ሕወሓት 45ኛ ዓመት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን አስመልክቶ የሠጠው መግለጫ
የትግራይ ሕዝብ የትጥቅ ትግል የጀመረበት የየካቲት 11 ቀን 45ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተሠጠ ድርጅታዊ መግለጫ
በዚች አገር የነበረውን ጭቆና፣ ተፅእኖና ቁጥር ስፈር የሌለው ግፍ ”እምቢ አንቀበልም፣ በፍጹም አንገዛም፣ እምቢ ለባርነት!” በማለት የትግራይ ሕዝብ በመሪ ድርጅቱ ሕወሓት እየተመራ የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 45ኛ ዓመት እያከበርን እንገኛለን። የካቲት 11 የትግራይን ሕዝብ ፅናትና ድል ወደኋላ መለስ ብለን የምናስታውስበት፣ የዛሬንና የነገ ጉዟችን ከፍተኛ ወኔና ፅናት ተላብሰን በከፍተኛ የትግል መንፈስ ወደፊት የምንገሰግስበት ዕለት ናት። የትግራይ ሕዝብ ጠብመንጃ አንስቶ ትግል ሲጀምር በጦርነት ወቅት የሚያጋጥመውን ሁለገብ ኪሳራ መገመት አቅቶት ሳይሆን ያነገበውን ቅዱስ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ተገዶ የገባበት ብቸኛ ኣማራጭ ስለነበረ ነው። የትግራይ ሕዝብ የትጥቅ ትግል ያካሄደው በኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለይ ደግሞ በትግራይ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተጭኖ የነበረውን የኣገዛዝ ቀንበር በመደምሰስ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመትከልና ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተከባብረው በእኩልነትና በወንድማማችነት የሚኖሩበት፣ በራሳቸው ጉዳይ ላይ ራሳቸው የሚወስኑበት አገር በመፍጠር የጨፍላቂዎች ህልም ለዘለዓለም የሚቀበርበት ሥርዓት በመፍጠር ከድህነትና ድንቁርና በመላቀቅ በሰላም፣ በልማት ዴሞክራሲ ጎዳና ለመገስገስ የሚያስችል መንገድ ለመጥረግ ሲል ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...



