PM Dr. Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

የጉብኝት ዋጋ ወጥቷል

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 4, 2019):- ለወራት በእድሳት ላይ የቆየውና ለቱሪስቶችና ለጐብኝዎች ምቹ በሆነ ዲዛይን ተጨማሪ የማስዋቢያ ሥራዎች ታክለውበት የተጠናቀቀው የአራት ኪሎው ቤተመንግሥት ከአንድ ሳምንት በኋላ ለጐብኝዎች ክፍት ሊሆን ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቤተመንግሥት እድሳት መጠናቀቁንና ሥራ መጀመሩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ ከጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ጐብኝዎች በመደበኛ ዋጋ 200 ብር በመክፈል ቤተመንግሥቱን መጐብኘት ይችላሉ፡፡

ሠልፍ ለመጠበቅ የማይፈልግና በቪአይፒ ለሚስተናገዱ ደግሞ 1,000 ብር ዋጋ የተቆረጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቤተመንግሥቱን በክፍያ ከሚመለከቱ ጐብኝዎች ቀደም ብሎ ግን፤ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌደራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ ባልደረቦች በቅድሚያ እንዲጐበኙት ይደረጋል ተብሏል፡፡

ከዚያም የተመረጡ አረጋውያን፣ የጐዳና ተዳዳሪዎች ከጐበኙት በኋላ ከፍሎ መግባት ለሚችለው የኅብረተሰብ ክፍል ክፍት ይደረጋል ተብሏል፡፡ (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ