አቦይ ፀሐዬ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ጄኔራል ጻድቃን ወልደተንሣይ (ከግራ ወደቀኝ)

በሕወሓት ትጥቅ ትግል የጀመረበትን 45ኛ ዓመት በዓል ሲያከብር ከተገኙት ነባር ታጋዮቹ ውስጥ አቦይ ፀሐዬ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ጄኔራል ጻድቃን ወልደተንሣይ (ከግራ ወደቀኝ)

ዳግም ለኤርትራ ጥሪ አቅርቧል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 16, 2020)፦ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 45ኛ ዓመት አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው የሕወሓትን ትግል የሚያትትና ከለውጡ ወዲህ አገሪቷ ችግር ውስጥ ነች የሚለው ጎልቶ የታየበት ነው።

በዚህ መግለጫው ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻዎችን በመጥቀስ ከሕወሓት ጎን ይቆሙ ዘንድ ጥሪ ያስተላለፈበት ሲሆን፣ አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ የኮነነበት ነው።

መግለጫው ኤርትራንም የተመለከተ አንድ አንቀጽ ያካተተ ነበር። “ባለፉት 20 ዓመታት አስፈላጊ ባልኾነ ጦርነትና ግጭት ውስጥ ገብተን ሁላችንም አስፈላጊ ያለኾነ ዋጋ ከፍለናል” ይልና፤ “ይህም የፈጠረው ጠባሳ ቀላል እንደማይኾን ሁላችንም የምንገነዘበው ሐቅ ነው” በማለት ለኤርትራ ሕዝብ ብሎ ባቀረበው ጥሪ ሥር አስፍሯል።

“አሁን ግን የጋራ ጥቅማችንንና ታሪካዊ ዝምድናችንን በማደስ የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ወደሚያስችል ደረጃ እንድናሸጋግረው ሕወሓት በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል” በማለት መግለጫው ለኤርትራ ሕዝብ ጥሪ ያቀርባል።

ርዝመት ያለው የዚሁ መግለጫ ማሰሪያም ይኸው ለኤርትራ ሕዝብ ብሎ ሕወሓት ያስተላለፈው መልእክት ነው።

መግለጫው በአመዛኙ ከለውጡ ወዲህ አገሪቱ የከፋ አደጋ ውስጥ ገብታለች የሚል መልእክት ያመዘነበት ሲሆን፣ ይህንንም በተለያዩ መልኮች የገለጸበት በርክቶ ይታያል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ