የታሪክ ዘይቤ (ብዕለ ስብሐትሁ ወጥበቢሁ!)

ሰሎሞን ተሠማ ጂ.

በመጀመሪያ፣ አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመጓዝ ላይ ሳለ፣ በአጋጣሚ አንድ ወርቃማ-ቁልፍ ቢጥል በዚያው መንገድ እንደሚመለስ አያጠራጥርም። ሰውዬው የጠፋበትን ቁልፍ ለማንሳት የፈለገውን ያህል ጊዜ (ዘመን) ቢቆይም እንኳ፣ ቁልፉን ፍለጋ በዚያው በተጓዘበት መንገድ ይመለሳል። እንጂ በሌላ አቋራጭ-መንገድ አይሄድም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፋሲካ - “ሥጋዊ ወመንፈሳዊ”

ኤፍሬም እሸቴ - ኢትዮጵያዊ

በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታላቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት መካከል ትንሣኤ ወይም ፋሲካ አንዱና ዋነኛው ነው። ሃይማኖታዊ ትርጓሜው እና ምንነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ባህላዊ አከባበሩ እና ምንነቱም ከኢትዮጵያውያን ባህላዊ ማንነት ጋር በጥልቅ የተያያዘ ነው። እንኳን በአገር ቤት ያለው በሰው አገር ያለነውም እንኳን ብንሆን እንደ አቅሚቲ የአገር ቤቱን መንፈስ በያዘ ሁኔታ እናከብራለን። ስለዚህ ፋሲካው መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን ሥጋዊ/ ባህላዊ አንድምታው ከፍ ያለ ነው ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሐተታ አድዋ - በዕውቀቱ ስዩም (ደራሲና ገጣሚ)

የአድዋ ድልን ከድንበር ሉአላዊነት ጋር አያይዞ መተንተን የተለመደ ነው። ድሉ አነሠ በዛ የሚለው ጭቅጭቅ ከዚህ መሠረት ይፈልቃል። በኔ ግምት የአድዋ ድል ትልቅ ጭብጥ ‹‹የሰውነት ክብር›› ይሰኛል። ቀደምቶቻችን ወደ አድዋ የጋለቡት በግፍ የተነጠቁትን የሰውነት መታወቂያ ለማስመለስ ነው። እንዲያውም ሰው መሆናቸውን በማያዳግም መንገድ ያረጋገጡት አድዋ ላይ ነው ማለት ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የደመራ ታሪክ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

ደመራ በኃይማኖታችን፣ በታሪካችን እና በባሕላችን አንጻር

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. መስከረም ፳፻፬ ዓ.ም.

‘ደመራ’ ደመረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው። ትርጉሙ ጭመራ ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው። ጥሪት (ካፒታል) እንዳይጎድል እንዳይቀነስ ይልቁንም እየበዛና እያደገ እንዲቀጥል ጠብቆ መያዝ የሚያስችል ደመራ ነው። ስሙ እንደሚያመለክተው ማስታወሻነቱ ለተጠራቀመ፣ ለተሰበሰበና ለተጨመረ ነገር ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...