Debre Markos University.

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 8, 2016)፦ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ማታ ቃጠሎ እንደደረሰበት ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ጠቆመ። ቃጠሎው በይበልጥ የደረሰው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የወንዶች ማደሪያ ክፍሎች (ዶርሚተሪ) ላይ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ተማሪዎች ከግቢው ለመውጣት ቢሞክሩም እንዳይወጡ ተከልክለዋል።

ከዚህ ቃጠሎ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ክስተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንዳንድ ታዛቢዎች ይናገራሉ። የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ1999 ዓ.ም. የተቋቋመ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ትምህርት ሚኒስቴር የመደቡለትን 3300 ተማሪዎች በመደበኛ መርኀ ግብር መቀበሉ ታውቋል። በዚህ ዓመት ዩኒቨርሲቲው ሠላሳ ሁለት ሺህ ተማሪዎችን በመደበኛና ተከታታይ መርኀ ግብር የመቀበል አቅም እንዳለው ተነግሯል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በደብረ ማርቆስ ከተማ ነጋዴዎች እና ወጣቱ ላይ ያተኮረ አፈሳ ሰሞኑን እንደተጀመረና አሁንም እንደቀጠለ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ይጠቁማል። ከትምህርት ገበታቸው፣ ከሥራ ቦታቸው፣ ከየመኖሪያ ቤታችውና ከየመንገዱ የሚታፈሱ ሰዎች ቁጥር እየበረከተ መምጣቱን ለመረዳት ተችሏል።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ በአማኑኤል ከተማ መልካሙ አበበ እና አሳዬ ስሜነህ የተባሉ መምህራን መታሰራቸውን ተከትሎ፤ የአማኑኤል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ሥራ በማቆማቸው የመማር ማስተማሩ ሥራ መቋረጡና ት/ቤቱ በፌዴራል ፖሊሶች መከበቡ ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ