ምስጢሩ The Secretወለላዬ ከስዊድን (ክፍል ስድስት)

የገንዘብ ምስጢር
ጥሩ ግንኙነት ከሰዎች ለመፍጠር
ማወቅ የሚገባህ የሚስጥሩ ተግባር
አመለካከትህ ያለህ አስተያየት
ካፍህ የሚወጣው የንግግር ቃላት
ከፍላጎትህ ጋር ግጭት እንዳይፈጥር
አጢነህ ተመልከት እራስህን መርምር


እራስህ እራስህን ማርካት ከተሳነህ
ለሰው የምትሰጠው ምንም ነገር የለህ
አክብሮት ስትሰጥ እራስህን ስትወድ
ሌላው እንዲያከብርህ ትፈጥራለህ መንገድ
ስለራስህ መጥፎ ነገሮች ስታስብ
ለሰዎች ያለህን ፍቅር በመገደብ
ለነገር ጫሪዎች ስሜት ለሚያስቆጡ
መንገድ ትከፍታለህ ወዳንተ እንዲመጡ


የሰዎችን ድክመት አጋነህ ከመውቀስ
ጥንካሬአቸውን ጠቅሰህ ስታሞግስ
አንተ በምትሻው በፈለከው መንገድ
ይተባበራሉ አብረውህ ለመሄድ
እንግዲህ ወዳጄ ይሄ ነው ምስጢሩ
ትልቁ ብልሃት አብሮ ለመኖሩ።


መልዕክትና አስተያየት ካለዎ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!