Afaan Oromoo

አፋን ኦሮሞ

ኢዛ (ቅዳሜ መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 5, 2019):- በፌዴራል ደረጃ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎቸን ለማከል የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ስለመሆኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተጨማሪ የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ ያስችላል የተባለ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ መረጃው ተጨማሪ የመንግሥት የሥራ ቋንቋዎችን ለማከል እየተደረገ ያለውን ጥናት ተግባራዊ ለማድረግ ጥናትና እውቀትን መሠረት አድርጎ መሆን እንዳለበትም ጠቅሰዋል።

አፋን ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች ቋንቋዎችን የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎችን የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም ይኸው መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎችን የፌዴራል መንግሥቱ እንዲጠቀም የሚለው ጥያቄ በተለያዩ ወገኖች ሲንሳ የነበረ ሲሆን፣ እንደ ኢዜማ ያሉ ፓርቲዎችም ይህንን ሐሳብ በፕሮግራማቸው እስከማካተት መድረሳቸው ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት በሕገ መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ ተብሎ የተጠቀሰው አማርኛ መሆኑ ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ