ተመስገን ደሳለኝ (ወለላዬ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

(ወለላዬ ከስዊድን)

(በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፈ መክብብ

ምዕራፍ አስራ አራት በአንክሮ ሲነበብ

«... የገዢዎች ቁጣ ሲነሳብህ ችግር

እንዳትነቃነቅ ካለህበት አገር ...»

በሚለው የጸናህ የቆየህ በቃሉ

ለካ! አንተ ኖረሃል ተሜ ባለውሉ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀን ጎዶሎ! (አትክልት አሰፋ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይህም ያልፋል? የሚሉት ቃል
ትርጉሙ ምን ይሆን? ጃል!
       አዎና…
      ሁሉም ያልፋል!!!
                 ቀን ሄዶ ቀን ይተካል፡፡
                ይሄ ነጉዶ ያ ይመጣል፤
                ትላንት ለዛሬ ይሰጣል፡
                ነገም ዛሬን ይወርሳል፡
                ዛሬ ትላንት ይሆናል፤
                ቀን መቁጠሩ ይቀጥላል፡፡
ህሊና ይንጻ'ንጅ፡
ክፋት ርቆ ከደጅ፤
አይቀር መከወኑ
መተግበር በቀኑ፡፡
               ጸጸት አይኑር በውስጥ፡
               ህሊናን የሚያፈርስ
               ፍቅ'ር የሚደመስስ፤
              ማንነትን ንዶ፡
              ራስን አዋርዶ፡
                  አይለፍ'ጅ ቀኑ…?
ዘመን ሁሉ ይለፍ
ይሂድ ይጓዝ ይክነፍ፤
ላይቀር መከወኑ
መተግበር በቀኑ፡፡
              ክብርን የሚጎዳ ለቋሚ ለኗሪ
             ቀኑ መልካም ሆኖ ካላገኘ አክባሪ
            'ይህም ያልፋል'ይሉት ብሂል
            ተጀመረ'ጅ በንጥልጥል
            ምን ትርጉም አለው ለብቻ
            ካላገኘ ሌላ አቻ
           ይህም ያልፋል!!! እንደተራ
           ታሪክ ሆኖ ካልተወራ

(ተጠናቀቀ ለፈረንጆቹ ገና ዋዜማ ሌሊት 2014)

ዘመን ሞቷል - ኃይሉ አትበሉ (ወለላዬ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Hailu Gebreyohannes (Gemoraw) ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)ወለላዬ ከስዊድን
(ግጥሙን በፒዲኤፍ አስነብበኝ!)
ማስታወሻው ጠፍቶ ምስሉ
ተገርስሶ ወድቆ አካሉ
ተሰርዞ ቃለ ውሉ
ዘመን ሞቷል ኃይሉ አትበሉ።

ታሪክ የለም አምልጦናል
ዘመን ቆመን ሞቶብናል
ሁሉም አልቆ ተጠቃሏል
ጋሼ ኃይሉ ይዞት ሄዷል

ለዘመን ነው እንባ ማፍሰስ
ለታሪክ ነው ከል መልበስ
ለጊዜ ነው ፊት መከስከስ
ለጋሽ ኃይሉ ይብቃን ማልቀስ
ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ