የዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ እና መቀበል ያቃተው መራራ እውነት
ግርማ ሠይፉ ማሩ
ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” በሚል አዲስ መጽሐፍ አስነብቦናል። በአንድ ጋዜጣ ላይ የዶክተር መረራ ከዩኒቨርሲቲ መሰናበት ያመጣው አንድ በጎ ጎን መሆኑን አንብቤያሁ። እኔም በዚህ እስማማለሁ። ብዙ የሀገራችን ፖለቲካኞች ጋዜጠኛ መቅረፀ ድምፅ ይዞ በሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ ከመስጠት የዘለለ ብዕርና ወረቀት አገናኝተው የሚያምኑበትን የፖለቲካ መስመር እና በግላቸው ያላቸውን ምልከታ ማካፈል ይቸግራቸዋል።