አቶ በረከት ስምኦን (ከግራ ወደቀኝ)፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝና አቶ ታደሰ ካሣ

አቶ በረከት ስምኦን (ከግራ ወደቀኝ)፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝና አቶ ታደሰ ካሣ

የእነ አቶ በረከት የመከላከያ ምስክሮች ቃል መሰማት ጀመረ

አቶ ደመቀ፣ አቶ ገዱና አቶ ኃይለማርያም በመከላከያ ምስክርነት ቢካተቱም አልቀረቡም

ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 14, 2020)፦ እነ አቶ በረከት ስምኦን በተመሠረተባቸው ክስ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ዛሬ ማሰማት ጀምረዋል።

ትናንትና በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ እነ አቶ በረከት ምስክሮቻቸውን ትናንት ታህሳስ 4 ቀን 2012 ለማቅረብ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን፤ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ካሣ በተከሰሱበት ጉዳይ ማብራሪያ ሲሠጡ በመዋላቸው የመከላከያ ምስክሮችን ቃል ለመስማት ለዛሬ ታህሳስ 5 ቀን 2012 ዓ.ም. በመቀጠሩ፤ በዚሁ መሠረት የመከላከያ ምስክሮች ቃል መደመጥ ተጀምሯል። አለን ካሉት 11 የቃል ምስክሮች አራቱን አቅርበዋል። ሦስቱ ግን ሊቀርቡላቸው እንዳልቻሉ የተከሳሹ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

የተከሳሽ ጠበቆች ሊቀርቡላቸው አልቻሉም ያሉዋቸው ሦስቱ የቃል ምስክሮች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸውና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎ ከሰዓት በፊት የአንድ የመከላከያ ምስክር ቃል አዳምጧል።

እነ አቶ በረከት ከመከላከያ ምስክሮቻቸው ውስጥ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ቢያካትቱም ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ያልቻሉበት ምክንያት ተገልጾ አለመቅረባቸው ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ