ› ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ-ስንብቱን በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ-ካሰጨነቀ፣ ካስጠበበን የመንፉሃ ሁከት መልስ!

ነብዩሲራክ

ትናንት እንደ ቀልድ ...
በያዝነው የፈረንጆች 2013 ዓም በወርሃ መጋቢት አጋማሽ የሳውዲ አረቢያ መንግስት " ህጋዊ ሰነድ ያልያዙትን አስወጣለሁ !" ብላ አወ ች ። ቀጠለና አፈሳ አሰሳው ተከተለ! አስፈሪው ያ ክፉ የጭንቅ ቀን በሳውዲው ንጉስ ሌላ የምህረት አዋጅ ተተክቶ ህገ ወጥ የተባሉትን ህጋዊ በሚያደርግ ህግ ተተካና የምህረቱ አዋጅ በያዝነው ህዳር መባቻ እንደሚያልቅ በተጠቆመው አዲስ የምህረት አዋጅ ተተካ !

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ቴዎድሮስና ሌሎቹ

ግርማ ጌታቸው ካሳ

ኢሕአዴግን እንደ አንድ የሚመለከቱ፣ ሁሉን አባላቶቹን በጅምላ የሚፈርጁ ጥቂቶች አይደሉም። ነገር ግን ኢሕአዴግ ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች አሉ። አንዱ የገነባውን አንዱ ያፈርሳል። አንዱ ሲያነሳ አንዱ ይጥላል። አንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ሲፈቅድ፣ አንዱ በጎን የዜጎችን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ይጋፋል። አንዱ የታሰሩ የሕሊና እስረኖች እንዲፈቱ ሲፈልግ፣ ሌላው "እዚያው ቃሊቲ ይበስብሱ" ይላል። አንዱ በጎና ቀና ሕሊና ሲኖረው፣ ሌላው ደግሞ የጠመመና የጫካ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን

አንዱዓለም ተፈራ

ዘግናኙ የስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ግፍ በሳዑዲ አረቢያዊያን እጅ፤ ከፊታችን ተደቅኗል። ሁላችን በያለንበት፤ "ለምን? ምን አደረግን? መጨረሻው ምንድን ነው? መቼ ነው ይኼ ሁሉ የሚያበቃው?" እያልን እርስ በርሳችን እየተጠያየቅን ነው። እኛ ወደ የምንፈልገው መንገድ ካልገባን፤ ሌላ ሊይስገባን የሚችል ኃይል የትም የለም። በሳዑዲ አረቢያ የተደረገውን ኢሰብዓዊ ድርጊት፤ ሁላችን ኢትዮጵያዊያን በግል በራሷና በራሱ እንደተደረገ በደል አድርገን ወስደነዋል። ተገቢም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሳውዲ ዐረቢያ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ዘመቻ

ወገን ለወገን ደራሽ ነው

ሜሮን አድማሱ ከኖርዌይ
በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵዊያን በሚኖሩባት ሳውዲ ዐረቢያ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ እያደረገችው ያለችው ኢሰብዓዊ ድርጊት ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ሲሆን፣ ከአንድ ኃይማኖት አለን ከሚል ሀገር የማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር ነው። በታሪክ እንደሰማነው የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ሲሠደዱ ኢትዮጵያ በጊዜው ተቀብላ መኖሪያና ማምለኪያ ቦታ እንዳልሰጠቻቸው ሁሉ፤ ዛሬ ግን በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ እያደረሰችባቸው ያለው ስቃይና እንግልት ውለታ በይነቷን ያሳያል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተማጽኖ ለጠ/ሚ ኃይለማርያም - ሳውዲን በተመለከተ

ግርማ ጌታቸው ካሳ

አይኖቼ በደም ቀሉ። ልቤ ተሰበረ። ከሳውዲ አረቢያ፣ ከባህር ማዶ፣ የወገኖቼ ጩኸትና ሮሮ፣ ከጣራዬ በታች የመነጨ ይመስል፣ በጆሮዬ በቅርበት ያቃጭላል። በርግጥ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ መዋረዳችንን አየሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኗ ሰዓት፣ እንደ ወገን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ውስጤ ደበነ። የማድርገውን ሳጣ መሬት ተንበረከኩ። አይኖቼን ወደ ላይ አንስቼ፣ እጆቼን ዘረጋሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እዚህም እዚያም አረቦች የእኛን መንግስት ያህል አልበደሉንም!

(የማለዳ ወግ) ነቢዩ ሲራክ
ትናንት ቅዳሜ ምሽት ላይ የማያልቅበትን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ምን አዲስ ነገር ይነግረን ይሆን? ብየ ከፈትኩት። ቀዳሚው ዜና የሳውዲ ጉዳየ ነው። ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም "በኢትዮጵያውያን ላይ የተለየ ጥቃት አልደረሰባቸውም!" ያሉት አስከፍቶኝ ካመሸው በሪያድ መጠለያ የሰማሁት እንግልትና ስቃይ ውል መቋጫ ጋር ተዳምሮ አሳዘነኝ! ዛሬም ሚኒስትራችን የመረጃ ምንጫቸው ችግር እንዳለበት ስረዳም ከፋኝ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጨክነው እንዳስጨከኑብን እንጨክን!

አበራ ሽፈራው /ጀርመን/

የሰው ልጅ ከተወለደበት አገር እንኳን ለመሰደድ ለአንድ ቀንም ለመሄድ አይፈልግም። በተለይም የተፈጥሮ ህግጋት፣ የኑሮ ቦታ ለውጥ፣ ለንግድ፣ለጉብኝት፣ እራሱን ለማዝናናት፣ለትምህርት፣ ቤተሠቡንና ጓደኛን ለመጠየቅ ወይም በአስገዳጅ ሁኒታ ካልሆነ በስተቀር ከሀገሩ ተለይቶ ለመኖር እንደማይፈልግ የአብዛኛው የሰው ልጅ ባህሪ መሆኑ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግና የሃይማኖት ነፃነት

ተመስገን ደሳለኝ
... ኢሠፓ መራሹ መንግስት በኢህአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በእርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግስት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የሀገሪቱ መደበኛ ወታደር፣ አብዛኛው ከእነ ትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በሀገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ