የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ስም ዝርዝራቸው ነገ ማክሰኞ ይገለጻል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 24, 2020)፦ መንግሥት ጉዳያቸውን በሕግ ሲከታተሉ ነበሩ ያላቸውን 60 ተጠርጣሪዎች ምሕረት እንዳደረገላቸው አስታወቀ። ስም ዝርዝራቸው ነገ ማክሰኞ ይገለጻል ተብሏል።

መንግሥት ክሳቸው ተቋርጦ በምሕረት እንዲለቀቁ የተወሰነላቸውና እስካሁን በሕግ ጥላ ሥር የነበሩት ተጠርጣሪዎች ማንነት ባይገለጽም፤ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት፣ መንግሥት በቻይነትና በሆደ ሰፊነት የተለያዩ ጥያቄዎች በመኖራቸው የተወሰደ እርምጃ እንደኾነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ አስታውቋል።

የተለያዩ ጥያቄዎች በመኖራቸውና ትምህርት ስለተወሰደበት የ60 ዜጎች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑንም ፕሬስ ሴክሬታሪውን በመጥቀስ የወጡ መረጃዎች እያመላከቱ ነው። ክሳቸው የተቋረጠላቸውና በምሕረት የሚለቀቁትን ተጠርጣሪዎች ማንነት በነገው ዕለት (ማክሰኞ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም.) ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ያሳውቃል ተብሏል።

በጉዳዩ ላይም መግለጫ ይሠጣል ተብሎ ይጠበቃል። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሕግ አግባብ በእስር ላይ ከሚገኙ ተጠርጣሪዎች እንዲፈቱ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቅጣጫ ተሠጥቷል ማለታቸው አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ