20210302 adwa

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለቀረበለት አገርን የማዳን ጥሪ በሕብረት መልስ መሥጠት የሚገባው ወቅት ዛሬ ነው! (ኢዜማ)

EZEMA

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሠጠ መግለጫ

ለኢትዮጵያዊያን የነፃነት፣ እኩልነትና የዴሞክራሲ ጥያቄ የሕይወታቸው አካል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከውጭ ወራሪም ሆነ ከውስጥ አምባገነን አገዛዝ ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ ዛሬም መቋጫ አላገኘም። በየምዕራፉ ግን የለውጥ ጮራዎች ብልጭ ድርግም ማለታቸው ሕዝባችንን ለሠቀቀን ዳርገውታል።

በዘመናዊት ኢትዮጵያ እንኳን ከአራት በላይ የለውጥ ብልጭታዎች ታሪክ ሆነው አልፈዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ ለውጥን ማስተዳደር አለመቻል ዛሬም ትልቁ ፈተናችን ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግሥት የዜጐችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣ!! (ኢሰመጉ)

ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL

መንግሥት የዜጐችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣ!!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)
ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL
ጋዜጣዊ መግለጫ
ጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ/ም

የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት ክፍል አንድ አንቀፅ 14 ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሠሥ፣ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነትና የነጻነት መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት እንዳለውና በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን እንደማያጣ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 15 ላይ ሠፍሯል፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 32(1) ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት መብት እንዳለው በግልጽ አስቀምጧል፡፡ እንደዚሁም፣ አንቀፅ 40 (1) ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤትነት መብት አጎናጽፏል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

EPRDF

ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም.

ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ሕብረ ብሔራዊ ውሕድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ በ1996 ዓ.ም. ከተካሄደው 5ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ በተካሄዱት የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ የቆየ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል። በሁሉም የኢሕአዴግ መድረኮች በውሕደቱ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት እየተያዘበት የሄደ ሲሆን በየጉባዔዎቹ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውሕደቱን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፈፀም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ይልቁንም በቅርብ ጊዜያት በተካሄዱ ጉባዔዎች ይነሳ የነበረው ቁልፍ ችግር በአፈፃፀሙ ላይ የታየው ከፍተኛ መጓተት ነበር። በተለይ ባለፈው አመት በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የጥናት ስራው በቶሎ ተጠናቆ የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ውሕደት ፈጥረው አንድ ጠንካራ አገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር ውሳኔ ተላልፏል። በሂደቱ የአጋር ድርጅቶችም ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፅንሰ ሐሳብን በመደመር ፅንሰ ሐሳብ ለመተካት ውይይት እየተደረገ ነው” ኦዴፓ

ODP

ጥቅምት 2012

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ባለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ በቆየው ስብሰባ አሁን የደረስንበትን የትግል ምዕራፍ እና በፓርቲው ውስጥ የሚስተዋሉ ጥንካሬዎችና ጉድለቶችን በጥልቀት በመገምገም የፓርቲው ውስጣዊ ክፍተቶችን ለመቅረፍና በቀጣይ ጊዜ የሚደረገውን ትግል ስኬታማ ለማድረግ የሚያግዙ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል። በዚሁ መሠረት የኦዴፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሁለት ቀናት ስብሰባው ባካሄደው ግምገማ ላይ ተመሥርቶ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቅማንትና በአማራ ክልል ጉዳይ ላይ የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስሉ ያወጣው መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ክልል የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል

የአማራ ክልል ደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል የጋራ መግለጫና ውሳኔዎች

በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የፀጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ የሚታወስ ነው። የክልሉ መንግሥት ሕግና ሥርዓትን በተከተለ አኳኋን ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎች የቅማንት ብሔረሰብን ጨምሮ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው። ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎችና መልሶች ቅሬታ ያቀረበ ኃይል፣ ቡድንና ማኅበረሰብ ሕግና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሀሳባቸውን፣ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን አቅረበው መስተናገድ እየተቻለና ለዚህም በርካታ ዕድሎች ብሎም ጊዜያት ተሰጥተው እያለ በኃይል ፍላጎትን ለማሳካት መሞከር ፀረ ሕገ-መንግሥትና የለዬለት ፀረ ሰላም ተግባር መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ

TPLF

ጥቅምት 4 ቀን 2012

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 2/ 2012 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 7 ቀናት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በ2011 ዓ/ም ተይዘው የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች፤ ድርጅታዊና ፖለቲካዊ ስራዎች በተለይ ደግሞ በአዲሱ የፖለቲካ መድረክ የትግራይ ሕዝብ ህልውና፣ ደህንነትና ዋስትና ለማስጠበቅ የተካሄደ ሁለንተናዊ የመመከት ትግል እና ይህንን መሰረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ገምግሟል። በዚህ ልዩ የትግል ምዕራፍ የታዩ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን በመገምገም ሊወሰድ የሚችል ትምህርት በመለየት በዚህ ዓመት ሊሰሩ የሚገባቸው ልማታዊና ፖለቲካዊ እቅዶችንም አጽድቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!