Dr. Hailu Araya“ፓርላማ የሚገኙት አባላቶቻችን በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሥራ ሊሠሩ በሚችሉበት ሁኔታ ጥረት ማድረግ አለባቸው” ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ

በምርጫ 97 በቅንጅት ስም ፓርላማ የገቡ 38 የፓርላማ አባላት በአንድነት ፓርቲ ስም እንዲመዘገቡ ፓርቲው ለአፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት ማመልከቻ ማስገባቱን ጥቅምት 1 ቀን 2001 ዓ.ም. ዘግበናል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ ጉዳዩን አስመልክቶ ከእንቢልታ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። 

 

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የቅንጅት ወራሽ መሆኑን በይፋ ገልፆ፣ ሕጋዊ ፓርቲ በመሆን ተመዝግቦ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል። በምርጫ 97 በቅንጅት ስም ተመርጠው፣ በፓርላማ ከገቡ 100 የሚሆኑ አባላት 38ቱ የአንድነት ፓርቲ፣ ሰሞኑን ለምርጫ ቦርድና ለፓርላማው በፃፈው ደብዳቤ፣ እነዚህ አባላት በአንድነት ስም በፓርላማው ድምፅ እንዲኖራቸው ጠይቋል።

 

አንድነት የቅንጅት ወራሽ ከሆነ ቅንጅት ፓርላማ ባለመግባት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጣቸው ስምንት ነጥቦች ለአንድነት ተመልሰውለት ነው የፓርላማ መቀመጫ የጠየቀው? ስትል የእንቢልታ ጋዜጣ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ዶ/ር ኃይሉ አርኣያን ጠይቃለች። (ሙሉውን ቃለምልልስ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ