ከጎደፈው ላይ ሌላ ጉድፍ

ነብዩ ሲራክ
የማለዳ ወግ
በሪያድ መንፉሃ በተከሰተው ሁከት ግራም ነፈሰ ቀኝ ተጎጅዎች እኛ ነን! እንኳንስ ሰው ተደብድቦ፣ ሞቶባቸው፣ እንኳንስ መኪና ተሰብሮባቸው እንዲያውም እንዲው ናቸው። ከማለዳ እስከ ሌሊት የዘለቀውን ሁከት መቆጣጠር ይቻል ዘንድ ገና ሲጀመር አቅጣጫውን አይተው የመንግስት ተወካዮችን የመከሩ በርካታ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብሔራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት 'ሌጋሲ'

ክንፉ አሰፋ

ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዜግነት ዋጋ ሲያጣ

Picture: Courtesy of Abenezer Marvel.ኤፍሬም እሸቴ
ዜጋህ እንደ ወንጀለኛ በየመንገዱ እየታፈሰ ሲታሰር፣ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ደግሞ አንዱ የአገርህ ልጅ በዐረብ ፖሊስ ጥይት ተመትቶ ዋዕዩ በሚነድደው አስፓልት ላይ ደሙ ረግቶ ስትመለከት ምን ይሰማኻል? ይህ ሁሉ በሳዑዲ ምድር ላይ በየቀኑ እተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ምን ይልኻል? ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሌላ ዜግነት በቅጡ አንሶ ይሆን? ትናንት ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችባቸው 5 ዓመታት ብዙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አድርሳለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ

በተለያዩ ዐረብ ሀገራት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው በደልግሩም ተ/ኃይማኖት
ይድረስ ያልኩት በቀጥታ ባይደርሶትም መስማትዎ እንደማይቀር እገምታለሁ። ሰላም የምሎት ሰላምታ የእግዚአብሔር በመሆኑ ነው። እንጂ ጫንቃችን ላይ ተጎብራችሁ የዜግነት ክብንርን አውርዳችሁ የዜግነት ክብር የምታዘምሩ በሆናችሁ፣ በብሔር፣ በጎሳ ከፋፍላችሁ ... ሰብዓዊ መብታችንን ገፋችሁ ... ኑሮን መቋቋም እንዳንችል አድርጋችሁ ለስደት ስለዳረጋችሁን ሰላምስ ማለት አይገባም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አመፀኛው ነፋስ (በልጅግ ዓሊ)

በልጅግ ዓሊ

"ባሰላው ባሰላው እንቢ አለኝ እንዝርቱ፣
ከታችም አይደለ ከላይ ነው ጥመቱ።"
የጎንደር ሕዝብ እንጉርጉሮ

ኦክቶበር 28 እንደ ሀገሩ አቆጣጠር ጠዋት ጉልበተኛ ነፋስ ከባሕር ተነስቶ በደቡብ እንግሊዝ በኩል አድርጎ እያቆራረጠ ወደ ሰሜን ተፈተለከ። የባሕሩ ሠይጣን የላከውን ጉልበተኛውን ነፋስ የፈራው አዳሜ ፈረንጅ ሁሉ ተርበትብቶ እኛንም በሬዲዮንና በቴሌቪዚዮን ሲያርበተብተን ሰነበተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስናን አስመልክቶ ይሀ ለሰባተኛ ጊዜ ያቀረብኩት ትችት በማዕድኑ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በሙስና ላይ ያቀረብኳቸውን ሌሎችን ትችቶች “Al Mariam’s Commentaries” የሚለውን ድረ ገጽ በማየት ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሃያ ዓመት ደብዳቤ (ፈቃደ ሸዋቀና)

እንዴት ነሽ ኢትዮጵያ፣ ሠላም ነው?

እንደዘበት ትቼሽ ወጥቼ ከቀረሁ ያለፈው መስከረም ገብርኤል ሃያ ዓመት ሆነኝ። ከጠቅላላ ዕድሜዬ ከሲሶው በላይ መሆኑ ነው። ጊዜው እንዴት ይሮጣል? ያኔ ትቼሽ ስወጣ ወደኋላ እንዳላይ ብዬ ድንጋይ ወርውሬ መውጣቴን ስለምታውቂ ምነው ይህን ያህል ዘመን ጠፋህ የምትዪኝ አይመስለኝም። ምን ላድርግ። አይንሽ እያየ አይገፉ መገፋት አስገፋሽኝ። ዘር አስቆጠርሽብኝ። መገፋቴን ለምን እንደማለት በመገፋቴ ከንፈር የሚመጡ ሰዎች አብዝተሽ አሳየሽኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
ወያኔና የፖለቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፖለቲካው ስር ቁማርተኞች!

ተመስገን ደሳለኝ
በሀገራችን መንግስታዊ አስተዳደር የ"ቁማር ህግ"ን ችግር መፍቻ አድርጎ መጠቀም የ መረበትን ጊዜ ለማስላት ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ምንሊክ እንደ"ተበሉበት" ከሚነግረን የሽኩሹክታ ታሪካችን አንስቶ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት... እያልን ለመቁጠር እንገደዳለን። ይሁንና ባለሙያ (በንባብ የደረ ) ቁማርተኛ ፖለቲከኛ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛበት ድንገቴ ክስተት የ1966ቱ አብዮት ዋዜማ ነው ቢባል ወደ እውነታው ይጠጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ