ፕሬዝዳንቷ ቀይ መስመር መጣስ የለበትም እንበል አሉ
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ
ዘርና ሃይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሐን ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ስናይ፤ ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል
ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 31, 2019)፦ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልናሰምረውና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር መጣሱን በመግለጽ፤ ይህ ቀይ መስመር መጣስ የለበትም እንበል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቷ ኦፊሻል ፌስቡክ ገጽ ላይ እንደተመለክተው አገራችን ካንዣበበባት ክፉ አደጋ ለማዳን ሁላችንም ሚና አለን ብለዋል። ሙሉ መልእክታቸው እንደሚከተለው ይነበባል። (ኢዛ)
ዘርና ሃይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሐን ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ስናይ፤ ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል። ለቅሶ፣ ድንጋጤና ሥጋት የብዙዎችን በር አንኳኩቷል፣ ኀዘናቸው ኀዘኔ/ኀዘናችን ነው።
ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልናሰምረውና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር ተጥሷል። አገራችንን ካንዣበበባት ክፉ አዳጋ ለማዳን ሁላችንም ሚና አለን፤ የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው። “ቀይ መስመር መጣስ የለበትም!” እንበል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ



