Addis Ababa Administration

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የከተማዋ የመሬት አስተዳደር ዘርፈብዙ ችግሮች አሉበት

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 12, 2020)፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሕገወጥ መሬት ወረራ ጋር በተያያዘ እየተፈጠረ ያለው ችግር እየባሰ ስለመምጣቱ እየተገለጸ ነው። የከተማዋ የመሬት አስተዳደር ዘርፈብዙ ችግሮች እንዳሉበት ተነግሯል።

ቀድሞም ቢኾን ከመሬት ይዞታና ወረራ ጋር ተዛማች የኾኑ በረካታ መረጃዎች በተደጋጋሚ የሚሰሙባት አዲስ አበባ፤ አሁንም ይኸው ችግር እየፈተናት መገኘቱን ጥናቶች እያመለከቱ ነው።

ከሰሞኑም የፌዴራል ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ላይ እንደተመለከተውም፤ ሕገወጥ የመሬት ወረራ ለከተማዋ አስተዳደር ፈተና እየኾነ መምጣቱ ተነግሯል። የአዲስ አበባ የመሬት ወረራ መፍትሔ ያልተበጀለት ስለመኾኑ ጭምር በዚሁ ከከተማዋ የመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ እየተስተዋል ያለውን ችግርና ብልሹ አሠራርን በተመለከተ በተደረገው መድረክ ላይ ተገልጿል።

በመድረኩ የከተማዋ የመሬት አስተዳደር ዘርፈብዙ ችግሮች ያሉበት ለመኾኑ እንደምሳሌ ከተጠቀሱት ውስጥ ሙስና፣ ብልሹ አሠራሮችና ሕገወጥ የመሬት ወረራ ይገኙበታል። የመረጃ አያያዝ ድክመት፣ የግልጽነትና ተጠያቂነትን የማስፈን ችግሮች ለሕገወጥ የመሬት ወረራ መባባስ ምክንያት ኾኗል ተብሏል።

በተለይ ከዚሁ ችግር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ያለመወሰዳቸው፤ ለከተማዋ አስተዳደር ፈተና የመኾኑ ጉዳይ አሁንም እንደቀጠለ አመላካች ኾኗል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ