ጥላ ከለላችን (በኩረ ይጥና)
ጥላ ከለላችን
በኩረ ይጥና ሚያዝያ 2001 ዓ.ም. / አፕሪል 2009 - ዳላስ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)
ጥላዬ ጥልዬ ብለን ስንጣራ - ከወዲያ ከወዲህ፤
ከሰውነታችን ካፋችን ሳትጠፋ - ሁሌም ስናነሳህ፤
ሰምተንህ ሳንሰለች - አይተንም ሳንጠግብህ፤
እንዲህ እንደ ዋዛ - ምነው ማሽለብህ፤
ላፍታ ሳናወራህ፤ የሆዳችንንም - ሳናጨዋውትህ፤
ሌላው እንኳን ቢቀር - ደህና ሁን ሳንልህ፤
አስደንጋጩ ዜና በዕለተ-ትንሳዔ - ተሰማ ህልፈትህ፤
“ጥላ-ከለላችን” ማሸለብክን ሰማን - እስከ መጨረሻህ፤
ጥላሁን ገሠሠ የአርቲስቶቹ ቁንጮ - የሙዚቃው ንጉሥ፤
በምትሄድበትም - በእግዚያብሔር ቤት ንገሥ፤
ከአብረሃም - ከሣራ - ከጻድቃን ጋር ተንፍስ፤
ዳግም እስክናይህ - እኛም ተራ ደርሶን
ትተህ በሄድክልን - በሙዚቃዎችህ
የጠላሽ-ይጠላ፣ የሕይወቴ-ሕይወት፣
ስትሄድ ስከተላት፤ ...
ያሳለፍነው ዘመን፣ አልቻልኩም፣ ኡኡታ፣ ያም ሲያማ፣ … ኧረ-ስንቱን እንቆጥራለን
እንዲያው በደፈናው - ሁሉን እየሰማን፤
እስከዘላለሙ እናስብሃለን፤
እንግዲህ “ጥልዬ” ከጨ ከንክ - ካመረርክ፤
ዳግም ላትመለስ - ለዘለዓለም ከሄድክ፤
አምላክ ለቤተሰብ - ለኢትዮጵያም ህዝብ
መጽናናቱን ይላክ፤
በኩረ ይጥና ሚያዝያ 2001 ዓ.ም. / አፕሪል 2009 - ዳላስ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)