"የጥፋት ዘመን" አዲስ መጽሐፍ በሙሉቀን ተስፋው
የመጽሐፉ ርዕስ፦ የጥፋት ዘመን
ደራሲ፦ ሙሉቀን ተስፋው
የገጽ ብዛት፦ ፪፻፺፪ (292)
ዋጋ፦ ፳፭ የአሜሪካ ዶላር ($ 25)
በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ነው። ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2007 ዓ.ም. በመላው ኢትዮጵያ በአማራው ህዝብ ላይ የደረሰውን ዕልቂትና የተቀነባበረ ዘር ማጥፋት ለሁለት ዓመታት በፈጀ ጥናት ተዘጋጅቶ በመላው ዓለም ለአንባቢያን ቀርቧል። ብዙ ምሁራን አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ”የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” በሚል ርዕስ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. አሳትመው ያወጡት መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ምርምርና ጥናት አዲስ ፈር ቀዳጅ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ውጪ (ከማዳጋስካር፣ ከኢስያ ክፍሎች) ወደ ኢትዮጵያ ፈልሶ የገባ ሲባል የኖረውን አፈ ታሪክ አሳማኝ ናቸው በሚባሉ ማስረጃዎች አስደግፈው ከእውነቱ የራቀ መሆኑን አሳይተዋል። ሁለተኛ አማራ የገዥ መደብ ተብሎ በአማራ ሥርወ መንግሥት ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች የባህል ገጽታዎቹን በኃይል ጭኖባቸዋል የሚለው ውግዘት ምንም ታሪካዊ መሠረት እንደሌለውና እንዲያውም፣ በአግአዚ/ሰሎሞናዊና በዛጉዌ ሥርወ መንግሥታት በንጉሠ ነገሥትና ደረጃ አማሮች የበላይነት ይዘው እንደማያውቁና ይልቁንም በዚህ የሥልጣን ደረጃ አብዛኞቹ ኦሮሞዎች እንደነበሩ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በዘመነ መሳፍንት በባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቱ በኢትዮጵያ ሥልጣን ይቀራመቱ የነበሩት አማሮች ሳይሆኑ፣ በተለይ የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ቁልጭ አድርገው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ አመልክተዋል። ሦስተኛ አማሮች የዘር ምድባቸው ሴማዊ (ሴሜቲክ) ሳይሆን እንደ ኦሮሞ ኩሻዊ መሆኑን፣ ሁለቱም ጎሳዎች (ጎሳ በቋንቋ መወሰኑን አመልክተዋል) የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጥንታዊ አባት ከሆነው ኩሻዊው ኢትዮጵያ ልጅ ከደሽት (ከደሴት) የመጡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ጂኦግራፊያዊ ወይም መልክዓ ምድራዊ ምንጫቸው ዛሬ ጐጃም እየተባለ የሚጠራው አካባቢ መሆኑን አመልክተዋል። እነዚህ ሁሉ አዳዲስ ታሪካዊ ግኝቶች ናቸው።


