The Secret ምስጢሩ ወለላዬ ከስዊድን
ስለተከሰተው ሚስጥርና የሚስጥሩን ቀላል መደረግ አሁን የሚጠይቁኝ አይመስለኝም። ይልቁንም አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ይሉኝ ይሆናል። ለዚህ በክፍል ሦስት ጽሁፌ መልስ ይዣለሁ። ከዛ በፊት ግን ታላቁ መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል? የሚስጥሩ ተጠቃሚዎችስ ምን ይነግሩናል? ይሄን አንብበው ወደ ሚስጥሩ አጠቃቀም ይሻገሩ።

 

"አምናችሁም በፀሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ"
ማቴዎስ፤ ም. ፳፩፣ ቁ. ፳፪
"የፀለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፤ ይሆንላችሁማል።"
ማርቆስ፤ ም. ፲፩፣ ቁ. ፳፬
"ነገሮች ሁሉ፤ ይለወጡልህ ዘንድ ዓለም እንደገና ራሷን ታዘጋጃለች።"
ዶ/ር ጆ ቫይታል
"የመጀመሪያው መነሻህ ታማኒነት ይሁን። የደረጃውን መጨረሻ አጠቃለህ ማየት አያስፈልግህም። ዝም ብለህ ወደ መጀመሪያው ደረጃ ውጣ።
ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጆ አር


የምስጢሩ አጠቃቀም
የምትፈልገውን ለመፍጠር ስታስብ
ሦስት ደረጃዎች እንዳሉ ተገንዘብ
ጥያቄህን አቅርብ አምነህ ሳትወላውል
የፈለከው ነገር ይመጣል ተቀበል
ለማየት ከፈለክ ይሄንን በተግባር
ፊት ለፊትህ ባለ ትንሽ ነገር ሞክር
መኪና ማቆሚያ አንድ ስኒ ቡና
የምትፈልግ ሆነህ ጥያቄ አቅርብና
ነገሩ ተሳክቶ ለማየት ስትችል
አቅምህን አዳብረህ ሌላ ደግሞ ቀጥል
ጠይቅ፣ እመን፣ አግኝ ይሄ ነው ሚስጥሩ
እጅህ ላይ ተቀምጧል መክፈቻው የበሩ
እንግዲህ ሕይወትህ በየአንዳንዱ ቀናት
በስኬት አጊጣ ትርጉም እንዲኖራት
የተዘጋባትን መንገድ ክፈትላት።
* * * * *
ወለላዬ ከስዊድን
መልዕክትና አስተያየት ካለዎት
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ